Get Mystery Box with random crypto!

በሸገር ባስ መምህራን ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ተወሰነ በአዲስ አበባ ከተማ አስ | ልዩ መረጃ ®

በሸገር ባስ መምህራን ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ተወሰነ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በሸገር ባስ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡


በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ከሰኞ ማለትም ከ13/6/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሸገር ባስን አሁን እየተጠቀሙበት ባለው መታወቂያ መጠቀም እንዲችሉ መወሰኑን የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ሌሎች በመምህራን የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ አስቻይ ሁኔታዎችን የሚያጠና ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

@leyumerga