Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተወሰደ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮ | ልዩ መረጃ ®

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተወሰደ

ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮስ አስፋው በዛሬው ዕለት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መወሰዱን ወንድሙ ቢኒያም አስፋው ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ቴዎድሮስ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ቱሉዲምቱ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አራት ሲቪል በለበሱና ኹለት የፌደራል ፖሊስ መለዮ በለበሱ የጸጥታ አካላት መወሰዱን የገለጸው ቢኒያም፤ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዱንም አስታውቋል።

ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮስ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የፖለቲካ ትንታኔዎች በመስጠትና አግባብነት የሌላቸውን ፖለቲካዊ ሂደቶች በመተቸት ይታወቃል።

@leyumerga