Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ አውጥታው የነበሩ የማዕቀብ ሕጎችና ረቂቆች ተሰረዙ በአሜሪካ የዴሞክራት 1 | ልዩ መረጃ ®

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ አውጥታው የነበሩ የማዕቀብ ሕጎችና ረቂቆች ተሰረዙ

በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ህወሓትን በመደገፍ ወጥተው የነበሩ ማእቀቦችና ሌሎችም አስገዳጅ ህጎችና ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸው ተገለፀ። ውሳኔውን የኢትዮ-አሜሪካዊያን ምክር ቤት ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ትላንት ለካውንስሉ አባላት በተደረገ ስብሰባ ይፋ ማድረጋቸው ነው የተጠቀሰው።

ማምሻውን በተሰማው በዚህ መግለጫ፤ አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛ ምክር-ቤት መላውን ኮንግረስ ሲቆጣጠሩ የነበሩት የዲሞክራቶች ረቂቅ ሕጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው መሆናቸውን በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ካውንስሉ ገልጿል። ይህ እንዲዘገይ ለሰሩ የካውንስሉ አባላት እንዲሁም ለዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ትልቅ ምስጋና አለን ብሏል።

ምክር ቤቱ አክሎም፤ አሁን በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምን ማድረግ በሚኖርብን ጉዳይ ላይ ከአዲሱ የኮንግረስ መሪ ኬቨን ማካርቲ ሃላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩን አቶ አምሳሉ ካሳው ለአባላቱ አስታውቀዋል ሲል ገልጿል።