Get Mystery Box with random crypto!

#BelaynehKindie ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገነቡት በዓመ | ልዩ መረጃ ®

#BelaynehKindie

ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገነቡት በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም የሚያስችል የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ገለፁ።

ይኸው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነባው የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካ 2 ቢሊየን ብር ወጪ እዳደረጉበት ተሰምቷል።

አቶ በላይነህ ፤ " ፋብሪካው ከሦስት ወር በኋላ ወደማምረት ሥራ ይገባል፡፡ " ያሉ ሲሆን " በዓመት 1ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም አለው " ብለዋል።

ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሥራ ሲገባ በዚህ ዓመት ከ250 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጠሙ አቶ በላይነህ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው #ለ500 ሰዎች #የሥራ_ዕድል እንደሚፈጥር መግለጫውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።