Get Mystery Box with random crypto!

#update የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በድርጅታቸው ድጋፍ ትግራይ | LEYU NEWS

#update

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በድርጅታቸው ድጋፍ ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ላልተወሰነ ጊዜ እንደቆመ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ድርጅቱ በክልሉ የዕርዳታ ሥርጭት ያቋረጠው፣ የዕርዳታ እህል ከመጋዘን ተዘርፎ ገበያ ውስጥ እየተሸጠ መኾኑን መረዳቱን ተከትሎ ምርመራ በመጀመሩ እንደኾነ ፓዎር ገልጸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ጉዳዩን ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት ማሳወቁንና ኹለቱም በምርመራውና ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ ዙሪያ ከድርጅቱ ጋር ለመተባበር ፍቃደኛ መኾናቸው ተገልጧል። ዩኤስአይዲ የዕርዳታ አቅርቦቱን እንደገና የሚጀምረው፣ በክልሉ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት እንደተዘረጋ ካረጋገጠ ብቻ መኾኑን መግለጫው አውስቷል።


@Leyu_News
@Leyu_News