Get Mystery Box with random crypto!

በታይላንድ ገንዘብ ያበደሯትንና ፍቅረኛዋን ጨምሮ 12 ጓደኞቿን መርዛ የገደለችዉ ግለሰብ በቁጥጥር | LEYU NEWS

በታይላንድ ገንዘብ ያበደሯትንና ፍቅረኛዋን ጨምሮ 12 ጓደኞቿን መርዛ የገደለችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የታይላንድ ፖሊስ 12 ጓደኞቿን በሲአናይድ መርዝ ገድላለች የተባለችውን ሴት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታዉቋል፡፡ሳራራት ራንጊሱታፖርን የተባለችዉ ተከሳሽ በባንኮክ ከተማ የተያዘች ሲሆን የቅርብ ጓደኛዋ ሞት ጥያቄ ማስነሳቱ በቁጥጥር ስር እንድትዉል ምክንያት ሆኗል።በዚሁ ወር መጀመሪያ ላይ ከሳራራት ጋር በጉዞ ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉ በተጎጂ ቤተሰቦች ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸው ነበር።ፖሊስ ሳራራት የቀድሞ የወንድ ጓደኛዋን ጨምሮ ሌሎች 11 ሰዎችን እንደገደለች ይፋ አድርጓል፡፡ፖሊስ ድርጊቱን የፈጸመችዉ በገንዘብ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡ ሳራራት የቀረበባት ክሶች በሙሉ ግን ውድቅ አድርጋለች። የታይላንድ ፍርድ ቤት ግን የዋስትና መብቷን ዉድቅ አድርጓል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ከጓደኛዋ ጋር ከባንኮክ በስተ ምዕራብ ወደምትገኘው ራትቻቡሪ ግዛት በማቅናት የቡድሂስት ሀይማኖት ስነስርዓት በማቅናት ተሳትፈዉ ነበር ሲል ፖሊስ ተናግሯል።ብዙም ሳይቆይ ጓደኛዋ በወንዙ ዳርቻ ህይወቷ አልፎ ተገኘች፡፡የአስከሬን ምርመራ ሲደረግ በሰውነቷ ውስጥ የሳያንይድ መርዝ መገኘቱን ፖሊስ ተናግሯል። ወድቃ በተገኘችበት ወቅት ስልኳ፣ ገንዘብ እና ቦርሳዋ ጠፍቷል።

ሌሎች ተጎጂ ናቸው የተባሉት ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መሞታቸውን የገለጹት ባለስልጣናት፣ ተጨማሪ መረጃ ግን አልገለጹም። ግድያውን ሳራራት በ2020 መጀመሯን ተናግረዋል።ከሟቾቹ መካከል የሳራራት የቀድሞ ፍቅረኛዋ እና ሁለት ሴት የፖሊስ መኮንኖችን አሉበት፡፡

ፖሊስ በዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰዉ ሳራራት ከአንዲት ሴት ጓደኛዋ 250,000 ባህት ወይም 7,300 ዶላር ትበደራለች፡፡ታዲያ ጓደኛማቾቹ አብረዉ ምሳ ከበሉ በኋላ ግን አበዳሪዋ ራሷን ስታ ትወድቃለች፡፡ግን በህይወት ትተርፋለች የዚህችዉ ወጣት ቤተሰቦች ወድቃ በነበረ ጊዜ ጌጣጌጥ እና ገንዘብ መጥፋቱን ተናግረዋል ሲል ፖሊስ ለምርመራዉ ዱካ ሆኖታል፡፡ነገር ግን የጓደኛዋ ቤተሰቦቿ ሳራራት እንዲህ አድርጋለች ብለዉ ፈጽመዉ አልጠረጠሩም ነበር ያሉት የፖሊስ መኮንኖቹ፣ ይህንን ማስረጃ መሰብሰብ ፈታኝ እንደነበረበት ገልጿል፡፡አንዳንድ አስክሬኖች ተቃጥለዋል ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

ሲአናይድ የተሰኘዉ መርዝ በከፍተኛ መጠን ጥቅም ላይ ከዋለ ከአስክሬን ላይ ሊታወቅ ይችላልለ፡፡መርዙ የልብ ድካም ሊያስከትል የሚችልና የሰውነት ኦክሲጅን ከሴሎች ላይ በመዉሰድ የመግደል አቅም አለዉ፡፡በታይላንድ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲአናይድ ያለ አግባብ ይዞ የተገኘ ሰዉ የሁለት ዓመት እስራት ይጠብቃቸዋል።

ዳጉ_ጆርናል
@Leyu_News
@Leyu_News