Get Mystery Box with random crypto!

ኦነግ ሸኔና የኢትዮጲያ መንግስት በታንዛኒያ ከማክሰኞ ጀምሮ ንግግር እንደሚጀምሩ ጠ/ሚ አብይ አህመ | LEYU NEWS

ኦነግ ሸኔና የኢትዮጲያ መንግስት በታንዛኒያ ከማክሰኞ ጀምሮ ንግግር እንደሚጀምሩ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተናገሩ

ይህ የተነገረው በዛሬው እለት በተካሄደው "ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና" የምስጋና እና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በተከነወነው መርሃ ግብር ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ከኦነግ ሸኔ ጋር የፊታችን ማክሰኞ በታንዛኒያ ንግግር እንደሚጀምር በመድረኩ ገልፀዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

በመረሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News