Get Mystery Box with random crypto!

በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ። ከካርቱም በስተምስራቅ የሚ | LEYU NEWS

በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ።

ከካርቱም በስተምስራቅ የሚገኙ አካባቢዎች በጀነራል አህመድ ሃምዳን ዳጋሎ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ትልቁ የአል-ሁዳ ወህኒ ቤት መሰበሩ ተሰምቷል። እስር ቤቱ ብዙ ኢትየጵየዊያን በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የሚታሰሩበት ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹ እንዲለቀቁ ማድረጉን ተሰምቷል።

ከካርቱም 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦምዱሩማን መንገድ የሚገኝና የወንጀለኛ ቡድን መሪዎች፣ አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተገናኘ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታሰሩበት እንደነበረ ምንጮቻችን ተናግረዋል።የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹን ማስለቀቁን ተከትሎ ሃሳባቸውን የሰጡ ምንጮች ታስረው ለነበሩት ኢትዮጵያውያን መፈታት በጎ ቢሆንም በከባድ ወንጀል የታሰሩ ሰዎችም መፈታታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮ 15 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ መገደላቸው የተገለፀ ሲሆንሲሆን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቂ መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑና ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ትችቶች እንዲሰነዘሩ አድርጓል።በግጭቱ መባባስ ምክንያት ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ አእያስወጡ ሲሆንአሁን የኢትዮጵያ መንግስትም ዜጎቹን ለመታደግ ሀገራዊ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

@Leyu_News
@Leyu_News