Get Mystery Box with random crypto!

ልሳነ ግእዝ ለኩልነ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lesangeez128 — ልሳነ ግእዝ ለኩልነ
የቴሌግራም ቻናል አርማ lesangeez128 — ልሳነ ግእዝ ለኩልነ
የሰርጥ አድራሻ: @lesangeez128
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.24K
የሰርጥ መግለጫ

የግእዝ ትምህርት በyoutube ተማሩ 👇
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
@lesangeez127
@Orthodox_Addis_mezmur
@Orthodox_spiritual_poems
@eotc_books_by_pdf
@lesangeez128_bot
ተመሰረተ
9/10/2012
ለአስተያየት @asrategabriel

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 57

2022-07-13 11:23:09 ✟ የዘወትር ጸሎት በግእዝ ✟
ክፍል ፩

አአትብ ገጽየ

አአትብ ገጽየ ወኲለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።

በቅድስት ሥላሴ እንዘ አአምን ወእትመሐጸን እክሕደከ ሰይጣን በቅድመ ዛቲ እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም ጽዮን ለዓለመ ዓለም።



በYoutube ለመማር
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

ለሐሳብ አስተያየት @asrategabriel

#ሼር_ሼር_ሼር

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
2.9K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:30:00 ክፍል አንድ - የግእዝ ፊደላት

1. የግእዝ ፊደላት እነማን ናቸው?
2. የፊደላቱ ታሪክ ምን ይመስላል?
3. ለአንድ "ድምጽ" ሁለት፣ ሦስት ፊደላት ለምን?
4. የግእዝ እና የአማርኛ ፊደላት አንድ ናቸው?


በዚህ ክፍል፣ እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል። ቪዲዮውን አዳምጡ፣ "Share" በማድረግ ለሌሎች አድርሱ፣ "Subscribe" በማድረግም በየሳምንቱ የሚለቀቁትን ክፍሎች ተከታተሉ።

መልካም ጊዜ









17.1K viewsedited  03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 15:42:47 የግእዝ ቋንቋን ባላችሁበት ሆናችሁ መማር ለምትፈልጉ
-------------------------
ግእዝ አሁንም ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ቋንቋ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያኗ ድርሳናትም የተጻፉት በግእዝ ነው። ነገር ግን ቋንቋውን ባለማወቅ ብዙው ሰው ስለ ገዛ ቤተ ክርስቲያኑ ያለው ግንዛቤ በጣም ውስን ሆኖ ይገኛል። ይኼንን ክፍተት ለመሙላት ያለው መንገድ ቋንቋውን መማር ነው ብዬ አስባለሁ። በዚሁ መሠረት፣ ከታች በተቀመጠው የ"You Tube" ቻናል ቋንቋውን ለማስተማር አስቤአለሁ። ስለዚህ ሁላችሁም በያላችሁበት ሆናችሁ፣ በተከታታይ የሚቀርቡትን ትምህርቶች እንድትከታተሉ፣ የሚኖሯችሁን አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በማካፈል ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ከወዲሁ እጠይቃችኋለሁ። በየሳምንቱ የሚለቀቁት ቪዲዮች እንዲደርሷችሁም ቻናሉን "SUBSCRIBE" እንድታደርጉ፣ ለሌሎችም "SHARE" እንድታደርጉ ጨምሬ እጠይቃችኋለሁ።
ትምህርቱን ሀምሌ 6/11/2014 ዕሮብ ለመጀመር ወስነናል የምትማሩበት ቻናል










SUBSCRIBE በማድረግ ይጠብቁን
21.8K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 15:03:09 ስለ ግእዝ አኃዝ ( ቁጥሮች )

ክፍል ፪

የግእዝ ቁጥሮችን በዝርዝር ጽፈን መጨረስ ባንችልም ከብዙ በጥቂት እንመልከት


አኀዝ በፊደል - በዓረብኛ - በአማርኛ

(አልቦ) 0 (ዜሮ)

፩ (አሐዱ) 1 (አንድ)

፪ (ክልኤቱ) 2 (ሁለት)

፫ (ሠለስቱ) 3 (ሶስት)

፬ (አርባዕቱ) 4 (አራት)

፭ (ኃምስቱ) 5 (አምስት)

፮ (ስድስቱ) 6 (ስድስት)

፯ (ሰብዓቱ) 7 (ሰባት)

፰ (ሰመንቱ) 8 (ስምንት)

፱ (ተስዐቱ) 9 (ዘጠኝ)

፲ (ዐሠርቱ) 10 (አስር)

፳ (እስራ) 20 (ሃያ)

፴ (ሠላሳ) 30 (ሠላሳ)

፵ (አርባ) 40 (አርባ)

፶ (ሃምሳ) 50 (ሃምሳ)

፷ (ስሳ) 60 (ስድሳ)

፸ (ሰብዓ) 70 (ሰብዓ)

፹ (ሰማንያ) 80 (ሰማንያ)

፺ (ተስዓ) 90 (ዘጠና)

፻ (ምእት) 100 (መቶ)

፲፻ (ዐሠርቱ ምእት) 1000 (አንድ ሺህ)

፼ (እልፍ) 10,000 (አስር ሺህ)

፲፼ (ዐሠርቱ እልፍ) 100,000 (መቶ ሺህ)

፼፻ (አእላፋት) 1000,000 (አንድ ሚሊየን)

፲፼፻ (ትእልፊት) 10,000,000 (አስር ሚሊየን)

፻፼፻ (ትልፊታት) 100,000,000 (መቶ ሚሊየን)

፲፻፼፻ (ምእልፊት) 1,000,000,000 (አንድ ቢልየን)


#ቁጥሮች

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

በYoutube ለመማር
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

ለሐሳብ አስተያየት @asrategabriel

#ሼር_ሼር_ሼር

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
3.9K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:37:49 በዚህ ክረምት ሁለቱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ

|°°|ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች በሙሉ
ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #200ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251914946589 ይደውሉልን።

ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም
2.3K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 15:13:34 ግእዝ አኃዝ ( ቁጥሮች )
ክፍል ፩


አኀዝ ማለት አኀዘ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ያዘ ፣ ቆጠረ ፣ ጀመረ ማለት ነው ትርጉሙም ቁጥር ማለት ነው፡፡

አኀዝ ብለን ስንጽፍ ነጠላ ቁጥር ሲሆን አኃዝ ብለን በራብዕ ስንጽፍ ደግሞ ብዙ ቁጥሮች ይሆናል።

በሥነ ጽሑፍ ግእዝን ምሉዕ ካደረጉት አንዱ ግእዝ የራሱ ቁጥር ስላለው ነው።
በአንድ ቋንቋ ውስጥ ቁጥር ትልቅ ድርሻ አለው። የግእዝ ቋንቋም የራሱ የሆነ አኃዝ (ቁጥሮች) አሉት።

የግእዝ ቁጥሮች በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ ሥፍራ አላቸው፡፡ የግእዝ ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ እራሱን የቻለ የቁጥር አጻጻፍ ስልቶች አሉት።
ለምሳሌ

1 ➺ ፩ 10 ➺ ፲
2 ➺ ፪ 20 ➺ ፳
3 ➺ ፫ 30 ➺ ፴
4 ➺ ፬ 40 ➺ ፵
5 ➺ ፭ 50 ➺ ፶
6 ➺ ፮ 60 ➺ ፷
7 ➺ ፯ 70 ➺ ፸
8 ➺ ፰ 80 ➺ ፹
9 ➺ ፱ 90 ➺ ፺
100 ➺ ፻
10000 ➺ ፼

የግእዝ ቁጥሮች ከላይ የተመለከትናቸው ሃያው መደበኛ ቁጥሮች ሲሆን ከነዚህ ቁጥሮች ተነስተን እስከፈለግነው ድረስ መጻፍ እንችላለን።

በግእዝ ዜሮ የለም ፤ 'አልቦ' ይባላል እንጂ ይህም የሆነው በግእዝ አሥር እራሱ የቻለ አሥር ቁጥር ስላለ ነው ፡፡

የግእዙም ሆነ አሁን እኛ የምንጠቀምበት ቁጥር ማለትም ከዐ/ዜሮ/ ጀምረን የምንጽፈው የአማርኛ ቁጥር ሳይሆን ስያሜው ከየት እንደመጣ ትክክለኛ መረጃዎች ባይኖሩም 0፣ 1፣ 2፣ 3….. እየተባሉ የሚዘረዘሩት ቁጥሮች የዐረብኛ ቁጥሮች ተብለው እንደሚጠሩ በተለያዩ መጻሕፍት ተጽፈው እናገኛለን፡፡

በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር /የቀን መቁጠሪያ/ ላይ የምናገኛቸውን በየወቅቱ የሚከበሩትን ሃይማኖታዊ በዓላትንና ብሔራዊ በዓላትን ለማክበር የምጠቀመው የቀን አቆጣጠር የግእዝ ቁጥር /ኢትዮጵያዊ/ ቁጥር እንደሆኑ በግልጹ ልንረዳውና ተገቢውን ስያሜ አውቀን በስሙ ልንጠራው ይገባናል፡፡

የግእዝ ቁጥሮችን ከነስያሜያቸው በዝርዝር ጽፈን መጨረስ ባንችልም ከብዙ በጥቂት በ ክፍል ፪ እንመለከታለን


ሠናይ ሶቤ
#መጀመሪያ
#ቁጥሮች

በYoutube ለመማር
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

ለሐሳብ አስተያየት @asrategabriel

#ሼር_ሼር_ሼር

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
3.4K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:47:54 ስለ ግእዝ ፊደላት
ክፍል ፫(3)


◌ ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።

በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።

እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።

ሀ ➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል።

ሐ ➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።

ኀ ➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

አ ➺ አልፋው "አ" ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ዐ ➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ሠ ➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።

ሰ ➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

ጸ ➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።

ፀ ➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።

እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ ፦
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ
ሰአለ = ለመነ
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ

◈ይቀጥላል...
#ፊደሎች


በYoutube ለመማር
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

ለሐሳብ አስተያየት @asrategabriel

#ሼር_ሼር_ሼር

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
3.5K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:31:15 ይህ ድንቅ መጽሐፍ ከ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ የተገኘ ልዩ ገፀ በረከት ሲሆን በያዕቆብ ሰንደቁ ተተርጉሞ የቀረበ ነው።
ይህን መጽሐፍ በpdf ማግኘት ለምትፈልጉ @eotc_books_by_pdf ልታገኙት ትችላላችሁ።



3.1K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:42:11 ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ብራና

ይህ pdf መጽሐፍ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ታሪክ ከብስራቱ እስከ ዕረፍቱ የሚያስነብበን ድንቅ መጽሐፍ ነው

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube



➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
6.2K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:40:20 መልክዐ ዮሐንስ መጥምቅ

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
2.2K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ