Get Mystery Box with random crypto!

ልሳነ ግእዝ ለኩልነ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lesangeez128 — ልሳነ ግእዝ ለኩልነ
የቴሌግራም ቻናል አርማ lesangeez128 — ልሳነ ግእዝ ለኩልነ
የሰርጥ አድራሻ: @lesangeez128
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.76K
የሰርጥ መግለጫ

የግእዝ ትምህርት በyoutube ተማሩ 👇
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
@lesangeez127
@Orthodox_Addis_mezmur
@Orthodox_spiritual_poems
@eotc_books_by_pdf
@lesangeez128_bot
ተመሰረተ
9/10/2012
ለአስተያየት @asrategabriel

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-24 23:44:05 ይቅር ደብዳቤ ለመፃፍ ለምትፈልጉ በሙሉ ተጠቀሙ

Bini Girmachew

የይቅርታ ደብዳቤ ለምወዳችሁ

ለተወደድከው /ሽ/...............ስህተት ትክክል የሚመ ስለው በተሠራበት ደቂቃ ነው:: ከደቂቃ በኋላ ኅሊና ይሟገታል፡፡

እኔ ምን ያህል እንደበደልኩ የማውቀው ትንሹን ነው ብዙ በደሌን ግን ሰዎች ሊያውቁት ይችላሉ::

እስከ ዛሬ የተሰበረ ነገር አይጠገንም ብዬ አምን ነበር::

ቃሉ ግን «እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ» ስላለኝ ግንኙነታችን ይታደስ ዘንድ ይህን የይቅርታ ደብዳቤ ከዚህ የቴሌግራም ቻናል @biniGirmachew ጋር ልኬአለሁ፡፡

ይቅርታ የዓለምን ኃይል ሁሉ ያሸንፋል ብዬ አምናለሁ፡፡

የምወድህ/ሽ/

የይቅርታ ደብዳቤ ከወጣቶች፣ ለአባቶች

ለተወደዳችሁ...................በወጣትነት ሁሉም
ነገር ትክክል መስሎ ይሰማል፡፡ በወጣትነት የተበላሸ ግን
እስከ ዕድሜ ልክ የማይጠገንበት ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ በርግማን ያደግን እኛ ወጣቶችም በእሸት መቅረታችን ተሰምቶናል፡፡ ይቅርታ አድርጋችሁልን ትመርቁን ዘንድ ይህን የይቅርታ ደብዳቤ ልከናል፡፡
ከምንወዳችሁ ልጆቻችሁ



የይቅርታ ደብዳቤ ከሕዝብ፣ ለመሪዎች

ምኞት ሲርቅ እጅ ራስን መምታቱ ሕይወት ነውና ይቅርታችሁን እንጠይቃለን፡፡ መሪ የሚጦርባትና በክብር የሚቀበርባት አገርን ስላልመሠረትን በድለናል፡፡ የዚህ ሁሉ ችግር ይቅርታ ማጣት ነውና ተጸጽተናል፡፡ የዋሁ ሕዝባችን የሚለው መደለያም ሰልችቶን የእግዚአብሔርን ምሕረት ናፍቀናል። ሰው ማለት ጥሩውን ጥሩ፣ ክፉውን ክፉ የሚል ነውና ያን ብታጡብን እንኳ ይቅርታ ለመጠየቅ ወደናል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ዳኛችን ፈጣሪ እንጂ የፈረንጅ ስንዴ ላይሆን ምለናል:: በምድራችን ላይ የፍቅር ነፋስ ይንፈስ፡፡



የይቅርታ ደብዳቤ ከመሪዎች፣ ለሕዝብ


የሚቀናበት ሥልጣን የሚታዘንለት መሆኑን ልንነግራችሁ ፈለግን፡፡ ፈጣሪ ካልረዳ በጸሎት የሚያግዝ ወዳጅ ካልተገኘ እንኳን አገር ቤት መምራት ይቸግራል፡፡ ቢሆንም ዓለም ኃላፊ ነውና እናንተን ሕዝቦቻችንን በፍቅር ተቀብለን ከዚህ በፊት ባልተሞከረው በይቅርታ ሥልጣን አሁን ለመምራት ተዘጋጅተናል:: ስህተታችንን ብናምንም ወደ ራሳችን ነው ስንናዘዝ የኖርነው፡፡ አሁን ግን ሕዝባችን ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልን፡፡ ይቅርታ አየሩን ሁሉ ይለውጠው ዘንድ ወስነናል፡፡ ፈጣሪ ላስተማራቸው ወገኖች ይቅርታ ያደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔርና ለይቅርታ ቦርድ አደራ ሰጥተናል፡፡ የይቅርታ ቀን እንድትሆንም ቀንን መርጠናል።


ፈጣሪ ሆይ ፣ ለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ታዛዥ አድርገን

@biniGirmachew

#ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን
233 views20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 20:42:43 ሐምሌ 7

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጠበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡
የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡
ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገባባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

የእኛንም ጓዳ ጎድጓዳ አጋዕዝት ዓለም ቅድስት ሥላሴ በምህረቱ የጎብኝልን አሜን

ምንጭመጽሐፈ ስንክሳር ዘተዋሕዶ


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
4.2K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:07:00
1, የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቱ እና ህይወቱ
2, ጉዞ ወደ እግዚአብሔር
3, የንስሐ ትምህርት
4, የዲያብሎስ ውጊያዎች
5, ጸሎት ንስሐ እና ተመስጦ
6, ዘጠኙ የመንፈስ ፍሬዎች
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ከ61,000 ምእመናንን ጋር መንፈሳዊ መጽሐፍ ይላላኩ ያንብቡ መልካም ንባብ

█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░  𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░  𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░  𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░  𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
919 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 22:34:41 ቅዱሱ መነኩሴ አባ በምዋ ለቅዱስ አባ ቢሾይ የነገሩት።

ስለ ምንኩስና አባ በምዋ የተናገሩት

ምንኩስና የክርስትና እምነት ማሳያ ነው እናም ወደ ዘለዓለማዊ ህይወት የሚመራን አይነተኛ ባህሪ ነው መነኩሴ ስትሆን ከክርስቶስ ጋር መኖር ትጀምራለህ በሙሉ ልብህም ትከተለዋለህ።
ሁሉንም ትተህ ከሁሉ ጌታ ጋር ትኖራለህ ራስህንም ከሁሉም ነገር ትገድባለህ እናም ሁሉ በቁጥጥሩ ስር ከሆነ አምላክ ጋር ትኖራለህ ለዚያም ሲባል ነው መነኩሴ ራሱን በጸጥታ ቦታ ማለትም በተራራዎች በበረሃ እንዲሁም በዋሻ የሚኖረው።
ምንኩስና የሚለው ቃል ትርጉሙ እግዚአብሔርን መፍራት በመብላት እና በመጾም ውስጥ በእንቅልፍ እና በመንቃት ውስጥ በዝምታ እና በንግግር ውስጥ እንዲሁም በሽንፈት እና በድል ውስጥ ሁሉ እርሱን መፍራት እና መገዛት ነው።

ስለ ምንኩስና ስብእና

ራስን ዝቅ ማድረግ ራስን ከፍ አድርጎ መመልከት ከኃጢአቶች ሁሉ የከፋ ነው በመላእክት መካከል መከፋፈል የፈጠረው ሰይጣንንም ከሰማይ ወድ ምድር የጣለው ይህ ባህሪ ነው።
ነገር ግን ራስን ዝቅ ማድረግ የሰውን ልጅ ከመሬት ወደ ሰማይ ከፍ ያደርገዋል ለዚያም ነው ራስን ዝቅ ማድረግ ትልቅ ስብእና የሆነው።

ነገር ግን እንዴት ነው ራስን ዝቅ ማድረግ የሚቻለው?

ሁሌም ኃጢአተኛ እና በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገርን ያላደረግን መሆናችንን ማስታወስ ይኖርብናል በአርምሞና በትካዜ ስለ በደላችን መተከዝ ይኖርብናል መዋሸትን ተዉት ስለ መጥፎ ነገሮች አታውሩ በፍጹም ከእድሜ ታላላቆቻቹ ጋር አትገዳደሩ ሁልጊዜም ይቅር በለኝ ማለትን ተለማመዱ ከዚያም ነው ኃጢአትን እንዳትሰራ ራስህን ዝቅ የማድረግ ስብእና የራስህ ማድረግ የምትችለው ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ ከጥፋትህ በፊት መኩራራት እና ከመውደቅህ በፊት ማን አለብኝነት ይቀድማል።

ሰይጣናዊ አስተሳሰብ

ሰይጣናዊ አስተሳሰቦችን ከተጠላለፈ ነገር ጋር ማመሳሰል ይቻላል ሰይጣን በመረቡ ሊይዘን ያደባል ተስፋ በማስቆረጥ ነፍሳችንን ሊያጠቃት ይፈልጋል ወይም የውሸት ክብር በመስጠት እንዲሁም የውሸት ስብእናን በማላበስ ነገርግን ታማኝ ነፍስ በስተመጨረሻ ድል ታደርጋለች።

ስለ መልካም ስብእና የተናገሩት

ከልብህ በመነሳሳት የምታደርገው ነው ስብእና ማለት ስጋህ ለመኖር መስራት እንዳለበት ሁሉ ነፍስህም ሁሌ አምላኳን ማመስገን አለባት ካልሆነ ግን በሰይጣናዊ አስተሳሰብ ውስጥ ትጠቃለች።

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት


•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
1.6K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 10:53:53 በዚህ ክረምት ሁለቱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ°°|
  ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250 ብር certificate ለማትፈልጉ 200 ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም
2.3K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 23:45:56 ➦ የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን
➦ የ2015 ፆመ ሐዋርያት(የሰኔ ፆም)መቼ ይገባል
➦ ለምንስ ይፆማል ??

ፆመ ሐዋርያት ወይም ሰኔ ፆም ግንቦት 28 ይገባል(ይጀምራል) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።

የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን

ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምእመናን የሰኔን ጾም አይጾሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ የበረከት ጾም ነው፡፡ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ “ክርስቲያኖች ነን” ባዮች “ከመጾም ተቆጥበው ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው!” ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም

እኛ ይህን ጾም የምንጾመው
የሐዋርያትን በረከት ለመካፈል፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ዲያብሎስን ድል ማድረጊያ መሣሪያ አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምእመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

➦ ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።

የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።



➦ የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል
የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን
የተቀበሉበት እለት ነው ።

➦ ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን
በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡


ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡

➦ ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡


‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው ?አሉት

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16


➦ አሜን አሜን አሜን እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
5.1K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 01:13:15 እውነትም ድንቅ ልጅ "የቀደሙ አባቶች እጃቸው ታስረው ነበረ የሚሾሙት...ዘንድሮ ግን!

ኮሜዲያን እሸቱን ጭንቅላቱን ያስያዘው ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ልጅ

ግቡና እዩት SUBSCRIBE LIKE SHARE እንዳይረሳ የተዋህዶ ልጆች









3.9K views22:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 11:00:36
አሁን ላይ የሚያስፈልጋቸው

1) ሲሚንቶ = 7 ኩንታል -- 1650 ብር (አዲስ አበባ )

2000 ብር (በቶ-ኬንቾ)፤

2) ፓርሊን ቆርቆሮ = 50 ሜትር (1 ሜትር=380 ብር)፤

3) የኤሌክትሪክ ሽቦ = 200 ሜትር (1 ጥቅል=2700 ብር)፤

4) ሚስማር  6 ቁጥር = 3 ፓኮ (1ፓከ= 900 ብር)፤

5) ቀለም = የውሃ -- 30 ጋሎን (1 "ጋሎን = 350 ብር)፤

              = የብረት --30 ጋሎን (1 ጋሎን =1000 ብር)፤

6) ፈሮ--- 12 ሳ.ሜ.--ውፍረት = ብዛት 18

               10  ሳ . ሜ.--ውፍረት =ብዛት 10

7) መጋረጃ --- 16 ሜትር (1 ሜትር=550 ብር)

8)የመሬት ምንጣፍ--- 20 ( 1 ምንጣፍ"ጅባ"=1000 ብር)።


የቤተክርስቲያኑ  አካውንት ነው

1000261754987= ኬንቾ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

እስክሪን ሹት ብትልኩልኝ በጣም ደስ ይለኛል @BeGood16 ላይ


እግዚአብሔር በፈቀደው ያቅማቸውን አስገብ
3.7K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 08:20:07
የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች እና ሁሉንም መጽሐፍ በpdf ከ62,000member በላይ ኦርቶዶክሳዊያን ባሉበት ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በሚለው ቻናል ከ200+ በላይ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍቶችን እንዲሁም የመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁን እና የርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳንን ትምህርቶች በpdf ያገኛሉ ይቀላቀሉን።

                       
https://t.me/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
https://t.me/+7Itsth8QSrY2Y2Q0
3.4K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 08:15:25 #ሰበር_መረጃ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከሞት ተረፈ በቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ | ልጄን ግዙኝ የምትለው እናት

                   








2.3K views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ