Get Mystery Box with random crypto!

ይቅር ደብዳቤ ለመፃፍ ለምትፈልጉ በሙሉ ተጠቀሙ Bini Girmachew የይቅርታ ደብዳቤ ለምወ | ልሳነ ግእዝ ለኩልነ

ይቅር ደብዳቤ ለመፃፍ ለምትፈልጉ በሙሉ ተጠቀሙ

Bini Girmachew

የይቅርታ ደብዳቤ ለምወዳችሁ

ለተወደድከው /ሽ/...............ስህተት ትክክል የሚመ ስለው በተሠራበት ደቂቃ ነው:: ከደቂቃ በኋላ ኅሊና ይሟገታል፡፡

እኔ ምን ያህል እንደበደልኩ የማውቀው ትንሹን ነው ብዙ በደሌን ግን ሰዎች ሊያውቁት ይችላሉ::

እስከ ዛሬ የተሰበረ ነገር አይጠገንም ብዬ አምን ነበር::

ቃሉ ግን «እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ» ስላለኝ ግንኙነታችን ይታደስ ዘንድ ይህን የይቅርታ ደብዳቤ ከዚህ የቴሌግራም ቻናል @biniGirmachew ጋር ልኬአለሁ፡፡

ይቅርታ የዓለምን ኃይል ሁሉ ያሸንፋል ብዬ አምናለሁ፡፡

የምወድህ/ሽ/

የይቅርታ ደብዳቤ ከወጣቶች፣ ለአባቶች

ለተወደዳችሁ...................በወጣትነት ሁሉም
ነገር ትክክል መስሎ ይሰማል፡፡ በወጣትነት የተበላሸ ግን
እስከ ዕድሜ ልክ የማይጠገንበት ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ በርግማን ያደግን እኛ ወጣቶችም በእሸት መቅረታችን ተሰምቶናል፡፡ ይቅርታ አድርጋችሁልን ትመርቁን ዘንድ ይህን የይቅርታ ደብዳቤ ልከናል፡፡
ከምንወዳችሁ ልጆቻችሁ



የይቅርታ ደብዳቤ ከሕዝብ፣ ለመሪዎች

ምኞት ሲርቅ እጅ ራስን መምታቱ ሕይወት ነውና ይቅርታችሁን እንጠይቃለን፡፡ መሪ የሚጦርባትና በክብር የሚቀበርባት አገርን ስላልመሠረትን በድለናል፡፡ የዚህ ሁሉ ችግር ይቅርታ ማጣት ነውና ተጸጽተናል፡፡ የዋሁ ሕዝባችን የሚለው መደለያም ሰልችቶን የእግዚአብሔርን ምሕረት ናፍቀናል። ሰው ማለት ጥሩውን ጥሩ፣ ክፉውን ክፉ የሚል ነውና ያን ብታጡብን እንኳ ይቅርታ ለመጠየቅ ወደናል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ዳኛችን ፈጣሪ እንጂ የፈረንጅ ስንዴ ላይሆን ምለናል:: በምድራችን ላይ የፍቅር ነፋስ ይንፈስ፡፡



የይቅርታ ደብዳቤ ከመሪዎች፣ ለሕዝብ


የሚቀናበት ሥልጣን የሚታዘንለት መሆኑን ልንነግራችሁ ፈለግን፡፡ ፈጣሪ ካልረዳ በጸሎት የሚያግዝ ወዳጅ ካልተገኘ እንኳን አገር ቤት መምራት ይቸግራል፡፡ ቢሆንም ዓለም ኃላፊ ነውና እናንተን ሕዝቦቻችንን በፍቅር ተቀብለን ከዚህ በፊት ባልተሞከረው በይቅርታ ሥልጣን አሁን ለመምራት ተዘጋጅተናል:: ስህተታችንን ብናምንም ወደ ራሳችን ነው ስንናዘዝ የኖርነው፡፡ አሁን ግን ሕዝባችን ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልን፡፡ ይቅርታ አየሩን ሁሉ ይለውጠው ዘንድ ወስነናል፡፡ ፈጣሪ ላስተማራቸው ወገኖች ይቅርታ ያደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔርና ለይቅርታ ቦርድ አደራ ሰጥተናል፡፡ የይቅርታ ቀን እንድትሆንም ቀንን መርጠናል።


ፈጣሪ ሆይ ፣ ለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ታዛዥ አድርገን

@biniGirmachew

#ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን