Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሱ መነኩሴ አባ በምዋ ለቅዱስ አባ ቢሾይ የነገሩት። ➦ስለ ምንኩስና አባ በምዋ የተናገሩት ም | ልሳነ ግእዝ ለኩልነ

ቅዱሱ መነኩሴ አባ በምዋ ለቅዱስ አባ ቢሾይ የነገሩት።

ስለ ምንኩስና አባ በምዋ የተናገሩት

ምንኩስና የክርስትና እምነት ማሳያ ነው እናም ወደ ዘለዓለማዊ ህይወት የሚመራን አይነተኛ ባህሪ ነው መነኩሴ ስትሆን ከክርስቶስ ጋር መኖር ትጀምራለህ በሙሉ ልብህም ትከተለዋለህ።
ሁሉንም ትተህ ከሁሉ ጌታ ጋር ትኖራለህ ራስህንም ከሁሉም ነገር ትገድባለህ እናም ሁሉ በቁጥጥሩ ስር ከሆነ አምላክ ጋር ትኖራለህ ለዚያም ሲባል ነው መነኩሴ ራሱን በጸጥታ ቦታ ማለትም በተራራዎች በበረሃ እንዲሁም በዋሻ የሚኖረው።
ምንኩስና የሚለው ቃል ትርጉሙ እግዚአብሔርን መፍራት በመብላት እና በመጾም ውስጥ በእንቅልፍ እና በመንቃት ውስጥ በዝምታ እና በንግግር ውስጥ እንዲሁም በሽንፈት እና በድል ውስጥ ሁሉ እርሱን መፍራት እና መገዛት ነው።

ስለ ምንኩስና ስብእና

ራስን ዝቅ ማድረግ ራስን ከፍ አድርጎ መመልከት ከኃጢአቶች ሁሉ የከፋ ነው በመላእክት መካከል መከፋፈል የፈጠረው ሰይጣንንም ከሰማይ ወድ ምድር የጣለው ይህ ባህሪ ነው።
ነገር ግን ራስን ዝቅ ማድረግ የሰውን ልጅ ከመሬት ወደ ሰማይ ከፍ ያደርገዋል ለዚያም ነው ራስን ዝቅ ማድረግ ትልቅ ስብእና የሆነው።

ነገር ግን እንዴት ነው ራስን ዝቅ ማድረግ የሚቻለው?

ሁሌም ኃጢአተኛ እና በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገርን ያላደረግን መሆናችንን ማስታወስ ይኖርብናል በአርምሞና በትካዜ ስለ በደላችን መተከዝ ይኖርብናል መዋሸትን ተዉት ስለ መጥፎ ነገሮች አታውሩ በፍጹም ከእድሜ ታላላቆቻቹ ጋር አትገዳደሩ ሁልጊዜም ይቅር በለኝ ማለትን ተለማመዱ ከዚያም ነው ኃጢአትን እንዳትሰራ ራስህን ዝቅ የማድረግ ስብእና የራስህ ማድረግ የምትችለው ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ ከጥፋትህ በፊት መኩራራት እና ከመውደቅህ በፊት ማን አለብኝነት ይቀድማል።

ሰይጣናዊ አስተሳሰብ

ሰይጣናዊ አስተሳሰቦችን ከተጠላለፈ ነገር ጋር ማመሳሰል ይቻላል ሰይጣን በመረቡ ሊይዘን ያደባል ተስፋ በማስቆረጥ ነፍሳችንን ሊያጠቃት ይፈልጋል ወይም የውሸት ክብር በመስጠት እንዲሁም የውሸት ስብእናን በማላበስ ነገርግን ታማኝ ነፍስ በስተመጨረሻ ድል ታደርጋለች።

ስለ መልካም ስብእና የተናገሩት

ከልብህ በመነሳሳት የምታደርገው ነው ስብእና ማለት ስጋህ ለመኖር መስራት እንዳለበት ሁሉ ነፍስህም ሁሌ አምላኳን ማመስገን አለባት ካልሆነ ግን በሰይጣናዊ አስተሳሰብ ውስጥ ትጠቃለች።

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት


•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆