Get Mystery Box with random crypto!

➦ የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን ➦ የ2015 ፆመ ሐዋርያት(የሰኔ ፆም)መቼ ይገባል ➦ ለምንስ ይ | ልሳነ ግእዝ ለኩልነ

➦ የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን
➦ የ2015 ፆመ ሐዋርያት(የሰኔ ፆም)መቼ ይገባል
➦ ለምንስ ይፆማል ??

ፆመ ሐዋርያት ወይም ሰኔ ፆም ግንቦት 28 ይገባል(ይጀምራል) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።

የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን

ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምእመናን የሰኔን ጾም አይጾሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ የበረከት ጾም ነው፡፡ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ “ክርስቲያኖች ነን” ባዮች “ከመጾም ተቆጥበው ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው!” ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም

እኛ ይህን ጾም የምንጾመው
የሐዋርያትን በረከት ለመካፈል፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ዲያብሎስን ድል ማድረጊያ መሣሪያ አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምእመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

➦ ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።

የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።



➦ የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል
የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን
የተቀበሉበት እለት ነው ።

➦ ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን
በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡


ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡

➦ ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡


‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው ?አሉት

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16


➦ አሜን አሜን አሜን እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆