Get Mystery Box with random crypto!

በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር | አሚነ ፅድቅ✨

በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በአለታ ወረዳ አረጊት ኪዳነ ምሕረት በተባለችው ገዳም ሰበካ፣ ልዩ ስሙ ማር ምድር በ1930 ዓ.ም.፣ ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከወ/ሮ ለምለም ገሰሰ ተወለዱ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 4ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም. ሲኾን፣ በፖሊቲካዊ ግፊትና ጫና መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን፣ ይታወቃል፡፡ ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ የበላዮቻቸውን መካሪ፣ የበታቾቻቸውን አክባሪ፣ በሥራ ታታሪ፣ መንፈሳዊ አባትነታቸውና ትሑት ሰብእናቸው አርኣያነት ያለው ቁጥብ አባት ናቸው፡፡ ምንጭ https://bit.ly/3pBMbKC