Get Mystery Box with random crypto!

Lemlem HS

የቴሌግራም ቻናል አርማ lemhs — Lemlem HS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lemhs — Lemlem HS
የሰርጥ አድራሻ: @lemhs
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

ከት/ቤቱ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ‼️

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 17:18:22 የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ
#ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱንም ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
958 viewsAsfaw Million, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 10:50:11 " የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ
#በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል ።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።
1.8K viewsAsfaw Million, edited  07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 15:19:19 ቀን 2/12/14
ለ12 ክፋል ተማሪዎች
የማጠናከሪያ ትምህርት መጀመሩን አውቃችሁ ዛሬ ማለትም 2/12/14 በትምህርት ገበታችሁ ላይ ያልተገኛችሁ ተማሪዎች አሳማኝ ማስረጃ በመያዝ ጠዋት እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን

ት/ቤቱ
2.0K viewsAsfaw Million, 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 13:40:49
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
1.9K viewsAsfaw Million, edited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 08:52:27 የ2015 ትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር

* በክፍል ውስጥ የመደበኛ ትምህርት

መስከረም 9/ 2015 ይጀምራል።

* የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና (ሚንስትሪ) ከሰኔ 5 - 9/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 21 - 25/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* ሰኔ 30/ 2015 ዓ.ም የዓመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

መልካም የትምህርት ዘመን
1.8K viewsAsfaw Million, edited  05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:38:49 ቀን 28/11/14 ዓ.ም

ለሁሉም የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች


የማጠናከሪያ ትምህርት ከ ነሐሴ 2- ነሐሴ 30 /2014 ዓ.ም የሚሠጥ መሆኑን በድጋሚ እየገለፅን የሚከተሉትን ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን ፡-
1) የመግቢያ ሠአት 2:00 ነዉ
2) የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ 2:15 ይጀመራል፡፡
3) የሚሠጡት ትምህርቶች English , Maths , Biology ,Chemistry , physics ,Geography & History ናቸዉ
4) የመዉጫ ሠዓት 5:50 ይሆናል፡፡

ማሳሠቢያ
ሠአት ይከበር
የደንብ ልብስ መልበስ አለባችሁ
በምንም አይነት ምክንያት መቅረት ፈፅሞ የተከለከለ ነዉ ::
1.7K viewsAsfaw Million, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 19:53:33 ቀን 26/11/14
ለ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ
የማጠናከሪያ ትምህርት ከ ነሐሴ 2 - ነሐሴ 30/2014 ዓም ስለሚሠጥ አስፈለጊውን ቅድመ ዝግጂት እንድታደርጉ እያሳሰብን ፤ የአንድ ወር ትምህርት ወጫችሁንም ትምህርት ቤቱ የሽፈነ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡


ት/ቤቱ
1.7K viewsAsfaw Million, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:09:20 ቀን 20/11/14 ዓ.ም
ለነባር ከ 8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ለተዛወራችሁ ተማሪዎች በሙሉ
የ2015 ዓ.ም ምዝገባ ከሐምሌ 21-25 /14 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ብቻ መሆኑን አዉቃችሁ እንድትመዘገቡ ለማስታወስ እንወዳለን ፡፡

ት/ቤቱ
2.2K viewsAsfaw Million, 02:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:08:46
2.0K viewsAsfaw Million, 02:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 05:08:46 19.Bitaniya Adane - 82.9
1.8K viewsAsfaw Million, 02:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ