2023-02-08 21:37:43
እኔ እንደሚመሰለኝ ከሆነ አጠገባችን ያለን መልካም ሰው ውይም መልካም ስብዕና አለው ብለን ያሰብነውን ሰው ብቻ የምናይ ከሆነና ሁሏም ደና ደናውን መርጣ ካገባች ከዚ ውጪ ጸባይ ያላቸው ወንዶች በሙሉ ውሃ በላቸው ማለትኮ ነው አይደል ..
ግን እንደኔ ምልከታ..
የኔ ውይም ባሌ ይሆናል ብለን የምንጠብቀው ሰው ፍፁም መልካም... ደግ... አሳቢ.. ወዘተ ነው ብለን ካስብን እና ከደምደምን በጣም ተሳስተናል እንድዚህ አይነት ሰው design አርጋችሁ ምጠብቁ ሰዎች ካላችሁ ንቁ
ምናልባት አሁን ላይ ሰፈር ውስጥ የምታውቂው ያ ረባሽ ቢሆንስ ባልሽ...አው ውይ ይሄ ልጅስ ! ተብሎ የተወራለት..!
አው አንቺም እራስሽ እኮ "ውይ አንተን ያገባችስ.. " ብለሽው ተቀላልዳቹ ታውቁ ይሆናል
ምንም ልረዳሽ አልችልም እንግዲህ እራሱ ነው በቃ! እና ምን ልልሽ ፈልጌ ነው እሩቅ በመሄድ አትድከሚ
"ግን እንዴት..?? " አልሺኝ.. Let's see
" ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይም::"አንቺ ምታይው እና ምታወጪለት መስፈርት እንደምንም ይሁን በእግዚአብሔር አይን ግን ሲታይ የልጁን ዋጋ የተመነበት... ምናልባትም እንደዛ ኮብልሎ ድርሽዬን ብሎ እንደሄደው ልጅ አንድ ቀን አስኪ መለስ አየተጠበቀ እንዳለ ውድ ልጅ ነው የእግዚአብሔር እይታ አባት ነዋ
አንቺ ዛሬውን አይተሽ ተስፋ እንደሌለው አስበሻል እግዚአብሔር ግን ነገውን አረ እንደውም ዘላለሙን ቀድሞ አይቶታልና መልካሙን አዘጋጅቶለታል :: አስታውሽ እግዚአብሔር ታሪክን መቀየር የሚችል አምላክ ነው!
ይሄንን ስል አንድ ነገር አስታውሰኝ
አይታቹ ከሆነ ዮኒ መልካም ወጣት ላይ ከሚታዩ የባለትዳሮች እርቅን ሳይ በጣም እገረማለው አንድም በሚስት ፅናት ና ትግስት ሊያውም ፍሬ አፍርቶ ባደባባይ ድጋሚ እስከ መሞሸር..
በሌላ በኩል ደግሞ ለካ እግዚአብሔር አይሳሳትም እላለሁ ምክንያቱም ሴጣን ለጊዜው የፈለገውን ያህል እና በሚችለው መጠን ነገሮችን ቢያበላሽም ግን እግዚአብሔር ያለበት ነገር መጨረሻው ክብር ነው ፍጻሜዉ የሚያምር ነው:: ለምን መጀመሪያም የእግዚአብሔር አጀንዳ ስለነበር ነው
የመጨረሻ አንድ ነገር ልናገር... እግዚአብሔር ሔዋንን ለአዳም ፈጠራት እዳያት ወደዳት ግን ትንሽ እንደቆየ ተሳስተች በዛም አልቀረችም እሱንም አሳሳተችው ግን ስተቷን አይቶ መልሶ አልጠላትም ነበር እግዚአብሔርም በሷ ፈንታ ሌላ የትሻለ ብሎ ሌላ አልፈጠረለትም :: ስለዚህ የናንተ የናንተ ነው በቃ እኛ ነን እንጂ በልክ እና ስህተት ሰውን ምንለካው እግዚአብሔር ግን አሻግሮ ነገዎቻችን አልፎ በኛ ውስጥ ቀጣይ ትውልዳችን ከኛ ስለሚወጡ ምንግሥታት ሃያል ሰራዊት ላሰራሩ የሚመቸውን አይቶ ይመርጥልናል...
እግዚአብሔር ሉዓላዊ!!
yordi hamdi
129 views18:37