Get Mystery Box with random crypto!

እልመስጦአግያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ learn_with_john — እልመስጦአግያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ learn_with_john — እልመስጦአግያ
የሰርጥ አድራሻ: @learn_with_john
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 647
የሰርጥ መግለጫ

"እልመስጦአግያ ብሂል ትምህርተ ኃቡአተ"
እልመስጦአግያ ማለት የተሠወረ ትምህርት
—— ማለት ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ከትንሳኤው በኁዋላ በመጽሐፈ
…… ኪዳን ያስተማረው ትምህርት ነው ……
ያንብብዋ ምዕመናን እምቅድመ ቅዳሴ ንጹሕ ለዛቲ
ሃይማኖት እልመስጦአግያ
—— 《ሃይማኖተ አበው ምዕ ፪ ፥ ፩》——
#አማርኛ #ትግርኛ #ኦሮምኛ_ቋንቋ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 08:48:14
ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ
ድምጽ እንሁን ! የእርሶ ይህንን መልዕክት
ሼር ማድረግ ለቤተክርስቲያኗ ጽምጽ መሆን ላይ ዋጋ አለው።
123 viewsmihret jiff, 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:48:14
#ምንድነው_የተፈጠረው?

በቡራዩ በጠሮ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወአርሴማ ቤተክርስቲያን ምንድነው የተፈጠረው ?

በ2005 ዓ.ም በባለራዕይ ታይቶ በ17 ክ/ዘመን ተቀብሮ የነበረ የወርቅ ጽላት እንዲሁም ፈዋሽ ጸበል የፈለቀበት ሥፍራ ነው።

በጸበሉም ብዙዎች ከአጋንንት እስራት ተፈተዋል፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ የተያዙ ብዙዎች የዳኑበት ታላቅ የበረከት ስፍራ ነው።

ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኗ የተተከለችው #የገበሬ_ማሳ ላይ በመሆኑ የራሱ መሬት የሌለው እና የቤተክርስቲያን መስሪያ ለነገ በማሰብ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ከገበሬው ላይ በ4,000,000/አራት ሚሊየን ብር /በ2 ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ በዱቤ ገዝቶ ነበር። ነገር ግን በቡራዩ አካባቢ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በኮቪድ 19 እንዲሁም ቦታው ከከተማ ወጣ ያለ በመሆኑ የምዕመናን እንቅስቃሴ ቀንሷል።

በዚህም ምክንያት በዱቤ የተገዛው መሬት ዋጋን ሳንከፍል ቀን ገደባችን ደርሶብናል። በመሆኑም የመሬቱ ባለቤት ገንዘቡ በጊዜው
ስላልተሰጠኝ የመሬት ውል አፍርሼ መሬቱን ለሌላ አካል ዋጋ ጨምሬ እሸጠዋለሁ በማለት አሳውቆናል። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤ እና ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ መሬቱን ለሌላ የቤተ እምነቶች ማለትም "ቸርች" እና "መስጊድ" እንሰራበታለን የሚሉ ገዝተው ሳይሰሩበት ቤተ ክርሰቲያን ልጆች የሆናችሁ ሁሉ ድረሱልኝ እያሉ ይገኛሉ።

በጠሮ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወአርሴማ ቤ/ክ ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000251919217

ስልክ :0912060052
:0917810611
:0912715915
110 viewsmihret jiff, 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 07:16:24
​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ።
ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።
ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
237 viewsmihret jiff, 04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 17:30:42 ሰውነታችሁን_ለሰይጣን_ምቹ_አታደርጉ!




ተወዳጆች ሆይ የብዙዎቻችን ሰውነት ለሰይጣን ምቹ ነው፡፡ ለሰይጣን ምቹ ሰውነት ማለት ንስሐ ያልገባ በኃጢአት ግራ የሚጋባ ሰውነት ነው፡፡ ለሰይጣን ምቹ የሆነ ሰውነት ማለት በሐሜት፣ በቧልት፣ በምቀኝነት፣ በክፋት፣ በዝሙት፣ በስኳር፣ በአድመኝነት፣ በዘረኝነት ወዘተ የረከሰ ሰውነት ማለት ነው፡፡

ለሰይጣን ምቹ ሰውነት ማለት ለፈጣሪ የማይንበረከክ፣ ሰማያዊ አምልኮት የማያቀርብ፣ የማይሰግድ፣ የማይጸልይ፣ የማይጾም፣ ቅዱስ ቁርባን የማይቀበል ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ሰውነት ለምጽዋት የተዘረጋ ነው፡፡ ነገር ግን በዝሙት የረከሰ ነው፡፡ ይህ ለሰይጣን ምቹ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ጸሎተኛ ነን፡፡ በጸሎተኝነታችን ልክ እጅግ ሐሜተኛ እና ቅናተኛ ነን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን እጅግ አማኝ እና ሰርክ ለኪዳን፣ ለቅዳሴ እና ለጉባኤ ከቤተ ክርስትያን የማንርቅ ነን፡፡ ነገር ግን ሲበዛ ቂመኛ እና ይቅርታ የለሾች ጨካኝ ነን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡ አንዳንዶቻችን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን አንደበታችንን በመዓዛ መለኮት ማጣፈጥ እየቻልን ‹‹እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝና›› እያልን አንደበታችን በሐሜት የመረረ ነው፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
አንዳንዶቻችን በመንፈሳዊ እውቀታችን ሰዎችን መክረን፣ አስተምረን ከኃጢአት መልሰን ለንስሐ እናበቃለን እኛ ግን ተመክረን የማንሰማ፣ ከኃጢአታችን መመለስ ያቀተን፣ ንስሐ የማንገባ ለቅዱስ ቁርባን የማንበቃ ነን፡፡ በዚህ ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን የወሲብ ፊልም ማየት፣ ግለ ወሲብ መፈጸም ኃጢአት እንደሆነ ለሰው እንናገራለን እናስተምራለን በዚህም እነዛ ሰዎች ከዚህ ሰይጣናዊ ሱስ ተላቀው ንስሐ ይገባሉ ልማደ ሰይጣንንም ይተዋሉ፤ እኛ ግን ሰው ባላየ እግዚአብሔር ባየ የወሲብ ፊልም እናያለን ግለ ወሲብ እንፈጽማለን፡፡ በዚህም ለሰይጣን እንመቻለን፡፡
አንዳንዶቻችን መጽውቱ ብለን ሰዎች እንዲመጸውቱ፣ ድሆችን እንዲረዱ እናደርጋለን፡፡ የእኛ እጅ ግን በታንክ ፍሬን ተይዟል፣ መመጽወትም እንቢ ብሎናል፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን ሰዎች ሲያማቸው እንዲጸልዩ፣ ጸበል እንዲጠመቁና በዚህም እንደሚድኑ መክረን እነዛ ሰዎች በምክራችን ተጠቅመው ጸልየው ተጠምቀው ይድናሉ፡፡ እኛ ስንታመም ግን እምነት አጥተን በየሆስፒታሉ እንንከራተታለን፡፡ በዚህ ለሰይጣን ምቹ ነን፡፡
ወዳጆቼ በየትኛውም ጉድለታችን ሰይጣን ወደ ሕይወታችን ይገባል፡፡ ሰይጣን ትንሿን ስህተታችንን፣ የኃጢአት ፍላጎታችንን አይቶ ወደ እኛ ጎራ ይልና ትንሿን ስህተት ትልቅ፣ ኃጢአትን ደግሞ ጽድቅ አድርጎ የእሱ መጫወቻ ያደርገናል፡፡

ሰይጣን አንዴ በዝሙት ከጣለን ስሜታችን ደግሞ ደጋግሞ ይጥለናል፡፡ ሰይጣን በመርፌ ቀዳዳ ስህተት ይገባና እኛ ግን ከስህተታችን በሰፊው በር መውጣት ያቅተናል፡፡
ዛሬ ሥጋዊ ፍላጎታችን፣ ዓላማችን፣ እውቀታችን፣ ትምህርታችን፣ ርእዮተ ዓለማችን፣ አመለካከታችን በራሱ ለሰይጣን ምቹ ስለሚሆን ልናስተውል እና ልንነቃ ይገባናል፡፡ ዛሬ ከላይ እስከታች፣ ከቤተ ክህነት እስከ ቤተ መንግስት፣ ከዓለማዊው እስከ መንፈሳዊው፣ ከምሁሩ እስከ ፊደል ነውሩ፣ ከወጣቱ እስከ አዛውንቱ ያለነው ሰውነታችን ለሰይጣን ምቹ ስለሆነ ሕይወታችን በፈተና፣ በስቃይ፣ በመንፈሳዊ ባዶነት የተመላ ነው፡፡
እግዚአብሔር ‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፣ ሰውነታችሁን ቀድሱ፣ ቅዱሳንም ሁኑ›› ብሎ አዞናል፡፡

ነገር ግን ሰውነታችንን በኃጢአት አረከስን፣ ሕገ እግዚአብሔርንም አፈረስን፡፡ በዚህም ለሰይጣን ምቹ ሆንን፡፡ ሰይጣን ለራሱ ምቹ በሆነ ሰው እና ሰውነት ላይ እንደፈለገ ይሆናል፣ የፈለገውን ዓላማ ይፈጽማል፣ ለሚፈልገው ዓላማ መጠቀሚያ ያደርገዋል፡፡ /ዘሌ 11÷44/
ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኃለሁ›› በማለት የልመና ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ /ሮሜ 12÷1/
በእውነት ሰውነታችን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው? ሰውነታችን ቅዱስ እና መሥዋዕት ነው? ሰውነት በኃጢአት ሲረክስ ነፍስም ትረክሳለች፡፡

ልብ በሉ ቆሻሻ ነገር ላይ እና ቆሻሻ ስፍራ ላይ ዝንቦች ይሰፍራሉ፡፡ በኃጢአት የቆሸሸ እና የተበላሸ ሰውነት ላይ አጋንንት ይሰፍራሉ፡፡ በቆሻሻ ነገር እና በቆሻሻ ስፍራ ላይ ዝንቦች ለሰው ጎጂ የሆኑ በሽታዎችን ያከማቻሉ፡፡
በኃጢአት በቆሸሸ ሰውነት ላይም አጋንንት መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያጠለሽ፣ ነፍሳችንን የሚያቆሽሽ ክፉ መርዙን ይረጫል፣ ጎጂ የሆነ ኃጢአትንም ያጠራቅማል፣ የሥጋ እና የነፍስ በሽታ ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር በዘሌ 11÷43 ላይ ‹‹በእነርሱ እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱ›› ብሎናል ‹‹በእነርሱ እንዳትረክሱ›› ያለው አንድም በሰይጣን ክፉ ምሪት እና ተግባራት ሰውነታችንን፣ ነፍሳችንን እንዳናረክስ ነው፡፡

ስለዚህ ሰውነታችሁን ለንስሐ፣ ለጽድቅ፣ ለጾም፣ ለጸሎት፣ ለስግደት እና ለቅዱስ ቁርባን ምቹ አድርጉ እንጂ በፍጹም ለሰይጣን ምቹ አታድርጉ፡፡

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ- ማርያም
286 viewsmihret jiff, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:02:49
ሙሽሮቹ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሉ ና ሣምራዊት ደመቀ
እንኳን ደስ አላችሁ እግዚአብሔር ትዳራችሁ ያባርክ
አሜን አሜን አሜን
907 viewsmihret j, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 11:18:16
''እስመ በትህትና ትትረከብ ልዕልና''

"ኦ ትሕትና ዘመጠነ ዝ ትሕትና::
†††
"ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው::
(ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ)
+++++
ብፁዕ አቡነ አብርሃም (የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) እና
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)
ለሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በጠቅላይ ሥራ አስኪጅነትና በቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊነት ለመምራት ተመርጠው፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ማርያም ሲቀበሉ፤
407 viewsmihret j, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 17:01:02
ማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ያስገነባቸውን አራት አብያተክርስቲያናት ሊያስመርቅ ነው!!!

በማኅበረቅዱሳን አስተባባሪነት በደቡብ ኦሞ ሀገረስብከት ግንባታቸው የተጠናቀቁ የአራት አብያተክርስቲያናት ሕንጻ ቡራኬና ቅዳሴ ቤት ከግንቦት 26-29 ቀን ዓ.ም ይከናወናል።

1. ከግንቦት 26-27 ቀን 2014ዓ.ም (ዓርብና ቅዳሜ) በበናጸማይ ወረዳ የይርጋ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሕንጻ
2. ከግንቦት 27-28 ቀን 2014ዓ.ም (ቅዳሜና እሑድ) በበናጸማይ ወረዳ የጎልድያ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሕንጻ
3. ከግንቦት 27-28 ቀን 2014ዓ.ም (ቅዳሜና እሑድ) በማሌ ወረዳ የአጆ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሕንጻ
4. ከግንቦት 28-29 ቀን 2014ዓ.ም (እሑድና ሰኞ)በዳሰነች ወረዳ የካፑሲያ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሕንጻ

እርስዎም በተጠቀሱት ዕለታት ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመገኘት በበዓሉ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።

የለብንም ስተት ካወራን በዋላ ሁሉም ነገር በትክክል እሄደ ነው ለዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ከልብ አመሰግናለሁ

ወደፊትም አንድ ላይ ተጠናክረን እንቀጥላለን
331 viewsmihret j, 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:14:01
242 viewsmihret j, 08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 11:01:32 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

=>ግንቦት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና)
3.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት
4.አባ ሖር ጻድቅ
5.አባ ዳርማ ገዳማዊ
6.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ
7.አባ ዘትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
231 viewsmihret j, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 08:47:40
#እፎ ኃደርክሙ?
እንዴት አደራችሁ?

✞✥✟
ሰናይ መዓልት!!
መልካም ቀን!!
✞✥✟

@Learn_with_John

ለሌሎች ያጋሩ
ለአስተያየት @JohnDPT27
✞✥✟
182 viewsmihret j, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ