Get Mystery Box with random crypto!

ሊያና ኬር Liyana Care 7755

የቴሌግራም ቻናል አርማ ldhsethiopia — ሊያና ኬር Liyana Care 7755
የቴሌግራም ቻናል አርማ ldhsethiopia — ሊያና ኬር Liyana Care 7755
የሰርጥ አድራሻ: @ldhsethiopia
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.07K
የሰርጥ መግለጫ

➮ የጤና ምክሮች 👨‍⚕️
➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755
➮ ቴሌሜዲስን 💉
➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-22 15:05:19
The world is moving towards digitization. Our center, Liyana Digital Healthcare Solutions, as the first licensed telemedicine company in Ethiopia, is working tirelessly towards realization of digital healthcare service delivery.

We would love to thank Safaricom Telecommunications Ethiopia in becoming part of this journey. We had such a great session with the employees after presentation of a webinar by our experienced psychiatrist Dr.Selam.

We look forward to a fruitful partnership.
742 views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 14:54:55
261 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:36:53 የጉበት ንቅለተከላ (Liver transplantation)

የጉበት ንቅለተከላ በትክክል መስራት ያቆመ ጉበት በጤናማ ጉበት የሚተካበት የቀዶጥገና ሂደት ነው፡፡

የጉበት ንቅለተከላ ቀዶጥገና ከ 6-12 ሰዓታትን ሲፈጅ ከ 85% እስከ 95% ስኬታማ የመሆን እድል አለው፡፡

በአሜሪካ የጉበት ፋውንዴሽን መረጃ መሰረት በየአመቱ 6000 የሚሆኑ የጉበት ንቅለተከላዎች በአሜሪካ ውስጥ ይካሄዳሉ፡፡ አፍሪካ ውስጥ ግን የጉበት ንቅለተከላ የሚደረገው በጣም በጥቂት ቦታዎች ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህም በየአመቱ አፍሪካ ውስጥ የሚደረጉ የጉበት ንቅለተከላዎች ቁጥር በጣም አናሳ ነው፡፡

ጉበት ከጉዳት በኋላ ራሱን የመጠገን ብቃት ካለው ምን ሲፈጠር ነው ሙሉ በሙሉ መስራት የሚያቆመው?

ጉበት ሁለት ሶስተኛ ክፍሉ ቢጎዳ ወይም ተቆርጦ ቢወጣ እንኳን ራሱን መጠገን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጉበት ራሱን መጠገን እስኪያቅተው ድረስ በጣም ሲጎዳ ራሱን መጠገን ያቅተውና መስራት ለማቆም ይገደዳል፡፡

ጉበት መለገስ የሚችለው ምን አይነት ሰው ነው?

የደም አይነቱ ለጉበት ተቀባዩ ሰው ተስማሚ የሆነ ሰው

የሰውነት መጠኑ ከተቀባዩ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ሰው፡፡ አንዳንዴ ግን ለጋሽ እና ተቀባዩ ተቀራራቢ መጠን ባይኖራቸውም የጉበት ንቅለ ተከላ ሊደረግ ይችላል፡፡

በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው

ከሱሶች ነፃ የሆነ ሰው

እድሜው ከ 18 እስከ 60 የሆነ ሰው

ጤናማ ክብደት ያለው ሰው

የጉበት ንቅለ ተከላ አይነቶች

1.ከሞተ ለጋሽ ተወስዶ የሚደረግ የጉበት ንቅለ ተከላ

በዚህ ሂደት ጤናማ ጉበት ከሞተ ሰው ይወሰድና ለታማሚ ሰው ይሰጠዋል፡፡ ይህ ቀዶ ጥገና ሰውየው በሞተ በ24 ሰዓት ውስጥ ስለሆነ የሚደረገው ጉበት ተቀባዩ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ሊነገረው ይችላል፡፡

2.በህይወት ካለ ለጋሽ ተወስዶ የሚደረግ የጉበት ንቅለ ተከላ

ይህ የጉበት ንቅለ ተከላ አይነት ከጤናማ ሰው የተወሰነ የጉበት ክፍል ወስዶ ወደ ታማሚ ሰው የሚተላለፍበት ሂደት ነው፡፡ ለጋሽ እና ተቀባዩ ጎን ለጎን ያሉ ቀዶ ጥገና ክፍሎች ውስጥ ሆነው ነው ቀዶ ጥገናው የሚካሄደው፡፡ ጉበት ራሱን የመጠገን ችሎታ ስላለው የለጋሹ እና የተቀባዩ ጉበት ጤናማ ወደሆነ የጉበት መጠን በጊዜ ሂደት ይመለሳሉ፡፡

3. ስፕሊት ዶኔሽን( Split donation)

ከሞተ ሰው የተወሰደ ጉበት ሁለት ቦታ ተከፍሎ ለሁለት ታማሚዎች የሚሰጥበት ሂደት ነው፡፡

በጉበት ንቅለተከላ ጉበት ያገኙ ሰዎች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የጤና ችግሮች

የሰውነት አዲሱን ጉበት መጉዳት(organ rejection)- ይህ የሚፈጠረው የተቀባዩ የበሽታ መከላከል ስርዓት አዲሱን ጉበት እንደ እንግዳ አካል ስለሚያየው ነው፡፡ ይህንን ሂደት ለመቀነስ የበሽታ መከላከል ስርዓትን የሚያዳክሙ መድሀኒቶችን መጠቀም እንችላለን፡፡

ኢንፌክሽን

ግፊት

ስኳር

ካንሰር

የጉበት ንቅለ ተከላ ካደረጉ ሰዎች 75% ያህሉ ቢያንስ አምስት አመት በህይወት የመቆየት እድል ሲኖራቸው 53% ያህሉ ደግሞ ቢያንስ ሀያ አመት በህይወት የመቆየት እድል አላቸው፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
157 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:36:30
152 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 10:19:20 በእድሜ የገፉ እናት/አባት ጤና ያሳስቦታል? የጤንነታቸውን ጉዳይ ለመከታተል ጊዜ ማግኘት አልቻሉም? ያሉበትን የጤና ሁኔታ እንዲሁም መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ እና የሚወስዱትን እያንዳንዱን መድሀኒት በቤትዎ ሆነው በሞባይል ስልክዎ መከታተል ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ሊያና ዲጂታል ሄልዝ ኬር ሶሉሽንስ መፍትሄ ይዞሎት መጥቷል፡፡

በየ2 ሳምንት በቤትዎ የሚደረግ የሀኪም ክትትል

በየ2 ሳምንት በስፔሻለሊስት እንዲሁም በሰብ ስፔሻሊስት የሚደረግ የርቀት ህክምና (virtual consultation)

ነጻ የስነአዕምሮ(psychiatry) ማማከር አገልግሎት

በወር አንድ ጊዜ የሚደረግ አስፈላጊ ላብራቶሪ ምርመራ

በፈለጉት ጊዜ በመደወል በፈለጉት የጤና ጉዳይ ላይ የሚሰጥ ማብራሪያ እና የምክር አገልግሎት

እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች በወር አንድ ጊዜ ብቻ እጅግ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755/+251910202776 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
266 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 10:19:09
241 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 09:56:44 ዳውን ሲንድረም (Down Syndrome / Trisomy 21)

ዳውን ሲንድረም ማለት በልጅ አፈጣጠር ስርዓት ውስጥ በሚገኙ ህዋሳቶች መካከል በሚፈጠር ችግር የሚከሰት እክል ነው። በሌላ አነጋገር ዳውን ሲንድረም የዘረመል(genetics) ችግር ነው።

ጠለቅ ባለ መልኩ ደግሞ ስናየው ይህ ችግር የሚያጠቃው የሰውነታችን ክፍሎች የሚሰሩበትን መልዕክት የሚይዙ ህዋሶችን ነው፡፡ እነዚህ ህዋሶች ክሮሞሶም(chromosome) ተብለው ይጠራሉ። እናም አንዳንዴ ባልታወቀ ምክንያት በእርግዝና ጊዜ ህዋሶቻችን በሚከፋፈሉበት ጊዜ ስህተት ይፈጥራሉ።

ይህ ስህተት ምንድነው? በትክክለኛው ሁኔታ አንድ ሰው 46 ወይም 23 ጥንድ ክሮሞሶምች ሲኖሩት ዳውን ሲንድረም ያላቸው ሰዎች ግን 47 ክሮሞሶም አሏቸው። ይህ ትርፍ ክሮሞሶም የሚገኘው 21ኛው ክሮሞሶም ላይ ነው። ለዛም ነው Trisomy 21 ተብሎ ሚጠራው፤ Tri ማለት 3 ማለት ሲሆን 21 ደግሞ በ 21ኛው ጥንድ ላይ የሚገኝ 3ተኛው ትርፍ ክሮሞሶም መሆኑን ያመለክታል።

ይቅርታ አወሳሰብኩት አይደል?

CDC እንደዘገበው በየዓመቱ 6,000 የሚያህሉ ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች ይወለዳሉ፣ ይህም ማለት ከተወለዱት 700 ሕፃናት መካከል አንዱ ህመሙ አለበት።

በህክምናው ለምን ይህ ችግር እንደሚከሰት ሊደረስበት አልተቻለም። ቢሆንም ግን የእናቶች እድሜ መጨመር የዚህ የጤና እክል ያለባቸው ልጆች የመውለድ እድልን እንደሚጨምር ይታወቃል። እናም ይህ ትልቁን ሽፋን ይይዛል።

የዳውን ሲንድረም ምልክቶች

ይህን ለማየት ከፅሁፉ ጋር የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ፡፡

ለዳውን ሲንድረም የሚደረጉ ምርመራዎች

ከወሊድ በፊት በአልትራሳውንድና ለዳውን ሲንደረም መለያ የሚያገለግሉ የደም ናሙናዎችን በማድረግ ፅንሱ ችግሩ እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ ይቻላል።
ከተወለደ በኃላ ብዙውን ጊዜ ምርመራ ሊደረግ የሚቻለው የሕፃኑን አካላዊ ገጽታ በመመልከት ነው።

ሊያስከትለው የሚችለው ተጓዳኝ ችግሮች
የልብ ችግር
የአይንና የመስማት ችግር
የአንጀት ችግር
በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
የእንቅልፍ ችግር
ውፍረት
የአከርካሪ አጥንት ችግር
የመርሳት በሽታ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ህክምናው

ዳውን ሲንድረም በእርግጥ ህክምና የለውም ማለትም ታክሞ ሚድን ነገር አይደለም፡፡ ሆኖም ልጆች ከትንሽነታቸው ጀምሮ በባለሙያ እና በቤተሰብ በደንብ እገዛ ከተደረገላቸው በደንብ የመሻሻል ሁኔታ ይኖራቸዋል። እናም ተጓዳኝ እክሎችን በህክምና ማዳን ይቻላል።

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
295 views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 09:56:11
284 views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 14:57:03 ለሚወዱት የሚያበረክቱት በጭራሽ ሊያመልጦት የማይገባ ልዩ አጋጣሚ!

ሊያና ዲጂታል ሄልዝ ኬር ሶሉሽንስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቴሌህክምና ማዕከል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ አገልግሎቱን ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በተለይም በኮቪድ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታካሚዎች በማገልገል ምስጋናን አትርፏል፡፡

እንደተለመደው ሊያና በአይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም ይዞላችሁ መጥቷል፡፡ በቤትዎ በእድሜው የገፋ ወይም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት መንቀሳቀስ የማይችል የቤተሰብ አባል እንዲሁም ስኳር߹ግፊት߹ኩላሊት߹ጉበት እና የመሳሰሉት ህመሞች ላሉባቸው ሰዎች በወርሀዊ ቋሚ ክፍያ ብቻ የሀኪሞች ክትትል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፕሮግራሙ የሚያካትተው፡-

በ 15 ቀን አንዴ በቤትዎ የሚሰጥ የሀኪሞች አገልግሎት

በወር አንዴ ስፔሻሊስቶችን/ ሰብስፔሻሊስቶችን በርቀት የማማከር አገልግሎት(virtual consultation)

በወር አንዴ አስፈላጊ የላብራቶሪ ምርመራዎችን የማድረግ ዕድል

በማንኛውም ቀን በተመቾት ሰዓት ሀኪሞችን በስልክ የማማከር አገልግሎት

እነዚህን ሁሉ ያካተተ አገልግሎት በወር አንድ ጊዜ ብቻ ክፍያ በመፈፀም ያገኛሉ፡፡

------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ወይም +251910202776 ይደውሉ፡፡

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
309 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 14:56:39
253 views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ