Get Mystery Box with random crypto!

🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ lailaha_ilellah_islamic — 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿 ረ
የቴሌግራም ቻናል አርማ lailaha_ilellah_islamic — 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿
የሰርጥ አድራሻ: @lailaha_ilellah_islamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.39K
የሰርጥ መግለጫ

#ረውደቱል_ኢስላም_የቁርአን_እና_የተርቢያ_ማዕከል ሲሆን በደሴ በአሁን ሰአት ትውልዱን በዲን በማነፅ ላይ ይገኛል። ይሁንና ተደራሽነቱን ለማስፋት በሶሻል ሚዲያው ብቅ በማለት ኡማውን ማገልገል ይፈልጋል።
#አላማችን
● በማዕከሉ የሚሰጡ ትምህርቶች እንዲሁም ተሰምተው ታይተው የማይታወቁ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በዩቲዩብ በማዘጋጀት ለሙስሊሙ ኡማ ማድረስ https://youtube.com/@farzanmedia

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-14 20:30:09 እስኪ ፈገግ በሉልን

#ፈገግታ_ሱናም_አይደል?

#ሶስት(3) ወጣቶች አንዲትን ልጅ ለትዳር የፈልጉና አባታን በየተራ መጠይቅ ይጀምራሉ፦

አባትየው የመስጂድ ኢማም ነበሩና ለምርጫ እንዲረዳቸውአላቸው አንድ ዘዴ ለመጥቀም አሰቡ

#አንደኛውን ልጅ ስምህ ማን ይባላል ብልው ጠየቁት?

#ኢብራሂም እባላልው በል ሱረቱል ኢብራሂምን ቅራ አሉት ልጁም በሚያምር ድምፅ ቀራላቸው

#ሁለተኛውንም ስሙን ጠየቁት ዩሱፍ እባላለው ሲላቸው በል ሱረቱል ዩሱፍን ቅራ አሉት ልጁም አሳምሮ ቀራላቸው

#ሶስተኛውንም ስሙን ጠይቁት ልጁም ፊቱ በላብ ተጥልቅልቆ ያሲን እባላለው

ነገር ግን ጋደኞቼ ሰፈር ሲያቆላምጡኝ #ቁልሁወላሁአሃድ ፣እያሉ ነው ሚጠሩኝ

ብሎ አረፈው ይባላል

#ሌሎችንም_አድ_በማድረግ_ይሄንን_ምርጥ_ግሩፕ_እንዲቀላቅሉ_ያድርጉ።


https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP

ለተለያዩ ትምህርቶች ይሄንን በመንካት ማግኜት ይችላሉ።

@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC


የላኢላሃ ኢለሏህ አማኞች
TELEGRAM CHANNAL
509 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:15:22 ትምህርቱ በጣም አስፈላጊ እና አሰገራሚ ስለሆነ እስከ መጨረሻው ያንብቡት

#_የውመል_ቂያማ

ክፍል ➊ (አንድ)
<=======> <=======>

ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ የሙታንን መንደር ተቀላቅሎ አለም በሚያስፈራ ሁኔታ በጭርታ ተውጣለች።

ፍጥረተ አለሙ ባዶ ሁኗል...።መላዕክት....፣
ሰዎች...፣ጂኖች...፣እንስሳዎች...ሁሉም ሙተው አላህ ብቻውን ቀርቷል።

ያ ቀን የአላህ ቁጣው እጅጉን አይሏል...።ያ ቀን
ለተፀፃቾች በሩ የሚዘጋበት ቀን ነው...።ያ ቀን ሚስጥሮች ሁሉ ይፋ የሚወጡበት ቀን ነው...።

አዎ!!! ያ ቀን መላዕክት በፍርሃት የሚንበረከኩበት ቀን ነው....ያ ቀን የውመል ቂያማ ነው።

ፍጥረተ አለም በደረቅ ጭርታ ተውጦ ሳለ አላህ ኢስራፊል የተባለውን መልዓክ በመቀስቀስ የመሰብሰብያ ጡሩንባውን እንዲነፋ ያዘዋል።

መልዓኩም ለትዕዛዙ እጅ በመንሳት ለእለቱ የተዘጋጀውን ጡሩንባ በከፍተኛ የድምፅ ሀይል ሲነፋ ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ ከሙታን መንደር መትመም ይጀምራሉ።

ሰዎች...፣ጂኖች...፣መላዕክት...እንስሳት እና ሌሎችም ፍጥረታት የጡሩንባውን ድምፅ ሲሰሙ ሁሉም በያሉበት ይባንናሉ።

የሰው ልጆችም በዚህ አስፈሪ ድምፅ በመበርገግ ከአደም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ትውልድ ያለው ሁሉ ከሰውነቱ አፈር እያራገፈ ከቀብሩ መነሳት ይጀምራል።

ሁሉም እርቃኑን ነው...። ጫማ የለም...፣ልብስ
የለም...፣ሁሉም አልተገረዘም ልክ እንደተወለደ ሆኖ ከቀብሩ እየወጣ መሰብሰብ ይጀምራል።

ትዕይንቱ እጅጉን ያስፈራል...፣ሰዎች በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው...፣ሁሉም ደንግጧል...፣ለዘላለም ከተጋደመበት ለምን እንደተቀሰቀሰ አያውቅም...፣ድንጋጤው ይሄን ለማስተንተን ፋታ አይሰጥም።

ሁኔታው ለሁም ያስደነግጣል...፣ማንም ስለማንም ማሰብም ሆነ መጨነቅ አይፈልግም ሁሉም እራሱን ማዳን ነው ሚፈልገው...።

በዚህ ሁኔታ ሁሉም ፍጥረታት ከሞታቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ወደ አረዱል መህሸር (የመሰብሰቢያይቱ ምድር) ሁሉም ይተማል።

ያች ምድር እኛ ምናውቃት ምድር አይደለችም። ያች ምድር ለሂሳብ ብቻ የተፈጠረች ምድር ናት...።

ምንም አይነት ወንጀል በላይዋ አልተፈፀመባትም...፣ዚና አልተሰራባትም...፣ደም አልፈሰሰባትም...በቃ ንፁህ ምድር
ናት።

ፍጥረታት ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እና ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ሳያውቁ ብቻ ወደዚያች ምድር በጅምላ ይነዳሉ...።

ከፊሉ ሰው እየጋለበ ወደዚያች ምድር ያቀናል። ሌላው በፍጥነት እየተራመደ ይሄዳል...፣ የተቀሩትም በፊቶቻቸው እየተንከባለሉ በግዳቸው ይሄዷታል። ብቻ ሁሉም እንደየስራው ጥራት የአካሄዱም ሁኔታ ይለያያል።

ያን ቀን ማንም ማንንም ሊያናግር አይችልም...፤ብቻ ሁሉም ከራሱ ጋር ያወራል <ይህች ምድር እኛ ምናውቃት ናት ወይስ ሌላ ናት...!!! አይ እሷ እንኳን አይደለችም።

እሷ ብትሆንማ የታሉ ወንዞቿ...?! የታሉ ጋራ ሸንተረሯ...?! የታሉ ሸለቆዎቿ...?!> በማለት እያሰላሰሉ ወደ መሰብሰብያው ያቀናሉ።

ሁሉም በማያውቋት ምድር ላይ ሁነው ዙሪያቸውን በመመልከት በፍራቻ እና በግርምት መሃል ሲዋልሉ ድንገት ከወደ ላይ በኩል በሚያስፈራ ሁኔታ ሰማዩ ይሰነጠቃል።

ሁሉም ድንብርብሩ ይወጣል...፣የሰማዩ መሰንጠቅ ያስከተለው ከፍተኛ እና እስፈሪ ድምፅ ሁሉንም ወደ ላይ ቀና ብለው እንዲመለከቱ ያስገድዳቸዋል።

አሁን የሁሉም አይን ተሰንጣቂው ሰማይ ላይ ፈጧል...፤ ሰማዩ እየተሰነጣጠቀ መላዕክቱን እየተሸከመ ይወርዳል...።

ይህ ሁኔታ ለሰው ልጆች ጉልበት አብረክራኪ ፍርሃትን ይፈጥርባቸዋል።በዚህም በመደናገጥ ሰዎች ለመላዕክት፦"እናንተ መሃል ጌታችን አለ እንዴ..!?" በማለት ይጠይቃሉ።

መላዕክቱም በመንቀጥቀጥ፦"ጌታችን ጥራት
ይገባው...!!! እኛ መሃል የለም። ነገር ግን ይመጣል" ይላሉ።

<=======> <=======>
Share ይደረግ

@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ግሩፕ ላይ አስተያየት ለመስጠት
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP
510 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 14:00:07 ፍትህ ከመስፈኑ የተነሳ ተኩላዎች ፍየሎችን መብላት ያቆሙበት ዘመን ይሉታል የታሪክ ሊቃውንታት። ዘራፊና ቀማኛ የጠፋበት ደጃፎች ተከፍተው የሚታደሩበት ይሉታል ሙጨሪኾች። አዎ በእርግጥም ነፍሱን ለአላህ ባሳደረ ፍፁም ፍትሀዊ መሪ አለም ትተዳደር ነበርና ነው። ሚስቱ የቀድሞው ኸሊፋ የዐብደላህ ኢብኑ መርዋን ልጅ ነበረች። አባቷ በተለያዩ ውድ ጌጣጌጦች አስውቧት። በወርቅ በተለበጡ ሸዋሊያዎች፣ በሚያብረቀርቁ የንገት ጌጣጌጦች፣ ውበትን በሚያጎናፅፉ የእግር አልቦዎች ተሽቀርቅራ አምራለች። ታዲያ እኚህ ሰው መንበረ ስልጣኑን ከአባቷ ሲረከቡ ለአስቸኳይ ጉዳይ እንደሚፈልጓት ነግረው ወደ ክፍላቸው አቀኑ። እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ጀመሩ:-

"አባትሽ በስልጣን ዘመናቸው የሰጡሽ ጌጣጌጦች የበዙ ናቸው። ይህ ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት የወጣ ንብረት ነውና እንድትመልሺ እጠይቅሻለሁ። ካልሆነ ግን የሙስሊሞችን ሐቅ ይዘሽ አብረን መኖር አንችልም። ጌጥሽን ወይም እኔን ምረጪ" አሏት።

አንገቷን ወደመሬት አቀርቅራ ንግግራቸውን ስታዳምጥ የነበረችው ፋጡማ
"አንተ የወደድከውን ጀነት እኔ የምጠላ ይመስልሀልን አኼራንና ድህነትን መርጬ ካንተ ጋር እኖራለሁ" አለች እጇን ወደ ጌጧ መክፈቻ እያስጠጋች። አውርታም አልቀረች ጌጧን ሁሉ አውልቃ አስረከበች። ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የነበረውን ውብ መኖርያ ቤታቸው ሳይቀር ወደ ሙስሊሞች ግምጃ ቤት አስገቡት። ግና ማረፊያ ይሆናቸው ዘንድ አንገት ማስገቢያ ቤታቸውን ሲቀይሩ ኻዲም ስላልነበራቸው ባለቤታቸው ፋጡማ ጭቃ ታቦካለች እሳቸው ተቀብለው ይለጥፋሉ። እኚያ ሰው ዑመር ኢብኑ ዐብዱል አዚዝ ይሰኛሉ። እንዲህ አይነት ፍትህ ነው ተኩላ ፍየልን እንዳይበላ ያደረገው።

[ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!!]
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

[ሀሳብ ለመቀያየር በግሩፓችን]
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP
452 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 08:38:06
የጁሙዓ ቀን ሱናዎች

➧ ገላን መታጠብ
➧ሲዋክ መጠቀም
➧ጥሩ ልብስ መልበስ
➧ሱረቱል ከህፍን መቅራት
➧ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
➧ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
➧በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
➧በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
➧ ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መጠባበቅ
519 views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 21:03:11 እኔ እኮ ግርም ሚሉኝ

#እስልምና የመጣው ከአረብ ነው፣የአረብ ባህል እና እምነት ነው ሙስሊሞች ምትከተሉት እያሉ ያፌዛሉ ብዙ አላዋቂ ክርስቲያኖች።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
ቆይ እኔ ምለው ክርስትና የመጣው ከየት ነው?

ሃገር በቀል ሃይማኖት ነውን?

አትሳሳቱ ክርስትና የመጣው ከመካከለኛው ምስራቅ #ከእስራኤል ሃገር ነው።

የጁዊሽ(የአይሁድ) ባህል እና እምነት ነው ክርስትና ።

ለኢትዮጵያውያን ምናቸውም አይደለም ክርስትና ።

☞ አምላክ ነው ምትሉት ኢየሱስ እንኳ አይሁዳዊ(እስራኤላዊ) ነው።

☞ የጌታ(ኢየሱስ) እናት ናት ምትሉዋት ማሪያም አይሁዳዊት(እስራኤላዊ) እንደሆነች
አታውቁምን?

☞የእስራኤል ነብይ ነው ምትሉት ሙሴ እንኳ የፃፋቸው እና እናንተ እንደ ምንጭነት
ምትጠቀሟቸው 5ቱ የኦሪት ህጎች(ብሉይ ኪዳን) የእስራኤላውያን ናቸውን? ወይስ
የአይሁዳያውያን?

☞እስከዛሬ የተላኩ #ነቢያት በሙሉ እስራኤላዊ ናቸው ትሉን የለ? ወይስ ኢትዮጵያውያንም ነቢያት አሉት።

☞እሺ ታቦት ማውጣት ማግባት የማን ህግ ነው? የኢትዮጵያውያን? ወይስ የአይሁዳውያን(የሙሴ)?

☞ሌላውን ተውትና አዲስ ክዳን (አሁን ምትመሩበት) የነ ጳውሎስ መፅሃፍ የማን ቃል
(መፅሃፍ) ነው? የኢትዮጵያውያን? ወይስ የአይሁዳውያን?

ለምንድነው ይህን ሁሉ ጉድ ተሸክማቹ እስልምና የአረብ ባህል እና እምነት ነው ምትከተሉት እኛ ክርስትያኖች ግን የራሳችንን ሃይማኖት ነው ምንከተለው ስትሉ ወላሂ
ለናንተ እኔ አፈርኩ።

ታሪክን አታውቁም እንጂ እስልምናም ክርስትናም ፣ጴንጤም፣ቆስጤም፣ካቶሊክም
ወዘተ የመጡት(የገቡት) ከ4ኛው ክፍለ ዘመን ከመካከለኛው ምስራቅ
( እስራኤል፣ፍሊስጤም፣ቤተልሄም) እንደሆነ እንኳ ስታውቁ ነው ክርስትና ሃገር በቀል
ሃይማኖት እስልምና ግን ከውጭ የመጣ ሃይማኖት ነው ብላቹ በሙሉ አፍ ምታወሩት።

እውነታው ግን ክርስትና በ4ኛው ክ/ዘመን በ 1 ግብፃዊ ነጋዴ ነው የገባው።

እስልምና ወደ ኢትዮጵያ ደግሞ በ7ኛው ክ/ዘመን እንደገባ ታሪክ ያስረዳናል ።

የሃይማኖቱ ቀድሞ መግባት አውነት አያሰኝም ዘግይቶ መግባቱ ደግሞ ውሸት አያስብልም።

ዋናው ውስጡ አስተምህሮቱ ምንድነው የሚለው ነው።
ስለዚህ እናንተ(ክርስትያኖች)

☞ምትጶሙት፣

☞ምታመልኩት፣

☞ፅላት፣

☞ታቦት፣

☞ሃይማኖታዊ አለባበሶች፣

☞ መፅሃፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን)

☞አዲስ ኪዳን፣

☞ሃይማኖታዊ እሳቤዎች፣ ወዘተ ..... በሙሉ የኢትዮጵያውያን ባህል እና እምነት
ሳይሆን የኢስራኤላውያን(የአይሁዶች) ባህል እና እምነት እየተከተላቹ እንደሆነ ልታውቁ
ይገባል።

ታድያ እናንተ እስልምና የአረብ ባህል እና እምነት ነው ለማለት ሞራሉን ከየት አገኛቹ?

እናቶች ሲተርቱ አንድ ቁጥር ላይ ቆማ 2ን ታማለች አሉ።
አላህ ሂዳያ ይስጣቹ።

ቀጥተኛውንም መንገድ ይምራቹ።

ለበለጠ ትምህርት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
268 views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 21:29:23 ውሐን ቁጭ ብሎ መጠጣት የሚያስገኜው ጤናዊ ፋይዳ

ውሐ ስንጠጣ ቆመን ከምንጠጣ ይልቅ ቁጭ ብለን ብንጠጣ የሚከተለውን ጥቅም እናገኛለን፡፡

❖ውሐን #ቁጭ ብለን ብንጠጣ ጥምን ይቆርጣል፤ ምክንያቱም ቆመን ስንጠጣ ውሀው በፍጥነት ነው የሚጓዘው ስለዚ የደረቀውን የምግብ ቱቦ ላያርሰው ይችላል፡፡

ቆመን በምንጠጣበት ጊዜ ከላይ ተንደርድሮ የሚመጣው ውሀ በሆዳችን ግርግዳ እና በዙሪያው ባሉ አካሎች በረጅም ጊዜ ልምድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤

#ልብ በሉ ትንሽ የውሀ ጠብታ እንኳን ከጊዜ ብዛት ድንጋይ ትሰብራለች ብዛት ያለው ውሀ ደግሞ በፍጥነት ሲንደረደር ተርባይን ያሽከረክራል ቁጭ ስንልና ስንቆም የሆዳችን ፖዚሽን ይለያያል ይህም ቆመን ስንጠጣ ከላይ የመጣው ውሀ ሆድ ውስጥ ሳይቆይ በቀጥታ ወደትንሹ አንጀት የመጀመሪያው ክፍል #Duodenum ይገባል ቁጭ ብለን ስንጠጣ ደግሞ ውሀው ሆድ ውስጥ የመቀመጥ እድል ይኖረዋል በዚህም ሆድ ውስጥ በሚገኙ አሲዶች ይጣራል ይህም ለኩላሊት ጤንነት ጠቃሚ ነው ቆሞ መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያለውን የፈሳሽ ባላንስ ያዛባል ይህም በረጅም ጊዜ #Arthritis ለተባለ የመገጣጠሚያ ህመም ያጋልጣል። የመሳሰሉት.....

ወሰላሙ አለይኩም
575 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 22:18:31
‹‹ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡
«ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡ኢስራ 17፡23-24


https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
740 views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 13:23:44 እኔ እኮ ግርም ሚሉኝ

#እስልምና የመጣው ከአረብ ነው፣የአረብ ባህል እና እምነት ነው ሙስሊሞች ምትከተሉት እያሉ ያፌዛሉ ብዙ አላዋቂ ክርስቲያኖች።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
ቆይ እኔ ምለው ክርስትና የመጣው ከየት ነው?

ሃገር በቀል ሃይማኖት ነውን?

አትሳሳቱ ክርስትና የመጣው ከመካከለኛው ምስራቅ #ከእስራኤል ሃገር ነው።

የጁዊሽ(የአይሁድ) ባህል እና እምነት ነው ክርስትና ።

ለኢትዮጵያውያን ምናቸውም አይደለም ክርስትና ።

☞ አምላክ ነው ምትሉት ኢየሱስ እንኳ አይሁዳዊ(እስራኤላዊ) ነው።

☞ የጌታ(ኢየሱስ) እናት ናት ምትሉዋት ማሪያም አይሁዳዊት(እስራኤላዊ) እንደሆነች
አታውቁምን?

☞የእስራኤል ነብይ ነው ምትሉት ሙሴ እንኳ የፃፋቸው እና እናንተ እንደ ምንጭነት
ምትጠቀሟቸው 5ቱ የኦሪት ህጎች(ብሉይ ኪዳን) የእስራኤላውያን ናቸውን? ወይስ
የአይሁዳያውያን?

☞እስከዛሬ የተላኩ #ነቢያት በሙሉ እስራኤላዊ ናቸው ትሉን የለ? ወይስ ኢትዮጵያውያንም ነቢያት አሉት።

☞እሺ ታቦት ማውጣት ማግባት የማን ህግ ነው? የኢትዮጵያውያን? ወይስ የአይሁዳውያን(የሙሴ)?

☞ሌላውን ተውትና አዲስ ክዳን (አሁን ምትመሩበት) የነ ጳውሎስ መፅሃፍ የማን ቃል
(መፅሃፍ) ነው? የኢትዮጵያውያን? ወይስ የአይሁዳውያን?

ለምንድነው ይህን ሁሉ ጉድ ተሸክማቹ እስልምና የአረብ ባህል እና እምነት ነው ምትከተሉት እኛ ክርስትያኖች ግን የራሳችንን ሃይማኖት ነው ምንከተለው ስትሉ ወላሂ
ለናንተ እኔ አፈርኩ።

ታሪክን አታውቁም እንጂ እስልምናም ክርስትናም ፣ጴንጤም፣ቆስጤም፣ካቶሊክም
ወዘተ የመጡት(የገቡት) ከ4ኛው ክፍለ ዘመን ከመካከለኛው ምስራቅ
( እስራኤል፣ፍሊስጤም፣ቤተልሄም) እንደሆነ እንኳ ስታውቁ ነው ክርስትና ሃገር በቀል
ሃይማኖት እስልምና ግን ከውጭ የመጣ ሃይማኖት ነው ብላቹ በሙሉ አፍ ምታወሩት።

እውነታው ግን ክርስትና በ4ኛው ክ/ዘመን በ 1 ግብፃዊ ነጋዴ ነው የገባው።

እስልምና ወደ ኢትዮጵያ ደግሞ በ7ኛው ክ/ዘመን እንደገባ ታሪክ ያስረዳናል ።

የሃይማኖቱ ቀድሞ መግባት አውነት አያሰኝም ዘግይቶ መግባቱ ደግሞ ውሸት አያስብልም።

ዋናው ውስጡ አስተምህሮቱ ምንድነው የሚለው ነው።
ስለዚህ እናንተ(ክርስትያኖች)

☞ምትጶሙት፣

☞ምታመልኩት፣

☞ፅላት፣

☞ታቦት፣

☞ሃይማኖታዊ አለባበሶች፣

☞ መፅሃፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን)

☞አዲስ ኪዳን፣

☞ሃይማኖታዊ እሳቤዎች፣ ወዘተ ..... በሙሉ የኢትዮጵያውያን ባህል እና እምነት
ሳይሆን የኢስራኤላውያን(የአይሁዶች) ባህል እና እምነት እየተከተላቹ እንደሆነ ልታውቁ
ይገባል።

ታድያ እናንተ እስልምና የአረብ ባህል እና እምነት ነው ለማለት ሞራሉን ከየት አገኛቹ?

እናቶች ሲተርቱ አንድ ቁጥር ላይ ቆማ 2ን ታማለች አሉ።
አላህ ሂዳያ ይስጣቹ።

ቀጥተኛውንም መንገድ ይምራቹ።

ለበለጠ ትምህርት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
726 viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 22:04:34 ታላቁ ሀዲስ ዘጋቢ ኢማሙ አል ቡኻሪ ሙሉ ስማቸው ማን ነው ?

መልሱ B) ሙሀመድ ቢን ኢስማዒል ቢን ኢብራሂም አል -ሙጊራ አል ቡኻሪ ።

ኢማም ቡኻሪ ማናቸዉ?

ኢማሙ ቡኻሪ የተወለዱት በ 13 ሸዋል ፥ 194 ዓ.ሂ . ነበር። በቡኻራ ወረዳ በኹራሳን ግዛት (ምዕራብ ቱርኪስታን ) ሙሉ ስማቸው ሙሐመድ ኢብን ኢስማኢል ኢብን አል -ሙጊራ አል ቡኻሪ ነው ።

አባታቸው የሞተው ገና ልጅ ሳሉ ነው ። በእናታቸው ቅርብ ክትትል ነበር ያደጉት የሐዲስ ትምህርታቸውን የጀመሩት በአስር አመታቸው ነው። ከእናታቸውና ከታላቅ ወንድማቸው ጋር በመሆን ወደ መካ በአስራ ስድስት ዓመታቸው ተጓዙ ። ኢማም ቡኻሪ መካና ኡለማዎቿን እጅግ በጣም በመውደዳቸው እናታቸውንና ወንድማቸውን በመሰናበት በቅድስቷ ከተማ ለሁለት አመታት ተቀመጡ ። ከዚያም ወደ መዲና በመሄድ ለአራት ዓመታት ሐዲስ በመቅሰም ኖሩ ።ከዚያም ወደ በስራ ፥ኩፍ ፥ባግዳድ ግብፅና ሶሪያ በመዘዋወር ከተለያዩ ሙሁራን ጋር ለመማርና ለመተዋወቅ በቅተዋል። ባግዳድ ለበርካታ ጊዜ ጎብኝተዋል ከእውቅ ሙሁራን መካከል ኢማም አህመድ ኢብን ሐንበልን አግኝተዋል ።

ኢማም ቡኻሪ እጅግ በጣም ታማኝና ቅን ሰው የነበሩ በመሆናቸው ልዑላኖችን ፣መሳፍንቶችንና ንጉሶችን ላለመገናኘትና ላለመወዳጀት ብርቱ ጥረት ያደርጉ ነበር ። እነርሱን ለማስደሰት ሲሉ አንዳች ነገር መናገር የሚሹ አልነበሩም -ቡኻሪ።

ኢማም ቡኻሪ ሐዲስ ለመሰብሰብ ያደረጉትን ብርቱ ጥረት በተመለከተ በርካታ ገጠመኞች ተወስተዋል ። ከታላቁ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንደበት የፈለቁ ትምህርቶችን በማሰባሰብ ያረገጡት ቦታ ፥ ያላወያዩት ዓሊም እጅግ ጥቂት ነበር ። ታላቁ ኢማም ቡኻሪ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አቻ የማይገኝለት የማስታወስ ችሎታ የነበራቸው ሊቅ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከሩ የኢስላም ባለ ውለታ "ዓሊም"ናቸው ። 300,000 ሐዲስ ሰብስበዋል ። ከዚህ ውስጥ 200,000 ያህሉን በአዕምሮአቸው ሸምድደዋል። ኢማም ቡኻሪ የተወለዱበት ዘመን የሐዲስ ትምህርትን በማዛነፍ ፍትህ የሚጎድላቸውን መሪዎች ለማስደሰት ወይም የኢስላምን ዲን ለማግሸብና ለማጭበርበር ከፍተኛ ጥረት የተደረገበት ነበር ።

የኢስላም ምሁራን የኢማም ቡኻሪን የሀዲስ ስብስብ፦ "ከአላህ መፅሀፍ(ቁርአን) በመቀጠል እጅግ በጣም አስተማማኙ መፅሀፍ በኢማም ቡኻሪ የተፃፈዉ "ሶሂህ አል-ቡኻሪይ" ነዉ" በማለት ገልፀዋል።

ኢማም ቡኻሪ "ሶሂህ አል-ቡኻሪ"ን ከማዘጋጀታቸው በፊት በሕልማቸው ያዩት ለጥረታቸው ልዩ እገዛ ማድረጉም ይነገራል ። " ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፊት ለፊት ቆመውና በእጃቸው ማራገቢያ ቢጤ ይዘው ከታላቁ ነብይ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፊት ላይ ዝንብ እንዳያርፍ ይከላከላሉ ።" ኢማም ቡኻሪ ይህን ሕልም በዘርፍ ዕውቀት ላላቸው ሰዎች ይገልጻሉ በነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስም የሚነገሩ ግን ከሳቸው አንደበት ያልፈለቁ ጥቅሶችን የማጥፋት ሚና ገልጹላቸው።

በመሆኑም ኢማም ቡኻሪ የፈጠራ ሐዲሶችን ከእውነተኛና ትክክለኛ ሐዲሶች የማበጠሩን ሥራ ተያያዙት ። ምንም እንኳ ማንኛውም ታሪክ ከሚዘገብበት መስፈርት አኳያ ኢማሙ የሰበሰቧቸው ሐዲሶች ውስጥ ውድቅ የሚደረጉበት ምክንያት ባይኖርም የኢማሙ ቡኻሪ የሐዲስ አሰባሰብ መስፈርት (ሸርጥ) ጥብቅ በሆኑ 7275 (ሰባት ሽ ሁለት መቶ ሰባ አምስት) የሚደርሱ ሐዲሶችን ብቻ ነው በ "ሶሒሕ ቡኻሪ"እንዲካተቱ ያደረጉት ። ከነኝህ ሐዲሶች መካከል የተደጋገሙትን ስንቀንስ 2230 ብቻ ሐዲሶችን እናገኛለን ። እዚህ ላይ አንባቢያን ልብ እንዲልልን የምንሻው ሐዲስ የሚቆጠረው በ "መትን" (ፍሬ የቃሉ) ሳይሆን በሰነዱ መሆኑን ነው። በመሆኑም አንድ ሐዲስ እስከ አራት መቶ ሠነድ ( የተዘገበበት መስመር ) ሊኖረው መቻሉን ልናስታውስ እንሻለን ።

ታላቁ የሐዲስ ሊቅ አንድን ሐዲስ በስብስባቸው ውስጥ ከመጻፋቸው በፊት ውዱእ የደርጋሉ ። ሁለት ረከዓ ይሰግዳሉ ። ጌታቸውንም ይለምናሉ ። በርካታ እውቅ ሙስሊም ዓሊሞች "ሶሕሒህ ቡኻሪ " ን መርምረዋል ግን አንድም እንከን ሊያገኙበት አልቻሉም። ለዚህም ነው በአንድ ድምፅ ከቁርአን በመቀጠል እጅግ በጣም ትክክለኛው መጽሐፍ "ሶሒሕ ቡኻሪ "ነው በማለት የገለጹት ።

ኢማም ቡኻሪ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ256 ዓ.ሂጅራ ነው ። በሰመር ቀንድ አቅራቢያ የምትገኝ ኸርታንቅ በተባለች መንደር መካነ መቃብራቸው ይገኛል ።

አላህ ይዘንላቸው ።

ዋናውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
766 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ