Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርቱ በጣም አስፈላጊ እና አሰገራሚ ስለሆነ እስከ መጨረሻው ያንብቡት #_የውመል_ቂያማ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

ትምህርቱ በጣም አስፈላጊ እና አሰገራሚ ስለሆነ እስከ መጨረሻው ያንብቡት

#_የውመል_ቂያማ

ክፍል ➊ (አንድ)
<=======> <=======>

ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ የሙታንን መንደር ተቀላቅሎ አለም በሚያስፈራ ሁኔታ በጭርታ ተውጣለች።

ፍጥረተ አለሙ ባዶ ሁኗል...።መላዕክት....፣
ሰዎች...፣ጂኖች...፣እንስሳዎች...ሁሉም ሙተው አላህ ብቻውን ቀርቷል።

ያ ቀን የአላህ ቁጣው እጅጉን አይሏል...።ያ ቀን
ለተፀፃቾች በሩ የሚዘጋበት ቀን ነው...።ያ ቀን ሚስጥሮች ሁሉ ይፋ የሚወጡበት ቀን ነው...።

አዎ!!! ያ ቀን መላዕክት በፍርሃት የሚንበረከኩበት ቀን ነው....ያ ቀን የውመል ቂያማ ነው።

ፍጥረተ አለም በደረቅ ጭርታ ተውጦ ሳለ አላህ ኢስራፊል የተባለውን መልዓክ በመቀስቀስ የመሰብሰብያ ጡሩንባውን እንዲነፋ ያዘዋል።

መልዓኩም ለትዕዛዙ እጅ በመንሳት ለእለቱ የተዘጋጀውን ጡሩንባ በከፍተኛ የድምፅ ሀይል ሲነፋ ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ ከሙታን መንደር መትመም ይጀምራሉ።

ሰዎች...፣ጂኖች...፣መላዕክት...እንስሳት እና ሌሎችም ፍጥረታት የጡሩንባውን ድምፅ ሲሰሙ ሁሉም በያሉበት ይባንናሉ።

የሰው ልጆችም በዚህ አስፈሪ ድምፅ በመበርገግ ከአደም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ትውልድ ያለው ሁሉ ከሰውነቱ አፈር እያራገፈ ከቀብሩ መነሳት ይጀምራል።

ሁሉም እርቃኑን ነው...። ጫማ የለም...፣ልብስ
የለም...፣ሁሉም አልተገረዘም ልክ እንደተወለደ ሆኖ ከቀብሩ እየወጣ መሰብሰብ ይጀምራል።

ትዕይንቱ እጅጉን ያስፈራል...፣ሰዎች በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው...፣ሁሉም ደንግጧል...፣ለዘላለም ከተጋደመበት ለምን እንደተቀሰቀሰ አያውቅም...፣ድንጋጤው ይሄን ለማስተንተን ፋታ አይሰጥም።

ሁኔታው ለሁም ያስደነግጣል...፣ማንም ስለማንም ማሰብም ሆነ መጨነቅ አይፈልግም ሁሉም እራሱን ማዳን ነው ሚፈልገው...።

በዚህ ሁኔታ ሁሉም ፍጥረታት ከሞታቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ወደ አረዱል መህሸር (የመሰብሰቢያይቱ ምድር) ሁሉም ይተማል።

ያች ምድር እኛ ምናውቃት ምድር አይደለችም። ያች ምድር ለሂሳብ ብቻ የተፈጠረች ምድር ናት...።

ምንም አይነት ወንጀል በላይዋ አልተፈፀመባትም...፣ዚና አልተሰራባትም...፣ደም አልፈሰሰባትም...በቃ ንፁህ ምድር
ናት።

ፍጥረታት ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እና ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ሳያውቁ ብቻ ወደዚያች ምድር በጅምላ ይነዳሉ...።

ከፊሉ ሰው እየጋለበ ወደዚያች ምድር ያቀናል። ሌላው በፍጥነት እየተራመደ ይሄዳል...፣ የተቀሩትም በፊቶቻቸው እየተንከባለሉ በግዳቸው ይሄዷታል። ብቻ ሁሉም እንደየስራው ጥራት የአካሄዱም ሁኔታ ይለያያል።

ያን ቀን ማንም ማንንም ሊያናግር አይችልም...፤ብቻ ሁሉም ከራሱ ጋር ያወራል <ይህች ምድር እኛ ምናውቃት ናት ወይስ ሌላ ናት...!!! አይ እሷ እንኳን አይደለችም።

እሷ ብትሆንማ የታሉ ወንዞቿ...?! የታሉ ጋራ ሸንተረሯ...?! የታሉ ሸለቆዎቿ...?!> በማለት እያሰላሰሉ ወደ መሰብሰብያው ያቀናሉ።

ሁሉም በማያውቋት ምድር ላይ ሁነው ዙሪያቸውን በመመልከት በፍራቻ እና በግርምት መሃል ሲዋልሉ ድንገት ከወደ ላይ በኩል በሚያስፈራ ሁኔታ ሰማዩ ይሰነጠቃል።

ሁሉም ድንብርብሩ ይወጣል...፣የሰማዩ መሰንጠቅ ያስከተለው ከፍተኛ እና እስፈሪ ድምፅ ሁሉንም ወደ ላይ ቀና ብለው እንዲመለከቱ ያስገድዳቸዋል።

አሁን የሁሉም አይን ተሰንጣቂው ሰማይ ላይ ፈጧል...፤ ሰማዩ እየተሰነጣጠቀ መላዕክቱን እየተሸከመ ይወርዳል...።

ይህ ሁኔታ ለሰው ልጆች ጉልበት አብረክራኪ ፍርሃትን ይፈጥርባቸዋል።በዚህም በመደናገጥ ሰዎች ለመላዕክት፦"እናንተ መሃል ጌታችን አለ እንዴ..!?" በማለት ይጠይቃሉ።

መላዕክቱም በመንቀጥቀጥ፦"ጌታችን ጥራት
ይገባው...!!! እኛ መሃል የለም። ነገር ግን ይመጣል" ይላሉ።

<=======> <=======>
Share ይደረግ

@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ግሩፕ ላይ አስተያየት ለመስጠት
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP