Get Mystery Box with random crypto!

كنز من كنوز الجنة

የቴሌግራም ቻናል አርማ kunuzil8jenah — كنز من كنوز الجنة ك
የቴሌግራም ቻናል አርማ kunuzil8jenah — كنز من كنوز الجنة
የሰርጥ አድራሻ: @kunuzil8jenah
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 464
የሰርጥ መግለጫ

★ የቱን ይመርጣሉ!!!★
✔ ቻናላችን በውስጡ ከሚሰጣቸው ትምህርቶች መካከል ፦
✔ ቁርኣን በተለያዩ ቃሪዎች ፣
✔ እውነተኛ ቂሷዎች / ታሪኾች ፣
✔ አጠር አጠር ያሉ ዳዕዋዎች ፣
✔ ት/ት አዘል ቀልዶች ፣
✔ ኢስላማዊ ጥያቄ እና መልሶች ።
✔ ዓላማዬ የአሏህን ቃል የበላይ ማድረግ ነው!
ለአስተያየቶ፦
@Ami_new_bot

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-22 09:15:43
ሱረቱል ካህፍ
በሼኽ አፊፍ ሙሀመድ ታጁ የከሚሴው እንቁ
211 viewsHiክማ, edited  06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:39:23 ፈገግ በሉልኝማ!
.
.
በየቀኑ ሚስቱ በውበቷ የምትኮራበት አንድ አይነ ስውር ነበር።

"ምናለ አይን ኖሮህ የፊቴን ቅላት ባየህ ኖሮ፣ ምነው አንዴ እንኳን ማየት በቻልክና የሰውነቴን ቅርፅ በተመለከትክ! ምናለ..." እያለች ንዝንዝ ስታደርገው ምን ቢላት ጥሩ ነው?

"ባክሽ ዝም በይ! እውነት እንዳልሽው ውበት ቢኖርሽ ኖሮ አይናሞች እንደኔ አይነቱ አይነ ስውር እስከሚያገባሽ ባልተውሽ ነበር!" ብሎ ልኳን ነገራት።

ምን ለማለት ነው። ውበት አስፈላጊ ቢሆንም እራሳችን ጠፍጥፈን ያበጀነው እስከሚመስል ድረስ ልንጎራበት ግን አይገባም። በተለይ ደግሞ የሌሎችን ህልውና ዝቅ በማድረግ ሲሆን።


@kunuzil8jenah
@kunuzil8jenah
303 viewsطلبتل اعلم, 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 13:13:10
317 viewsطلبتل اعلم, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 15:17:42 እኔ ምለው
ወንዶች መነፅር እና ሽጉጥ ገዝታችዋል ነገ ኢድ ስለሆነ ይወደድባቹዋል አሁን ግዙ፡፡
ሴቶችዬ ደግሞ ሸዋልያ፣ ቲያራ ማስቲካ ምናምን ገዝታቹዋል፡፡

ለትዝታው ያክል ነው ፡፡ያጥሩ ዘመን ናፈቀኝ አቦ
346 viewsطلبتل اعلم, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:42:20
305 viewsطلبتل اعلم, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:50:35
በጣም ነው የተመቸኝ ፎቶው ፡፡በጣም ደስ ይላላ ።
አላህ እኛንም ከሚያደርጉት ያድርገን ፡፡አሚን በሉ እንጂ ፡ሆሆሆ

አንዴ እናቴ የነገረችኝ ትዝ አለኝ ፡፡
ቁጭ ብለን የእናቴን የሠርግ Video እያየን የኒካህ ቀን የተቀዳውን እያየን እያለ የሆነ ሰውዬ ናቸው (አላህ ይርሀማቸው) አሳየቺኝ እና እንዲህ አለችኝ ሁሌም ዱአ ሲያደርጉ ያአላህ ሆይ ኻቲማዬን መካላይ ሀጅ አያደረኩ አድርገው ብለው ከልባቸው ዱአ ያደርጉ ነበር እንደተመኙትም አላህ አሳካላቸው፡፡
ሀጅ እያረጉ ነው የሞቱት ፡፡ እንዴት የሚያምር ኻቲማ ነው ኢላሂ፡፡
አስባቹታል ልክ ነገ የውመል ቂያማ ላይ ስትቀሰቀሱ ለበይከ አላሁመ ለበይክ እያላቹ ስትነሱ ኢላሂሂ ኻቲማዬን አሳምርልኝ ፡፡

@kunuzil8jenah
288 viewsطلبتل اعلم, edited  07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:27:24 የኡድሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች
-
ኡድሒያ ማለት በዒደል አድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡድሒያን ያርዱ ነበር፡፡ (ሚሽካት፡ 1475) እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “አቅሙ እያለው ኡድሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡ (ከኡድሒያ ጋር የተያያዙ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች፡-
የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት :-

1. የሚታረደው እንስሳ ከሚከተሉት የእንስሳት አይነቶች ብቻ መሆን አለበት፡- በግ፣ ፍየል፣ ከብትና ግመል፡፡
2. ከነዚህ እንስሳቶች የትኛውን ማረድ ነው የሚበልጠው? በቅደም ተከተል ግመል፣ ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ ግመል በጋራ፣ ከብት በጋራ።
(ፈትዋ ለጅነተ ዳኢማህ) (ኢብኑ ዑሠይሚን፡ አሕካሙል ኡድሒያ ወዘካት)
* ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ለ7 ሰው ነው መሆን አለበት፡፡
* ፍየልና በግ ለጋራ ማራድ አይቻልም፡፡

3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡

4. የሚታረደው እንስሳ እውር፤ በሽተኛ፤ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡

5. የሚታረደው እንስሳ ህጋዊ በሆነ መልኩ የራስ ንብረት መሆን አለበት፡፡ (የተሰረቀ፣ የተነጠቀ፣ የተጭበረበረ ..መሆን የለበትም።)

6. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ባሉት አራት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ይላሉ፡፡ (ቡኻሪ)

7. ያለምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም ከሴትም ለኡድሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ (ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሪን ዐለደርብ፡ ካሴት ቁ. 72)

8. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡድሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ﷺ “የኡድሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡድሒያ የለውም” ብለዋል፡፡ (ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2/1055) ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡድሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክኒያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሰደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ (ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 25/162) ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡

9. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል፤ ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል፣ ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡

10. ኡድሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡
ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡

@kunuzil8jenah
262 viewsطلبتل اعلم, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 14:18:56
242 viewsطلبتل اعلم, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:32:56 ኒቃቢስቷ አላህ ከዋክብቶች የሰማይ ማስዋቢያ አድርጎ ፈጠራቸው። አንቺን ደሞ የምድርን ውበት መጠበቂያና መለኪያ አደረገሽ።

ኒቃቢስቷ የምድር ከዋክብቷ
273 viewsmiqbas(፪) miqbasudin(፪) , 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ