Get Mystery Box with random crypto!

. ውስጤን ሲረብሸው የጊዜው ትኩሳት፣ ከሁለት አቅጣጫ የሚነደው እሳት፣ ልቤ ቢፈልግም የውስጡን ሊ | ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

.
ውስጤን ሲረብሸው የጊዜው ትኩሳት፣
ከሁለት አቅጣጫ የሚነደው እሳት፣
ልቤ ቢፈልግም የውስጡን ሊናገር፣
እጀን ይከብደዋል ያነሳና ብዕር።

በዚች ትንሽ እውቀት በኮልታፋ አንደበት፣
ተገቢ እንዳልሆነ ሌሎችን መተቸት፣
የሐሳብ ጦርነት ውስጤን ሲሞግተው፣
ዝምታ እመርጣለሁ ሁሉንም በመተው።


ዳግም ሲፈትነኝ ሲሟጠጥ ትዕግስቴ፣
በዝምታው መሀል ሲፈርስብኝ ቤቴ፤
በቃ ወስኛለሁ ይታይ ማንነቴ፤
ከእንግዲህስ ይውጣ ይነበብ መልዕክቴ፤
መሆን እስካለበት ሁሉም ይታገሳል፣
ውሃም ሲያስገድዱት ወደላይ ይፈሳል

ⒿⓄⒾⓃ ⓈⒽⒺⓇⓇ

@kumis4274
@kumis4274