Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር መስጠትና መቀበል ላይ የተመሰረተ ዉለታ መመላለሻ አደለም።ላፈቀሩት ሰው ከምንም በላይ እራስን | ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

ፍቅር መስጠትና መቀበል ላይ የተመሰረተ ዉለታ መመላለሻ አደለም።ላፈቀሩት ሰው ከምንም በላይ እራስን አሳልፎ መስጠት ያለበት ከራስ ወዳድነት የፀዳ ከንፁህ ልብ እሚመነጭ ኮለል ያለ ፀበል ነው።

ፍቅር የጎደለን ሟሟያ አደለም ከጥቅም ፈፅሞ የራቀ ነው።

ፍቅር የአላማን መንገድ እየተጓዙ አብሮ መራመድ አደለም።ያፈቀሩት ሰው መንገዱን ሲስት መምራትን ይፈልጋል።በጉዞው ደክሞ ወድቆ ቢገኝ እንኳን አዝሎ መራመድን የሚያፀና ነው።

ፍቅር በደልን ይቅርታ የሚል አደለም እሚረሳ እንጂ።

ፍቅር ማዕበሉን ንፋስ ቢያናውጠውም ፀጥ ማድረጊያው ትእግስት አለው።

ፍቅር ውድ ነው መሬት ወድቆ ከምናየው ሰው ጀምሮ እስከ ይነግሳል እስከምንለው በፍጡራን ሁሉ ውስጥ የተቀመጠ ድንቅ ስጦታ ነው።

ከከበረ ነገር ሁሉ የላቀ የህይወት ማዕዘን ፍቅር ነው።

ፍቅር አይገዛም አይሸጥም በባህሪው ገዢ ነው።

ፍቅር ሰጪ ነው ተቀባይ አደለም ሁሉ አለዋ.. ..ምን ጎሎበት ይቀበላል....ብዙ ብዙ ነው።


ፍቅር ቃላት አይገልፀውም።

በፍቅር ያኑረን አሜን

@kumis4274
@kumis4274
@kumis4274