Get Mystery Box with random crypto!

ሳቄን መልስልኝ ፍቅርን ስንጋራ፤ መውደድን ስንቅም፤ ሀዘንኮ አናውቅም። በሳቅ ተሸፍነን፤ በደስ | ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

ሳቄን መልስልኝ

ፍቅርን ስንጋራ፤
መውደድን ስንቅም፤
ሀዘንኮ አናውቅም።
በሳቅ ተሸፍነን፤
በደስታ ታጅበን፤
ፍቅርን ስናዜማት፤
እንደ ንብ ስንቀስማት፤
በጨረቃ ብርሀን በወፎች ዝማሬ፤
በደስታ ባህር ውስጥ ካንተ ጋር አብሬ፤
ባዜምልህ ፍቅርን ብቀኝልህ ቅኔ፤
አልሰለችም ነበር አንተ ካለህ ጎኔ።
እንዲ ነበርኩ ያኔ
ልቤም በሙሉ እምነት ባንተ ተደግፎ፤
ድንገት ሸርተት ብትል ማገሩ ተዛንፎ፤
ላይነቃ አሸለበ ላይሳሳ አመረረ፤
ላይድን ቆሰለብህ ላይነጣ ጠቆረ፤
እንዲያ እንዳልሆነልህ እንዳላፈቀረ፤
በክህደትህ ዱላ በ'ጅህ ተሰበረ።
ውስጠቴ አዘነብህ ጠላኸው አፍቅረህ፤
ሳቄንም ወሰድከው በለቅሶ ቀይረህ።
እናም ስማኝ ውዴ፤
ላስቸግርህ አንዴ፤
ቀርቶብኛል ፍቅርህ ይቅርብህ መውደዴ፤
ግና ተለመነኝ እሺ በል ወዳጄ፤
ሳቄን መልስልኝ
መኖር እንዲያስችለኝ ከሰው ተላምጄ።



••●◉Join us share◉●••

@kumis4274
@kumis4274