Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት ናችሁ!   የፊታችን እሁድ ነሐሴ 22 ቀን ወደ ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት) በምናደር | ኮረማሽ - Koremash

እንዴት ናችሁ!

  የፊታችን እሁድ ነሐሴ 22 ቀን ወደ ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት) በምናደርገው ቀላል የእግር ጉዞ (Hiking) ፕሮግራም ላይ አብራችሁን የምትጓዙ ቤተሠቦቻችን!

*  በዕለቱ ከእናንተ የምንጠብቃቸው ነገሮች....

*  ከአዲስ አበባ የመነሻ ሠዓታችን ከጠዋቱ 12:30 በመሆኑ ይህንኑ አውቀን ከመነሻ ሰዓታችን ቀደም ብለን ከጣይቱ ሆቴል (ፒያሳ) ላይ እንድንገኝ ይሁን።

*  ለጉዞ የሚሆን በጀርባ የሚታዘል ቦርሳ

*   ወቅቱ የክረምት ወራት እንደ መሆኑ መጠን ዝናብ ሊኖር ስለሚችል የዝናብ መከላከያ አልባሳትን ወይም ዣንጥላ መያዝ እንዲሁም መዳረሻችን እጅግ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ስላለው ቅዝቃዜውን ለመከላከል የሚረዱ ልብሶችና የእጅ ጓንት ስካርፍ ኮፍያ የመሳሰሉትን በቦርሳችን ብንይዝ

*  በተጨማሪም በጉዟችን ላይ እርጥበታማ እና የሚያዳልጥ መንገድ ሊያጋጥመን ስለሚችል ለዚህ አይነት ጉዞ የሚሆንና ሶሉ የሚቆነጥጥ ለእግራችን የሚመቹ ሙቀት  ጫማዎችን እንድናደርግ ይመከራል።

*   ተጓዦቻችን በጉዞ ላይ እያሉ ሊመገቧቸው የሚችሉ ቀለል ያሉ የጉዞ ምግቦችንና መጠጦችን በግላቸው ይዘው መምጣት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ :-  ማርፈድ አይፈቀድም

በተጨማሪም ተጓዦች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዛቸው እንዳይረሳ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን።

በቸር እንገናኝ!

ለመረጃ በ0993949053 መደወል ይችላሉ!