Get Mystery Box with random crypto!

ትንሽ ስለ ገማሳ ገደል ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላ | ኮረማሽ - Koremash

ትንሽ ስለ ገማሳ ገደል



ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ጥድ እና ጅብ ዋሻ የሚባሉ አካባቢዎች የሚያዋስኑት ትልቁ የስምጥ ሸለቆ በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ መስህብ ነው የምኒልክ መስኮት፡፡

ይህ ድንቅ ስፍራ ስያሜውን ያገኘው አጼ ምኒልክ ወደዚህ ስፍራ በተደጋጋሚ እየተገኙ ይጎበኙት ስለነበር እንደኾነ ታሪክ ያስረዳል፡፡

አጼ ምኒልክ መቀመጫቸው አንኮበር በነበረበት ጊዜ ወደ ደብረሲና ዘመድ ለመጠየቅ ሲያልፉ ይጎበኙት እንደነበር እና ጠላትንም ይቆጣጠሩበት የነበረ ወሳኝ ቦታ ነው፡፡

የምኒልክ መስኮት ሥፍራ ላይ ሲገኙ ማራኪ አየር በጉም የተሸፈነ ስፍራ እና ለጎብኝዎች ቀልብን የሚስብ ስፍራ መኾኑን ይገነዘባሉ፡፡

በምኒልክ መስኮት አሻግረው ካዩ እስከ አዋሽ ሰባት ድረስ ያሉ ማንኛውንም ጉዳዮች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ቦታ ነው፡፡

አካባቢው በርካታ ጎብኝዎችም የሚጎበኙት ድንቅ ስፍራም ነው፡፡

አካባቢው ላይ ጭላዳ ዝንጀሮዎች በሰፊ የሚታዩበት፤ አንኮበር ሳይድ የተባለች ልዩ ወፍም የምትገኝበት ነው፡፡

ሥፍራው አምስት ወረዳዎችን ማለትም፦ ጣርማ በርን፣ ቦሰና ወረናን፣ አንኮበርን፣ መንዝ ማማ ምድርን እና መንዝ ጌራን የሚያካልለውን የወፍ ዋሻን በከፊል የያዘ ነው፡፡