Get Mystery Box with random crypto!

ሠላም ቤተሠቦቻችን! ከቀጣዩ የውሎ ገብ የHiking ፕሮግራማችን ጋር ተመልሰናል!   ቀጣይ መዳ | ኮረማሽ - Koremash

ሠላም ቤተሠቦቻችን!

ከቀጣዩ የውሎ ገብ የHiking ፕሮግራማችን ጋር ተመልሰናል!

  ቀጣይ መዳረሻ ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት)

  እሁድ ነሐሴ 22 ቀን 2014 ከአዲስ አበባ በስተሠሜን 160 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት) ጀማሪ ተጓዦችን ያማከለ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ (hiking) ፕሮግራም ተወዳጅ ከሆነው የደብረ ብርሃን የጥሬ ስጋ ቁርጥና ባሕላዊ መጠጦች ጋር አዘጋጅተናል።

የጉዞ አይነት

ቀለል ያለ የእግር ጉዞ

(ጀማሪ ተጓዦች ሊሳተፉበት የሚችል)

  በመሆኑም የተፈጥሮና የእግር መንገድ ወዳጆች በዚህ ጉዞ ላይ አብራችሁን እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።


ጉዞው ውስን ሰዎችን የሚያሳትፍ ብቻ በመሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት ቀድመው እንዲመዘገቡ እንመክራለን ።

የጉዞ ዋጋ

  ከፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ገማሳ ገደል የደርሶ መልስ ትራንስፖርት ቀለል ያለ ቁርስ ምሳ (የቁርጥ ስጋ እና ባሕላዊ መጠጦች) የታሸገ ውሃ እንዲሁም የአስጎብኚ ክፍያን ጨምሮ:

ብር 1650

ለበለጠ መረጃ 0993949053 ይደውሉ!