Get Mystery Box with random crypto!

​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ ክፍል አርባ አንድ (41) . . . አስቡ ይሄም ከአመታት | ETHIO BOOKS PDF

​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል አርባ አንድ (41)
.
.
.
አስቡ ይሄም ከአመታት በፊት ያለ ታሪክ ነው።
ህይወት የአንድ ወቅት ብርሀን የአንድ ወቅት ጨለማ እና መከራ ነው ። ሚካኤሌ
ከደረሰበት አደጋ ከሞት ተርፏል በሰውነቱ ላይ ተሰካክተው የነበሩት የመኪናው
የፊት መስታወት ስብርባሪ እዚሁ ባለ ህክምና ተነቃቅለው ወጥተዋል በአይኖቹ
ላይ የተሰኩት ግን መስታወቱ ቢወጡም አይኑ ማየት አልቻለም ።
አድማሱና ሰላም ሚካኤሌ ሆ/ል እያለ አብረው አድረው ጠዋት ቁርስ ስጦታም
አብራ ተቀምጣ እየበሉ ሳለ።
" ቆይ እኔ የምልህ አድማሱ " አለች ስጦታ የሁለቱን ሁኔታ ካየች በኋላ ምንም
የሚጥም ነገር በለማየቷ ።
" እሺ ስጦትዬ የኔ ቆንጆ ምን ነበር ? " አላት ፈገግ ብሎ እየተመለከታት ።
" ለምንድን ነው እዚህ ቤት ያደረከው " አለችው በጥላቻ እያየቺው ። ሁለቱም
በግርምት ተመለከቷት ።
" ምን ማለት ነው የኔ ልጅ " አለች ሰላም በመሀል በመግባት።
" እንደዚህማ አትበይ እማዬ አባቴ እቤት በሌለበት ወንድ ልጅ እንዴት ያድራል "
አለች ።
" አንቺ ልጅ እንደ ልጅ ሁኚ እንጂ ምንድን ነው እንዲህ አደኩ አደኩ የምትይው
........ እዩኝ እዩኝ የምትይው " አለች ሰላም
" ይሄ የአባቴ እና የቤተሰቤ ጉዳይ እኮ ነው " አለች ስጦት
" የኔ ልጅ እኔ እኮ የአጎቷ ልጅ እኮ ነኝ " አለ አድማሱ
" ማን ያውቃል ..... ቢሆንስ ደግሞ አባወራ በሌለበት ቤት ማንም ሁን ማደርህን
እኔ አልፈልግም " ስትል ሰላም ከተቀመጠችበት በንዴት ተነስታ ስጦታን በጥፊ
ጉንጯን አቀላቻትና በንዴት በዛቻ።
" አንቺ እርኩስ መናጢ ልጅ ...... ሂጂ ውጪና ቁርስሽን እቤትሽ ሄደሽ ብዪ
በጠዋቱ ቀኔን አትበጭብጪ .... እንደውም እዛው አዳሪ ት/ቤትሽ ወስጄ
እወረውርሻለው እሺ ያኔ ዋጋሽን ታገኚያለሽ አሁን ሂጂ ወደ እዛ " አለቻት በጥላቻ
እና በመጠየፍ ስጦታ የተመቻውን ጉንጯን እያሻሸች እና እያለቀሰች ወደ ክፍሏ
የሚወስደውን መንገድ በፍጥነት እየተራመደች ሄደች።
" ለምንድን ነው እንደዚህ መጥፎ የምትሆኚባት " አላት
" ምን አገባህ አንተ ባክህ ዝም በል .... እኔ የእሱ አለመሞት ጭራሽ አናዶኛል
አንተ እዚህ እንደገና ታናደኛለህ " አለች በቁጣ አድማሱ በግርምት አያትና።
" ታዲያ ምን ያናድድሻል " አላት
" አትሰማም እንዴ የምልህን አልሞተም እኮ ነው እያልኩሁ ያለሁት ታሾፋለህ "
አለችው
" ይሀውልሽ የኔ ቆንጆ አይሙት ጥሩ አማራጭ ነው እንደውም ተረጋጊና ቁጭ
ብለሽ ልነግርሽ እሺ " አላት
" ሌላ አማራጭ አለህ ደስ ሲል እሺ ንገረኝ " አለች በጉጉት
" ሳስበው መሞቱ ትርጉም የለውም ነበር ለአንቺም ውጣ ወረድ ነበር የሚኖረው
ስለዚህ አይኑ ጠፍቶ በህይወት መኖሩ ላይ እኛ ዳማ እንጫወትበታለን " አላት
" እንዴት እንደሆነ ንገረኝ ሌላውን ወሬ ተወውና " አለች
" ይሀውልሽ .........." አላት እና ሁሉንም ነገር ዝርዝር አድርጎ ነገራት ሰላም አፏን
ከፍታ ነበር ትሰማው የነበረው ልክ እንደጨረሰ ዘላ አቀፈችውና ደጋግማ ስማው

" ለዚህ ምርጥ ሀሳብህ እና እቅድህ ጥሩ አሰጣጥ ያስፈልገሀል ምርጥ ስጦታዬ
ይሆናል የኔ ቆንጆ " አለችውና ይዛው ወደ መኝታ ክፍል እየገባች በሀሳቧ " አንተ
ጅል ይሄ እቅድህ ሲፈፀም እኔ የናጠጠ ሀብታም አንተ ድሀ ትሆንና
አስወግድሀለው " እያለች እራቁታቸውን አልጋዋ ላይ ተያይዘው ወደቁ።
ሚካኤሌ አይኑን ወደ ውጭ ሄዶ እንዲሞክር ተነግሮት ከሀኪም ቤት ወጣ እናም
ወደ ቤቱ ሄደ ። አይኑ ማየት ስለማይችል ሙሉ የስራውን ሀላፊነት ለሰላም ሰጥቶ
አድማሱም እንዲረዳት አድርጓል የግድ በእሱ እጅ የሚፈረሙትን ይዛ እየመጣች
ታስፈርመው ነበር።
አንድ ቀን ሰላምም አድማሱም ወደ ድርጅቱ በሄዱበት ወቅት ከስጦታ ጋር
አብረው ቁጭ ብለው ሳለ ስጦታ።
" አባ አንድ ነገር ልነግርህ ነበር ግን እንዳላስከፋህ ፈራሁ " አለች ሚካኤሌ
እቅፍ ውስጥ እየገባች።
" አንቺ እኮ ልጄ ነሽ በአንቺ እንዴት እቀየማለው " አላት እቅፍ አርጎ እየሳማት ።
" አውቃለው አንተ የእኔ ብቻ ሳትሆን የፍቅር አባት ነህ " ስትለው ድጋሚ በደንብ
አቅፏት ሳማት ።
" እሺ በይ ንገሪኛ የኔ ልጅ "
" አንተ ሀኪም ቤት ሳለህ እሱ እዚህ ቤት ነበር የሚያድረው "
" አይ ልጄ ታዲያ ምን ችግር አለው የአጎቷ ልጅ እኮ ነው " አላት ነገሩን ቀለል
አድርጎ።
" በምን አወክ እነሱ ስለነገሩህ ብቻ እኔ ግን አባ ደስ አላለኝም እባክህ
ተጠንቀቅ " አለች ስጦታ።
" ልጄ የአጎቴ ልጅ ነው ካለች ማመን ነው ያለብን ህፃን ልጅ አይደለችም እሷን
የምንቆጣጠራት እውነት እኔንና ትዳሯን ካከበረች የትም አትሄድም ካላከበረች
የፈለገቺውን ታድርግ የእኔ ሀላፊነት ልጄ እንደ አባትነት አንቺን መውደድ ማፍቀር
ማስተማር መሰረታዊ ነገሮችሽን ሟሟላት እንደ ባል ደግሞ ትዳሬን ቤቴን
ቤተሰቤን ሚስቴን መውደድ ማክበር ታማኝ መሆንና እሷንም ማመን ነው
አይመስልሽም ልጄ " አላት
" አባቴ ስለሆንክ እኮራለው ከዛ ትምህርት በላይ የአንተ ትምህርት መንፈሴን
ይሞላዋል"አለችውና ተቃቅፈው ተሳሳሙ
ጊዜያቶች ሲሄዱ ሚካኤሌ ለአይኑ ህክምና ውጭ መሄድ ነበረበት ስለዚህ እሱ
በአጠገቧ ስለሌለ ፊርማውን እራሷ ፈርማ እንድታስተዳድር ሙሉ ሀላፊነቱን
በውክልና ሊሰጣት ሲያስብ ሰላምና አድማሱ በዚህ ወቅት አይኑ ባለማየቱ
እቅዳቸውን ለመፈፀም ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ በአጠገቡ ስጦታ እንዳትኖርና
ውሉን እንዳታነበው አርቀው ወደ አዳሪ ት/ቤት ላኳት ። በቃ ሁሉም ነገር ለሰላም
እንደሸጠላት የሚገልፅ ውል ይዘው ወደ ቤት መጡ።.......
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot