Get Mystery Box with random crypto!

ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ ክፍል አርባ (40) . . . ወደ ኋላ ከዕረዥም አመታት በፊት። | ETHIO BOOKS PDF

ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ

ክፍል አርባ (40)
.
.
.
ወደ ኋላ ከዕረዥም አመታት በፊት።
እንደ እውነቱ ፍቅር የልብ ጤንነት የአጥንት ጥንካሬ የመንፈስ እርካታ የስሜት
ደስታ ነበር እንደ እባብ በመሬት እየዳሀየች ተስባ ነክሳ መርዟን በሰውነቱ
እረጭታ በደም ስሩ እንዲሰራጭ በማረግ ካለ እሷ እንዳይቀሳቀስ እንዳይተነፍስ
አርጋ አስራና ወታትባ ሰለ እሷ ሀብት ንብረቱን አይደለም ሁለመናውን ሊሰጣት
ግድ ያሰኘው አንድኔ አንድ ምክንያቱ ፍቅርና ፍቅር ብቻ ነው።
ዕለት በዕለት የሚካኤሌ እና የሰላም የንግግር ቋንቋ ተለዋውጦ ፍቅር
በሚረጭበት አንደበት ሰላም የራሷ ለሚካኤሌ ያላት ግምት ግራ አጋብቷት።
ታፍቅረው ወይም አታፍቅረው አታውቅም ግን ሚኪን ሀብቱን ለመቀማት
አድማሱን ደግሞ የሰጠችውን ንፁሁ ፍቅር እና ገላዋን እንደ ምራቁ ሀክ ቱ ብሎ
ተፍቶት ብር እና ሀብት በመመኘቱ ሁለቱንም ለመቅጣት ዝግጁ ነች ። ይህን
የምታደርገው ደግሞ ውበቷንና የወሲብ ጥማታቸውን ለሀለቱም እየሰጠች
ገላዋን በደስታ የሰጠች እያስመሰለች በውሸት ደስታና ፈገግታ መስጠት
ያለበትን ሁሉ መስጠት።
አንድ ቀን ሴራቸው አድማሱና ሰላም እየሸረቡበት ሳለ ሚካኤል ድንገት መጣ
ሁለቱም ደነገጡ ። ሚካኤሌ ሁለቱንም ሰላምታ እንዳቀረበላቸው እሷ ድንገት
አፏ ላይ የመጣውን ጊዜያዊ ምክንያት ተነፈሰችለት እሷ በጊዜያዊነት የዘላለም
አሪፍ ምክንያት ሆኖ አድማሱ ከእዛ ቤት እንዳይወጣ አደረገው ።
" አይገርምህም ሚኪ ጠፋ ያሉኩሁ የአጎቴ ልጅ ነው ለካ አጎቴም ሞቷል እሱ
የአጎቴ የመጀመሪያም የመጨረሻም ልጅ ነው ..... ስላገኘሁት በጣም ነው ደስ
ያለኝ " አለች ደስ ያላት በማስመሰል ማስመሰሉ ከእሷ ውጪ ማን ተክኖበት ።
ሚካኤሌ ስለ አጎቷ በመስማቷ የደስደስ በማለት ልብስ እንድትቀይርና እራት
እንደሚጋብዛቸው ነገራቸው ቀጥሎም ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ ።
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ከመኝታ ክፍሉ ሲወጣ ሰላም እጅግ ተውባ እና አምሮባት
ተመለከተ በአድናቆት አፍን ከፈተው ።
ወደ አንድ እሬስቶራንት እራት ለመብላት ተያይዘው ተጓዙ ከታረቀኝ ጋር
ትውውቃቸውም በዚህ ወቅት ነበር ትውውቃቸውም እጇን ለመታጠብ ከሚኪ ጋር
ሄደው እሱ ለውሀ ሽንት መፀዳጃ ቤት ሲገባ እና እሷ እጇን በመታጠብ ላይ ሳለች
ግን መልኩ ስላስጠላት አቋሻው ነው ያባረረችው ከዛ በኋላ ሁሌም አቋሿው
ነበር የምታባርረው እሱ ግን አንድ ቀን ብሎ በተስፋ ይጠብቃት ነበር ።
እናም እቺ ቀን የብዙ ነገሮች መፈጠሪያ ሆናለች እራት ከበሉ በኋላ መጠጥ
ጀምረው ሰላም እራሷን እስክትስት ያረገችውን አለማወቅ ድረስ ነበር የሰከረቺው
በዚህ ወቅት ከአድማሱ ጋር ተጠቃቅሳ ሽንት ቤት ብለው በመሄድ በጓሮ የዕነ
ቶሎ ቶሎ ቤት የሆነ ወሲብ ፈፀሙ ምስኪኑ ሚኪ ከአጎቷ ልጅ ጋር ነው የሄደችው
ብሎ ቁጭ ብሎ ይጠብቃል።
ለሊቱ አጋማሽ ላይ በበቃኝ ከሬስቶራንቱ ወጥተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ አድማሱ
መንገድ ላይ ወረደ እነሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ ። እቤት ከደረሱ በኋላ ግን
ተነጣጥለው መተኛት አላስፈለጋቸውም ወደ እሱ መኝታ ክፍል ተያይዘው ገቡ
ሁሌም ሚኪ ከሰላም ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ መከላከያ ይጠቀም ነበር ዛሬ ግን
ያንን ለማረግ አቅሙም ሆነ ብቃቱ አልነበረውም ዝም ብሎ ነበር የፈፀመው
የስጦታ ትክክለኛ አባት ማን እንደሆነ እራሷ ሰላም ግራ የገባት ለዚህ ነው
ማስታወስም አልቻለችም ከስካሯ አንፃር በዚህ ላይ ለስጦታ ምንም የእናትነት
እና የልጅነት ፍቅር በሁለቱም ውስጥ ምንም ፍቅር የለም ። ስጦት ወደ
ማደሪያው ት/ቤት ከመግባቷ በፊት ዲ ኤን ኤ ተመርምራ የአድማሱ ልጅ
እንደሆነች ማረጋገጫ አጊተዋል ሰጦት ግን ደሜ የሚለኝ የሚኪ እንጂ የአድማሱ
አይደለም ትላለች እና መቀበል አቅቷታል በፍፁም አትፈልጋቸውም ።
በወቅቱ ሚካኤሌ በሰማኒያ ሊያገባት የተስማማውም ስጦታ መፀነሷን
ስትነግረው ነበር ተጋብተው ጥሩ ሚስት ሆና የኖረችው ከዛ በኋላ ሚስት ሳትሆን
መከራ እና ስቃይ ሆና ፍዳውን ስታሳየው የኖረችው ። ይሄ ድርጊቷ የአድማሱ
እቅድ ነበር ተሰላችቶ እንዲፈታት ነበር አልተሳካም።
ስጦት ካደገች በኋላ አድማሱ የመጨረሻ ሚካኤሌን ለመግደል እቅድ አወጡ
የመኪናውን ፍሬዬን በጥሰው ገደል ለመክተት እንዳሰቡትም ፍሬዬኑን በጠሱት ።
ሚካኤሌ ሀገር ሰላም ብሎ ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ መኪናውን አስነስቶ
እየበረረ ወደ ድርጅቱ በመሄድ ላይ ሳለ መሀል መንገድ ላይ ፍሬዬኑ እንቢ አለው
በመጨረሻ ማድረግ ያለበት በሰው ላይ አደጋ በማይፈጥር ቦታ ላይ አጋጭቶ
ማቆም እንዳለበት ወስኖ ከአንድ ግንብ ግቢ ላይ አጋጨው መኪናው ጭርምት
ከማለቱ የፊቱ መስታወት እረግፎ በሚካኤሌ ሰውነት ላይ እና አይኑ ላይ ተሰካካ
።..........
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot