Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_7

... በቃ ጌዲዮ ሄደ አንድ ሁለት ተብሎ ሶስተኛ ቀን ተቆጠረ መቅደስ ግራ ገባት ከክፍል ተማሪ አንስታ እስከ ዳሬክተር እየተመላለሰች በምን ምክንያት እንደጠፋ ጠየቀች ግን መልስ ማግኘት አልቻለችም የጌዲዮ መጥፋት የዩንቨርስቲውም አሳሳቢ ዜና ሆኑዋል ምክንያቱም ጌዲዮ በጣም ተስፋ የተጣለበት ጎበዝ ተማሪ ነው።
........መቅደስ ምግብ አልበላ ውሀ አልጠጣ አለች ትኩረቷም ከትምርቷ ተነሳ ታመመች ምንም የግሏ ባይሆንም አቅፋ ስታስታምመው የራሷ ያደረገችው ያክል ስለሚሰማት ደስተኛ ነበረች ፍቅሯ የጋራ ባይመስላትም እሷ ግን አይኑ ነበር የፍቅር ምግቧ አሁን ግን ጠፋ ምክንያቱን እንኳን ሳታውቅ ተሰወረባት ብቸኝነት ተሰማት።
.......አሁን የዮናስ እና የወይንሸት ሀሳብ ተሳካላቸው የጀመረውን ጌም ለማሸነፍ አንድ እንቅፋቱን አስወገደ መቼም ከዚህ ቡሀላ ይመጣል ብሎ መገመት ከባድ ነው።
.........መቅደስ እራሱዋን አስራ ብቻዋን ዶርም ተኝታ በናፍቆት እየተብሰለሰለች ትገላበጣለች ከዛም እነሰአዳ መጡ በየቦታቸውም አረፍ አሉ ወይንሸት ግን ይህን የተወጣጠረ እርቃኑዋን ነች አትባል ለብሳለች አትባል ብቻ ለባብሳ መቀባባት ጀመረች እነብርሀን የመቅደስን ሁኔታ እያዩ ነው አያባብሏት ነገር ብዙ ብለዋት ማፅናኛ ቃል አልቆባቸዋል ደግሞ ያውቃሉ መፍትሄ እንጂ ምክር አይጠቅማትም.....
....ከዛም ሰአዳ ወደ ወይንሸት ዞራ ወይና ግን በአላህ ምናል ትንሽ እንኳን ሸፈን ያለ ነገር ብትለብሺ አለቻት እሷም አረ ይሄም እራሱ እረዝሟል ስትል ብርሀን እግዚኦ ታዲያ አንድኛሽን እርቃንሽን አትሄጂም ስትል መቅደስ በተዋጠው ድምጿ ግን የት ልትሄጂ ነው እንዲህ ሆነሽ አለቻት እሷም እእእ ፖርቲ ዛሬ እኮ እኔና ሚኪ የተዋወቅንበት አንደኛ ወራችን ነው አለች መቅደስም አይ ለወደፊትማ ሰላም ከተባባልሽው ወንድ ሁሉ ልደት ታከብሪያለሽ ብርሀን ሳቅ ብላ የት ይቀራል አለቻት።
ከዛም ወይና ወደ መቅደስ ከተኛችበት አልጋ ተጠግታ እንዳዘነ ሰው ቅልስልስ ብላ መቅዲ ግን ይሄን ጌዲዮን እረስተሽ ለምን ከዮናስ ጋር አዲስ ላይፍ አትጀምሪም እስከመች እንዲህ ተኮራምተሽ አለቻት እነብርሀንም ግራ ስለገባቸው አው እርሺው እሱ እንደሁ ጥሎሽ ሄዷል እራስሽን ማረጋጋት አለብሽ አሏት መቅደስም እናንተ ምን ነካችሁ ዮናስ እኮ ንፁህ ጓደኛዬ ነው ወይንሸትም ፈጠን ብላ እሱ ግን ያፈቅርሻል ስትላት ስልኳ ጮኸ በቃ መቅዲ አስቢበት ብላ ቦርሳዋን ይዛ ስልኳን እያናገረች ወጣች ከዛም እነብርሀን ወሬውን ሊቀጥሉ ሲሉ መቅደስ ይልቅ እኔም ስለ ጌዲ ያልጠየኩት አንድ የክፍሉ ልጅ አለ እሱ ጋር ልሂድ ብላ ተነሳች ሰአዳና ብርሀንም ተከተሏት።
...ሄደውም ሌላ ጓደኛውን አገኙ ይቅርታ ወንድም በለጠውን ፈልገን ነበር ሲሉት በሌ መቃሚያ ቤት ነው በዚህ ሰአት እዚህ አይገኝም ግን እኔም እዛው ልሄድ ድለሆነ ከፈለጋችሁ ልውሰዳችሁ አላቸው እነሱም ተስማምተው አብረውት ሄዱ።
በእውነት እዚህ መንደር መቃሚያ ቤት ቀርቶ ሱቅ እንኳን ያለ አይመስልም ብቻ እያሹለከለከ ወሰዳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ በጣም ተደናገጡ ውስጥ ያሉት እነመቅደስን እነሱ ደግሞ ተማሪዎቹን እያዩ ተፋጠጡ ግማሹ ጫት ይቅማል ግማሹ ሺሻ ያጨሳል ሌሎቹ ሲጋራ ቀስ ብለው ተቀመጡ ከዛም በትዝብት ቤቱን ይቃኙ ጀመር አብዛኞቹ የግቢ ተማሪዎች ናቸው ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚቅሙና የሚያጨሱም አሉ
ከዛም አንዷ መጣችና ምን ልታዘዛችሁ አለቻቸው በዚህ ሰአት ያመጣቸው በለጠውን ሊጠራ ሄዶ ነበር እናምአረ ምንም አንፈልግም አሉ ታዲያ ምን ልትሆኑ ገባችሁ ስትላቸው በለጥው ተያቸው እኔን ፈልገው ነው አላት
ከዛ አጠገባቸው መጥቶ ተቀመጠ ምን እንደፈለጉ ሲጠይቃቸው ስለጌዲዮ የምታውቀው ነገር ካለ ብለን ነው አሉት።
.......ስለሱማ እኔም በጣም ታስዝቤሻለሁ ያረግሽው ነገር እኮ ከንዳንቺ አይነት ሴት የማይጠበቅ ነገር ነው አላት መቅደስ ምን እንደምታወራ አልገባኝም አለችው ለማንኛውም ልወጣ ስለሆነ እየሄድን እናውራ አላቸው ከዛም ተነሱ
....ቀጠለ ልንገርሽ ጌዲዮ ትምርቱን የተወዉ ባንቺ ምክንያት ነው መቅደስ በጣም ደነገጠች ማፍቀሩን ባይገልፅላትም ያኔ ጌዲዮ ብቻውን ሆኖ ሲያወራ ከበር ቆሞ የሰማውን ሁሉ ነገራቸው።
.........መቅደስ እነ ብርሀንን ጠየቀች ማነው ማነው እንዲህ ያለው?? እኔኮ የወደኩት ብላ የወደቀችበትን ሁኔታ ነገረቻቸው እነሱም አንገት ደፉ ብርሀንም ሙሉ ግቢው እኮ ነው በሱ በሽታ መውደቅሽን ያወራው ስትል ታዲያ ለምን አልነገራችሁኝም ብላ ጮኸች ሌላ ህመም ጌዲዮ በሷ ሰበብ እንደሆነ አወቀች ትምርቱን የተወው...
በቃ ትምርትም አስጠላት ይኸው ክፍል ቁጭ ብላ ሀሳቧ ግን ሌላ ጋር ነው ከዛም አቋርጣ ወጣች ሰአዳም ተከተለቻት መቅደስ ግን ምን እየሆንሽ ነው ቢያንስ ለናት አባትሽ ለቤተሰቦችሽ አታስቢም የውጪ እድልሽን አሳልፈሽ እየተማርሽ ያለሽው እኮ ያስተማረሽን ህዝብና ሀገር ለመጥቀም ነው ከሁለት አጥ አትሁኚ እንጂ አላማሽን እንዴት ትዘነጊያለሽ ብላ ሰአዳ ተቆጣቻት መቅደስም እንባ ተናንቋት አቃተኛ አቃተኝ ምን ላርግ አልቻልኩም እንደውም እኔም አልማርም ስትል ሰአዳ መቅደስ ይሄ መፍትሄ አይሆንም ባይሆን ለምን አድራሻውን ፈልገን አንሄድም አለቻት ከዛም ተያይዘው አድራሻውን ለማግኘት ወደ ቢሮ ሄዱ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic