Get Mystery Box with random crypto!

. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_5

... መቅደስ ልትመለስ ስትዞር ቀሚሷ ጠልፏት እየጮኸች ቁልቁለቱን ተንከባለለች።........ሶስቱ ጎረምሶችም ድምጿን ሰምተው ከተቀመጡበት በፍጥነት ተነሱ ግን ወዲያው ፀጥ ስላለች ያለችበት ቦታ ጠፋቸው ግራ በመጋባት እየዞሩ ፈለጓት ከዛም አይ ጆሯችን ነው ብለው ወደ በርጫቸው ሲመለሱ ድጋሚ በስተ ኋላቸው ድምፅ ሰሙ እየተሯሯጡም ሲሄዱ መቅደስ በሾክ ፊቷ ተቦጫጭሮ ደም ለብሷል መነሳት አቅቷት እያቃሰተች እየተፍጨረጨረች ነው እንዲህም ሆና ውበቷ እንኳን ለመረቀነ ለማንም አሳልፎ ይሰጣል ሶስቱም ሊበሏት ጎመጁ ስቃዩዋና ለቅሶዋ አልታያቸውም እርስ በርስ ተነጋገሩ አቅፈውም ወደ ተቀመጡበት ቦታ ወሰዷት መቅደስም ሊደፍሯት እንደሆነ ሲያወሩ ስትሰማ ጭንቅላንቷ ከመታት ድንጋይ ጋር ተደምሮ እራንሷ ሳተች።
............ጌዲዮ በዚያ ሰአት ጥናቱን ጨርሶ ሳያያት አልፏቸው ወደ ግቢ ሄደ.።
....... ጎረምሶቹም እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም እያሉ መጨቃጨቅ ጀመሩ ከመቅፅበት ያንድኛው ስልክ ጮኸ በፍጥነት አንስቶ ሄሎ ዮኒ ሲል ምኑ ጋር ናችሁ አለ ልጁም የባለፈው ቦታ ነን ደግሞ ዛሬ በተቀደሰው ማእዳችን ላይ የተቀደሰ የምስራች ይዘን ነው የምንጠብቅህ አለውና ስልኩን ዘጋው ዮናስን በጣም ስለሚፈሩትና ስለሚያከብሩ ሊጠብቁት ተስማሙ።
.......እነብርሀንም የመቅደስ ያለወትሮ ሳትናገር መጥፋት አሳስቧቸው ስልኳን ደጋግመው እየሞከሩ ነው ቢሆንም ስልኳ ካገልግሎት ክልል ውጪ ነች ይልላ አሁን ያላቸው አማራጭ ትሄዳለች ብለው ያሰቡበት ቦታ እየሄዱ መፈለግ ነው እስካሁንም የቆዩት እንደለመደባት ጌዲዮንን ተከትላ ነው ብለው ነበር አንሁ ደግሞ ጌዲዮን ግቢ ውስጥ አዩት
........ዮናስ ጓደኞቹ ከሚቅሙበት ቦታ ሲደርስ መቅደስን አያት ባይደነግጥም በጣም እንደደነገጠ ሆነ መቅደስን ከጁ መዳፍ ለመጣል ትልቅ ወጥመድ አገኘ በርግጥ ዮናስ እንደ መላእክት ቀርቦ የልቡ ሲደርስ ሰይንጣ መሆን የለመደው ድርትጊ ነው።ጓደኞቹም በሁኔታ ተገርመው ምን ታቃለታህ እንዴ አሉት እሱም አይ አላቃትም ግን የግቢያንች ተማሪ ናት ሲል ሳቁበትንና አረ ዮኒ ላሽ እርኩስ ደርሶ ፃድቅ ልንሁ ሲል አምያርትበም አሉት ዮናስ ግን እንቢ እንምይማሉት ስለሚያውቅ ዛሬ ማታ በርድ በርድ የሆኑ ቺኮችን አመጣላችኋለሁ መቅደስን ግን ለኔ ተዉዋት አላቸው ሆኖም ሁኔታው ቢያስገርማቸውም ብምዙ ሳይከራከሩ በሀሳቡ ተስማሙ።............ዮናስም እዚያው እንድትነቃ ስላልፈለገ አቅፎ ወደ ሆስፒታል ይዟት ሄደ።
.........ቀኑ ምሽቱን ተካ የመቅደስን መሰወር ሙሉ ግቢው ሰማ ትኖራለች ተብሎ የታሰበበት በሙሉ ተፈለገች ግን አልተገኘችም የበላት ጅብ አልጮህ አለ ጓደኞቿ በጣም ተጨናነቁ........
......መቅደስ ሆስፒታል በገባች ግማሽ ሰአት ውስጥ ነቃች ስትነቃ የምታየውን ማመን አቃታት ከዛ አስፈሪ ጫካ ወጥታ ሆስፒታል ከነዛ የሰው አውሬዎች ተርፋ እራሷን ከዮናስ ጋር ስታገኘው በህልሟ መሰላት እውነታውን ለማረጋገጥ ቸኮለች ዮናስም ጭንቅላቷን በጆቹ እየደባበሰ አይዞሽ አታስቢ ተርፈሻል አላት መቅደስም ይህ እንዴት ሆነ እዛስ ጫካ እንዴት መጣህ እንዴትስ ምንም አልሆንኩም ስትል ጥያቄ ደርድራ ጠየቀችው ዮናስም በገዳይ ምላሱ የሌለ ውሸት ጨማምሮ ብዙ ችግር ደርሶበት እንዳዳናት ነገራት ነግሮም አሳመናት መቅደስም በደስታ እያመሰገነች አቀፈችው።
.....በጣም ቆስላ ስለነበር ለትንሽ ቀን እንደልብ መንቀሳቀስ አትችልም ለዛሬ እዚሁ ትደር ብላ ነርሷ ለዮናስ ነገረችው።እናም እዚያው አብሯት አደረ።
........እውነት ለመናገር ጌዲዮ መጥፋቱዋን ከሰማበት ሰአት ጀምሮ በሀሳብ ሲብሰለሰል መሄጃ ጠፍቶት ሲቁነጠነጥ እንዲችው እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አደረ።...... ጓደኞቿም ቢሆኑ ሲፈልጓት ነው ያደሩት
........ጠዋት ዮናስ መቅደስን በኮንትራት ታክሲ ይዟት መጣ ከዛም አውርዶ እስከ ሴቶች ዶርም ድረስ ተሸክሟት ሄደ ጌዲዮም ከሩቅ አያቸው ጓደኞቿም እየተሯሯጡ ተቀበሉት ምን ሆና እንደሆነም ጠየቁት እሱም ጫካ ውስጥ ወድቃ እንዳገኛት ነግሯቸው አስተዛዝኖ እግዚአብሔር ይማርሽ ብሏት ተመለሰ መቅደስም ዮኒ አለችው እሱም ቶሎ ተመልሶ ፊትለፊቷ ቆመ መቅደስም ምን ብዬ እንደማመሰግንህ አላቅም ቃላቶች ያጥሩኛል ብቻ ፈጣሪ ውለታህን ይክፈልልኝ ብላ ጥምጥም ብላ አቀፈችው።ጌዲዮ አሁንም እያያቸው ነው መተቃቀፋቸው ሳይሆን ምን እንደሆነች ለማወቅ ነበር የጓጓው ።ሆኖም
...... መቼም ወሬ የማያጣ ሰው እንዲህ ሲባል ወሬ ተለኮሰ የመቅደስ መውደቅ የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው እያለ ወሬ ከዛ ከዚ ሲወረወር ደጋግሞ የጌዲዮ ጆሮ ገባ ጌዲዮም እውነት ይሆን እንዴ ብሎ አነባ እራሱን የማይረባ የማይጠቅም ሰበበኛ አድርጎ ቆጠረ ለምን ፈጠርከኝ ብሎ ፈጣሪውን አማረረ ........በቃ ሂወት እጅ እጅ አለችው እራሱን አገለለ ...

ይቀጥላል...

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic
በታሪኩ ዙሪያ comment አድርጉልን