Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_4

... ጌዲዮ ከዛን ቀን ጀምሮ ወድቆ ሲነሳ ማንንም አያገኝም ይበልጥ ከፋው ምክንያቱም መቅደስ የረሳውን ልምድ ነበር እንዳዲስ ያስጀመረችው ቢሆንም በሱ ሀሳብ ድጋሚ ልትደግፈው እንደማትመጣ ያውቃል።ገና ባጭር ጊዜ ትናፍቀው ጀመር ደግሞ በሱ ምክንያት እንዳትጎዳ ማድረጉን ሲያስብ ውስጡ ሰላም ያገኛል።

........መቅደስ ወድቆ ስታይም ይሁን ወደቀ ስትባል ሞተ የተባለች ያክል ነው የምታነባው....ፍቅሯ ሲብስባት እየተደበቀች በሄደበት ሄዳ ታየዋለች።የሱ አትንኪኝ አትደግፊኝ ስለኔ አይመለከትሽም ማለት ፍቅሯን አልቀነሰውም እንደውም ይበልጥ አፈቀረችው።

........መቅደስ ከጓደኞቿ ጋር በመሆን ከቤተ-መፃህፍት ሲወጡ ሰአቱ ምሽቱን ሊቀበል ተዘጋጅቶ ነበር። የጅማ ነፋሻማ አየር ወደ ዶርም እንዲገቡ አልጋበዛቸውም።እናም ወጣ ብለው ወክ እያረጉ ለመናፈስ ተስማሙ።...............
ብርሀን በተፈጥሮዋ ቅልብልብ ነች እናም በዛ ሰአት የማይነሳ እርእስ አንስታ ወሬ ጀመረች...መቅዲ እኔ ግን ያንን ደነዝ አስተማሪ ይቅርታ ሳጠይቂው መግባትሽ ገርሞኛል ስትል ሄዋን ቀበል አርጋ ምን ይገርማል ጥፋተኛው እኮ እሱ ነው አለች ሰአዳም መቅደስ እንደከፋት ብታውቅም ወሬውን ለማስጨረስ ወላሂ እንዳለው ቢከሳት ኖሮ ግን የሚቀጣው እሱ ነበር ስትል መቅደስ ፕሊስ ጨዋታ እንቀይር አለች።
ይህን ጊዜ ሰአዳ መቅደስ ከገጠማት ሀዘን እንድትላቀቅ ያሰበችውን መፍትሄ ለማቅረብ እኔ ግን አንድ ሀሳብ አለኝ ስትል ሁሉም በመጓጓት ምን አሏት.......እእእ ምን መሰላችሁ ያው ሁሉም እንደሚያውቀው ጌዲዮ ሲወድቅ እራሱን አያውቅም ከህመሙ ከተረጋጋም ቡሀላ ለመንቃትና እራሱን ለማወቅ ብዙም ባይሆን የተወሰኑ ደቂቃዎች ይፈጅበታል ይህ ማለት መቅደስ እሱ ሳያይሽ ልትረጂውና ከጎኑ ልትሆኚ ትችያለሽ አለቻት በሰአዳ ሀሳብ ሁሉም ደስ አላቸው።
.........መቅደስ አሰበች ጌድዮ ስነቃ አጠገቤ ባገኝሽ እመታሻለሁ ያላት ትዝ አላት ድንገት ቢነቃብኝ ብላ ሰጋች ቢሆንም ካጠገቡ ሆና ህመሙን ለመታመም ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አታገኝም ከዛ በሀሳቧ ሙሉ ለሙሉ ተስማምታ ወካቸውን በደስታ ቀጠሉ።

........ጌዲዮ ከቤተ-መፅሀፍት ይልቅ ብቻውን እራቅ ብሎ ጫካ ውስጥ ማጥናትን ያዘወትራል ሰሞኑን ግን ካለወትሮው ብዙ ነገሮቹ ተቀይረዋል ከትምርትና ከምግብ ሰአት ውጪ እንዲሁም ድንገት ወደዶርም ሲገባ አልያም ከወደቀ እንጂ ግቢ ውስጥ በብዛት አይታይም ካንገቱማ ቀናም ብሎ አያቅ ነበር አሁን ግን ቀና ብሎ አሻግሮ ያላየውን ጉድ እያየ መታዘብ ጀምሯል ይሁን እንጂ ይባስ በሽታ ጨምሮበታል።መውደቅ መነሳት ግቢውን እየዞረ መቅደስን ለማየት መጣር ውይይይይይ ብቻ እሷ ባታውቅም እሱም በሷ በሽታውን አብሷል በሀሳቡም በለፈለፉ ይጠፉ አለ ያገሬ ሰው ምነው የዛን ቀን አፌን በቆለፈው ብሎ ተመኘ።

..........መቅደስ እንዳያያት እየሸሸች ከጎኑ ተለይታም አታውቅም ውይ እንዳያያት በምታደርገው እሩጫ የማይገርመው የለም ስንት አማላይ ቆንጆ እየለመናት አሻፈረኝ ብላ ጌዲዮ ላይ ሙጭጭ ማለቷ እውነትም ታምር ነው።
.....ይኸው ዛሬ ጌዲዮ እሷን በመፈለግ ቆይቶ እንደማያገኛት ሲሰማው መፅሀፉን ይዞ ወደለመደው ጫካ ሄደ መቅደስም ተደብቃ ተከትላው ሄደች።
.....ጌዲዮ እንደደረሰ ለምለም ሳር ላይ አረፍ ብሎ ዛፎቹን ተደገፈ መፅሀፉንም ሳይከፍት ሀሳቡን ወዳስገረመው የዩኒቨርሲቲ ግቢ ወሰደው በጣም ብዙ ተማሪና ሰራተኞች ካንዱ ወዳንዱ ከዚ ውደዛ ከዛ ወደዚ ውር ውር ይላሉ ግን አንድ አመት ከግማሽ መንፈቅ ሊሞላው ቢሆንም ይህን ሁሉ ጊዜ ሲማር አንድም ሰው እንዳልተጠጋው ሲያስብ ግን መቅደስ ለምን ከዚህ ሁሉ ሰው ተለይታ ልትረዳው እንዳሰበች ጥያቄ ሆነበት.....ሌላው ያስገረመው አንገቱን ቀና ቢያደርግ ብዙ ጥንዶች አየ ብዙ ጓደኛሞችም ተሰብስበው ሲጫወቱ ሌሎች ደግሞ ምንገድ ላይ ሳይቀር ሰላም ሲባባሉ ያየውን በህሊናው ስሎ ቆይ እኔ ማነኝ ብሎ አሁንም የማይመለስ ጥያቄ ለራሱ ጠየቀ።የጌዲዮ አለም መፅሀፍ ብቻ ነው ከዛ ውጪ የህይወትን ጣእም አያውቃትም...አሁን ህሊናውን እንደምንም ሰብስቦ መፅሀፉን ገለጠ።

......መቅደስ ከሩቅ ሆና በስስት ታየዋለች የለበሰችው ቀሚስ ስለነበር አላራምድ ብሏት ከፍ አድርጋ ይዛዋለች አሁንስ ለራሷም ገረማት ፍቅር እንዲህ ያደርጋል ብላ አስባም አታውቅም አረ እንደውም በጓደኞቿ ስታሾፍ ነበረ ያው የናቁት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል ነውና ተረቱ ጊዜ ተረኛ አርጓት እንዲህ ስትባዝን እራሷን ታዘበች።
ጫካው በጣም ጥቅጥቅ ያለ እና ፀጥታ የሰፈነበት ነው ካዋፋትና ከዛፎቹ ሽውሽው ድምፅ ውጪ ምንም አይሰማም እንደው ደፍራ ብቻዋን እዚህ ጫካ የምትገባ ሴት ያለችም አይመስልም ዞር ዞር ስትል ፈራች መጀመሪያ ጌድዮን ብቻ እያየች ነበር ተከትላው የገባችው አሁን ግን ድንገት ቢያየኝ ምን ይፈጠራል ብላ ስታስብ ፍርሀቷ ጨመረ እናም ለመመለስ ወሰነች...መንገዱን እንኳን በትክክል አታውቀውም ቢሆንም በግምት እየተደናበረች ጉዞ ጀመረች አሁን ጌዲዮ ከተቀመጠበት ብዙ እየራቀች ነው......ኮሽ ባለ ቁጥር እየተንቀጠቀጠች እየወደቀች እየተነሳች ጉዞዋን ቀጠለች አሁን ግን መሀል ጫካ ውስጥ ቆመች የምትሄድበት ጠፋት መንገዱ ተሰወራት ግራ ቢገባት ወደ ጌዲዮን ለመመለስ ወሰነች ቢሆንም በየት ብላ ትሂድ ማንን ትጣራ ጨነቃት ግን አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ እግሯ ወዳመራት መጓዝ ጀመረች ጫካው ትልቅ ነው በውስጡ ብዙ አውሬ እንዳለ ባታይም ባትሰማም መገመት አላቃታትም እዛው እያለች እንዳይመሽ ፈጣሪዋን እየለመነች ምንገዷን ቀጠለች።

........ጥቂት ከተጓዘችም ቡሀላ ባየችው ነገር ምነው ጌዲዮ አይቶ በገደለኝ ብላ እስክትመኝ ክው ብላ ቀረች በጣም የሚያስፈሩ ሶስት ጎረምሶች ቁጭ ብለው ጫት እየቃሙ ነው ፊትለፊታቸው ከመቆሟ አንፃር ትንሽ ኮሽ ብታደርግ እንኳን ያዩዋታል ካዩኝ ደግሞ አይለቁኝም ብላ በንባ ትእርሳ የዱር አውሬ ቢበላኝ ይሻለኛል ብላ ወደ መጣችበት ልትመለስ ስትዞር ቀሚሷ ጠልፏት እየጮኸች ቁልቁል ተንከባለለች...

. ይቀጥላል...

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic

በታሪኩ ዙሪያ comment አድርጉልን