Get Mystery Box with random crypto!

፨፨ አንቺ ባትኖሪልኝ፨፨ የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ፣ የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ፣ | መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

፨፨ አንቺ ባትኖሪልኝ፨፨
የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ፣
የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ፣
የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ፣
የሀጢያት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ፣
ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ፣
ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ?
አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ፣
የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ፣
በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ፣
በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ።
ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ?
ሀጥያት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ፣
ብርሀንን ወልደሽ ፀሀይ የሆንሽልኝ፣
ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ፣
አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ፣
ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ።
https://t.me/kinexebebe