Get Mystery Box with random crypto!

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ #ከማስታዎሻየ_ማህደር!! . . . #ህይወት_የመኖር_እዳ!! . . .. | ቅንጭብጭብ

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
.
#ህይወት_የመኖር_እዳ!!
.
.
.. ከተወለድኩ ጀምሮ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር ወደ ህይወት እየመጣሁ ይሆን ወይስ ወደ ሞት እየሄድኩ እንደሆን አላዉቅም! ስለ ህይወት እያወኩ ለመኖር እየጀመርኩ ግን ወደ ሞት እየሄድኩ ይመስለኛል! መኖር ታዲያ እንዴት ስጦታ ሊሆን ይችላል?? ሐይማኖተኛ ሰዎች አንደበት ላይ እማይጠፋ ቃል "በህይወት ስላለህ ብቻ አመስግን!!" እሚለው ነው!! ግን ለኔ አይታየኝም! መፈጠሬን እንደስጦታ አይቼ ለማመስገን ህይወት በቃኝ እስክል መኖር አለብኝ! ካልሆናማ እንዲሁ ወደ ህይወት እየመጣሁ ወደ ሞት ከሄድኩ ስጦታነቱ ቀርቶ ኑሮ እዳ ይሆንብኛል!! ሳልሞት በፊት ተሽቀዳድሜ መኖር ያለብኝ እዳ ሁኖ ይሰማኛል። ሰው ሳይኖርም ይሞታል!
   ህይወት ከፈጣሪ እምትሰጠን ብድር ትመስለኛለች ብድራችን ለመክፈል ስንፈጋ ስንታገል የተሰጠን የክፍያ የቀን ገደብ አልቆ እኛም በነፃነት ሳንኖር እምንነጠቃት ናት። የሰው ልጅ ሁሉ "የህይወት ግብ ደስተኛ መሆን ነው!" በምትለው ህግ ይተዳደራል! ይሄን ህግ ሐይማኖተኞች ቢያጥላሉትም በነሱ ልብ እንደማያምኑበት ቢናገሩም እነሱም በሆነ የህይወት ዘመናቸው ይከተሉታል። ሁሉም ሰው በራሱ ዛቢያ ኑሮን ለማሸነፍ ይሽከረከራል፤ ኑሮን ማሸነፍ ያው ሀፍታም መሆን ነው! ብሎ አዕምሮው ላይ በሰቀለው ሃሳብ ይነዳል። መፈጠሩን እንደ እዳ ለማየት ወይንም እንደ ስጦታ ለመቀበል በቀላሉ በአኗኗር ዘይቤው ይወስናል፤ ብዙዉን ጊዜ ሀፍትን ካካበተ ስጦተነቱን በተቃራኒው በድህነት ከተሰቃየ ደግሞ እዳነቱን ይቀበላል፤ እዚህ ላይ አንዳንድ ነገረኛ አንባቢ "ታዲያ አንተ በድህነት ተሰቃይተህ ነው! ህይወት የመኖር እዳ ናት የምትል" ይል ይሆናል! ግን ህይወት እንዳለህ ሀብት ወይም እዉቀት የምትወሰን ናት በሚለው አልስማማም!! ምክኒያቱም ህይወት አወቅንም አላወቅን ሀፍታም ሆን ወይ ፀደቅን እስክንሞት ድረስ እዳ ናት!! አዋቂው ህይወትን ተረዳኋት ባላት መጠን ሲያብራራና ሲያወጣ ሲያወርዳት ትንሽ በተጠጋት ቁጥር እማያዉቀው እልፍ መሆኑን እየተረዳ አለማወቁን አዉቆ እንኳ እረፍት ሳያገኝ የእዉቀት ጥሙን ሳያረካ ያርፋል!! አላዋቂዉም መኖር ባለማወቅ የሰጠችዉን ሰላም ተቀብሎ መኖሩ ሳይታወቅ በሚራመድበት መሬት የሆነ መስመር የእግሩ አሻራ ሳይታይ ይሞታል!! ሀፍታሙ ሃፍቱን የደከመበትን ያህል ሳያጣጥመው ወይ ደግሞ በሀፍቱ ልክ ደስተኛነቱ የወረደ ሲሆንበት! ወይ ሀፍቱ እረፍት እንደነሳው ሌላ አስደሳች ግብ ወይ ምላሽ ሲፈልግ ያልፋል!! ፃዲቁ ደግሞ የፈጣሪው ፍርድ እያስፈራው በአካባቢው ያሉ ሰዎች ኑሯቸዉን በሐጢያታቸው እየለካ የመኖር ጣእሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ሞቱ እንዲቀርብለት እየፀለየ ይኖራል!? መፈጠሩ ስጦታ ነው ብሎ ግን መኖሩን ከመሞት በላይ አይወደዉም! ስጦታ ብሎ የተቀበለዉን ህይወት በሞት መነጠቅን ይናፍቃል እንደናፈቀዉም አይቀርምና ያገኘዉና ይቀበላል!!
   በነዚህ ሁሉ መሃል እኛ "ሁሉን ቀመስ!" እምንባል አይነት ሰዎች አለን!! የማህል ዳኛ ማለት ነን፤ ሌሎች በተለያየ አቅጣጫ የመኖራችን ግብ ብለው ያመኑበትን ሲያስቆጥሩ እምናጨበጭብ አንዳንዶች ደግሞ ሲደናቀፉም (ፋዎል) ሲሰሩ እምንታዘብ!! አለን። ለኛ ህይወት ጥያቄ እንጅ መልስ ሁና እማታዉቅ!! ህይወት የመኖር እዳ እንጂ ስጦታ ሁና እማትታየን!! ብዙ የገባን ይመስለናል ግን አንዳች ነገር አንፈታም! እምናምን ግን ደግሞ እማናምን! ወደ ህይወት እንመጣል ግን ደግሞ እማንደርስ! ወደ ሞት እምንሄድ!! እዉቁ ፈላስፋ.. "ያልተመረመረ ህይወት ለመኖር ያልተገባ ነው!" እንዳለው የኛ እዳ ጥያቄ የሆነ ነን። የናንተስ የመኖር እዳ ምንድን ነው?? እዳ ካልሆነ ስጦታነቱን በምን አመናቹህ? ስጦታነቱ ምኑ ላይ ነው? ተሰቶ እሚነጠቅ ስጦታ መሆኑንስ እንዴት ታዩታላቹህ? ወደ ህይወት እየመጣቹህ ነው ወይስ ወደ ሞት እየሄዳቹህ??
.
.
.
ህዳር 28/2015 ዓ.ም

Aman YTZ
@amanYTZ23

join
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23


@kinchebchabi @kinchebchabi