Get Mystery Box with random crypto!

✞✞✞ ቅዱሳን ዘ ኢትዮጵያ ✞✞✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusan_z_ethiopia — ✞✞✞ ቅዱሳን ዘ ኢትዮጵያ ✞✞✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidusan_z_ethiopia — ✞✞✞ ቅዱሳን ዘ ኢትዮጵያ ✞✞✞
የሰርጥ አድራሻ: @kidusan_z_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.02K
የሰርጥ መግለጫ

✞ቅዱሳን ዘ ኢትዮጵያ ✞
♦♦♦ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን♦♦♦
❇ የዚህ ቻነል አላማ ❇
▶ ▶ ▶ ከኢትዮጵያ የተገኙ የቅዱሳን አበው እመውን (አባቶች እና እናቶች) የቅዱሳንን ስም ፡ የተጋድሎ ህይወት ፡ ፍሬ በጥቂቱ ማስተላለፍ ማስተማር ነው፡
➕ የቅዱሳን <ቅድስና>የብፅዕና የቅድስና ተጋድሎ ታሪክ ገድል ቃልኪዳን እንገብይ እንምሰላቸውም፡፡
ዕብ ፲፫÷፯-፱
@kidusan_Z_ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2020-09-22 19:32:55 # የቅዱስ_ሶፍሮኒ_ጸሎት !
ዘላለማዊ ጌታና የሁሉ ፈጣሪ በማይሻር መልካምነትህ
ወደዚህ ሕይወት ጠርተኸኝ የጥምቀትን ጸጋ እና የመንፈስ
ቅዱስን ማኅተም ስጦታ ሰጠኸኝ ፡፡ ፊትህን የመፈለግ
መሻትን በውስጤ አኖርክ ፡፡ ጸሎቴን ስማ!
አቤቱ ያለ አንተ ሕይወት ፣ ብርሃን ፣ ደስታ፣ ኃይል ፣
ጥንካሬ ፣ ጥበብ የለኝም ፡፡ ከዓመፃዬ የተነሳ ዓይኖቼን
ወደ አንተ ለማንሳት አልደፍርም ፡፡ ነገር ግን
"አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ"
ያልከውን አንተን እታዘዛለሁ። (ማቴ 21: 22)። እውነት
እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ
ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤
ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። (ዮሐ
16፥23-24) ብለአል። ስለዚህ አሁን ወደ አንተ
ለመቅረብ ደፈርኩ፡፡ ከሥጋና ከመንፈስ እድፍ ሁሉ አንጻኝ
፡፡ በትክክል እንድፀልይ አስተምረኝ፡፡ ለማይገባኝ
አገልጋይህ ለእኔ የሰጠኸውን ቀን ባርክ፡፡ በበረከትህ
ኃይል ሁልጊዜ በእምነት ፣ በተስፋና ፍቅር ፣ በትሕትና ፣
በትዕግሥት ፣ በገርነት ፣ በሰላም ፣ በንጽህና ፣ በታናሽነት
፣ በድፍረት እና በጥበብ የምናገረውንና የምሰራውን
በንጹህ መንፈስ ለአንተ ክብር እንድሠራ አድርገኝ።
ሁልጊዜ ህልው እና መገኘትህን አስታውቀኝ ፡፡ ጌታ
አምላክ ሆይ በማይለዋወጥ ቸርነትህ ፈቃድህን አሳየኝና
ያለ ኃጢአት በፊትህ እንድጓዝ አድርገኝ፡፡ አቤቱ ልቦች ሁሉ
የተከፈቱልህ ፤ የምፈልገውን እና የሚያስፈልገኝን
ታውቃለህ። ዓይነ ስውርነቴን እና ድንቁርናዬን ታውቃለህ፡፡
የእኔን ድካም እና በደል ታውቃለህ፡፡ የእኔ ህመም እና
ጭንቀት ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡ ስለዚህ
እለምንሃለሁ ጸሎቴን ስማኝ የምሄድበትን መንገድ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይልህ አስተምረኝ፡፡ ጠማማነቴ በሌላ
መንገድ አይምራኝ። አቤቱ አትተወኝ ይልቅ ወደ መንገድህ
መልሰኝ፡፡
ጌታ ሆይ በፍቅርህ ኃይል መልካም የሆነውን አጥብቄ
እንድይዝ እርዳኝ ። ነፍስን ከሚያቆሽሽ ከማንኛውም ቃልና
ድርጊት ሁሉ ፣ በፊትህም ከማይደሰት እና በዙሪያዬ ላሉት
ሰዎችን ከምጎዳበት ከማንኛውም ስሜቶቼ ጠብቀኝ፡፡ ምን
ማለት እንዳለብኝ እና እንዴት እንደምናገር አስተምረኝ ፡፡
ዝምታዬ ቅዱስ ፈቃድህ ከሆነ ዝም እንድል እና መልስ
እንዳልሰጥ እርዳኝ። ሌሎች ሰዎችን እንዳልጎዳና
እንዳልሰብር በሰላም መንፈስ ዝም እንድል አነቃቃኝ
አበረታታኝ ፡፡ በትእዛዛትህ መንገድ አቁመኝ ፣ እስከ
መጨረሻ እስትንፋሴ ድረስ ከመንግሥትህ የብርሃን ህግ
እንዳልለይ እርዳኝ። አቤቱ ወደ አንተ እጸልያለሁ ማረኝ ፡፡
በመከራና በጭንቀት ጊዜ አድነኝ የማዳንህም መንገድ
ከእኔ አትሰውር፡፡ በሞኝነቴ እግዚአብሔር ሆይ ስለ ብዙ
እና ታላላቅ ነገሮች እለምንሃለሁ ፡፡ ግን እኔ ሁል ጊዜ
ክፋቴን ፣ ኃጢአቴን ፣ በደሌን አስባለሁ ማረኝ! በሞኝነቴ
ትምክህት ከአንተ ፊትም አትጣለኝ ፡፡ ከሰው ሁሉ ይልቅ
ኃጥህ የሆንኩ እኔ እንደ ትዕዛዝህ አንተን በፍጹም ልቤ ፣
በፍጹም ነፍሴ ፣ በፍጹም አሳቤ ፣ በፍጹም ኃይሌ
እንድወድህ የምችልበትን ጉልበትና ጸጋህን ስጠኝ።
ጌታ ሆይ ፣ በመንፈስ ቅዱስ መልካሙን ማስተዋልን
ስጠኝ፤ መሠረታዊውን ነገር አስተምረኝ ፡፡ ከመሞቴ በፊት
እውነትን አሳውቀኝ ፡፡ ለኃጢአቶቼ ከልቤ ንስሃ ሳልገባ
አትውሰደኝ። አዕምሮዬ በክፋት ታውሮ አትውሰደኝ ፡፡
ሕይወቴን ለማጠናቀቅ በደረስኩ ጊዜ ነፍሴን በፊትህ
እንድትመጣ እንዳዘጋጃት ማስጠንቀቂያ ስጠኝ ፡፡ ጌታ
ሆይ በዚያ አስደናቂ ሰዓት ከእኔ ጋር ሁን መድኃኒቴ
ደስታዬ በጸጋህ መዳኔን አረጋግጠኝ።
በምስጢር ከሰራሇቸው ኃጢአቶች አንጻኝ ፡፡ ከተሰወረ
በደል እጠበኝ፡፡ በፍርድ ወንበርህ ፊት እንዳላፍር መልስን
ስጠኝ፡፡
ትርጉም ፡ ብስራት ገብርኤል
[ምንጭ ፦ Orthodox Mistry Prayer at
Daybreak by St. Sophrony of Essex]
3.5K viewsYadesa Damena, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ