Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው ዘመን ክርስትና እንደገና ያብባል! የእግዚአብሔር ክብር ተመልሶ አብያተክርስቲያናት፣ አ | የክብረወሰን መልእክት

በመጪው ዘመን ክርስትና እንደገና ያብባል!

የእግዚአብሔር ክብር ተመልሶ አብያተክርስቲያናት፣ አደባባዮች፣ ስታድዬሞችና አዳራሾች በክብር ደመና ይሞላሉ።
አብያተክርስቲያናት ሁሉአምላካቸውን በመንፈስና በእውነት በሚያመልኩ አማኞች ተሞልተው እናያለን። ነፍሳት ሁሉ ወደ አዳኙ ጌታ ሲፈጥኑ የሚታይበት ዘመን ይመጣል።

አዲስ ትውልድ ይነሳል! ከኢትዮጵያ የሰላም ወንጌል መልዕክተኞች አፍሪካን አልፈው አውሮፓንና አሜሪካን አዳርሰው የወንጌልን እዳ ሊከፍሉ የሚንቀሳቀሱበት ወሳኝ ዘመን ይመጣል።

ፀሎት ይህንን ተስፋ ያፋጥናል! ምንን?
➥ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የምትዘረጋበትን ዘመን፤
➥የሪቫይቫልን ዘመን፤
➥የተሀድሶን ዘመን፤
➥ የኢትዮጵያን የብልፅግና ዘመን፤
➥ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መልዕክተኛነት ዘመን፤...

ስለዚህ ጎበዝ እንነሳና አሁን መፀለይ እንጀምር። እጃችንን ወደፈጠረን ጌታ እናንሳ።

https://t.me/KibreSolEmu
https://t.me/KibreSolEmu
https://t.me/KibreSolEmu