Get Mystery Box with random crypto!

የፀሎት ህይወታቹን ጠብቁ ሰይጣን እናንተን ሊነጥቃቹ የሚፈልገው አንድ ውድ ሀብት አላቹ፤ እርሱም | የክብረወሰን መልእክት

የፀሎት ህይወታቹን ጠብቁ

ሰይጣን እናንተን ሊነጥቃቹ የሚፈልገው አንድ ውድ ሀብት አላቹ፤ እርሱም የፀሎት ህወታቹን ነው፤ የፀሎት ህይወታቹ እየደከመባቹ ያላቹ ሰዎች ካላቹ አሁኑኑ ፈጥናቹ ወደቀድሞ ህይወታቹ ተመለሱ፤ ካለዚያ ግን ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ ያገኝና ህይወታቹን ያበላሸዋል። ለምሳሌ አንድ አይናቹ አመም ቢያደርገውና ማየት ቢያቅተው ዝም ትሉታላቹ በእርግጠኝነት አትሉትም ምክንያቱም ምን ያህል እንደሚጠቅማቹ ስለምታውቁት፤ የአባቴ ልጆች ፀሎትም ልክ እንደዚሁ ነው፤ ብዙ ሰዎች ወዳልተገባ ህይወት የገቡት የፀሎት ህይወታቸውን በገዛ ራሳቸው አሰርቀው ነው፤ ስለዚህ በጌታ ቤት መኖር ከፈለጋቹ ከምንምና ከማንም በላይ ለፀሎት ህይወታቹ ቅድሚያ ስጡ።

የደከማቹ ካላቹ መንፈስ ቅዱስ ያግዛቿል


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost