Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳን እባካችሁ በፀሎት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው ። | የክብረወሰን መልእክት

ቅዱሳን እባካችሁ በፀሎት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ!

ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው ። እኛ ለእርሱ የምንናገርበት እርሱም ለእኛ በቃሉ፣ በአንድም በሌላ ፣ በወደደበት መንገድ የሚናገርበት መሳሪያ ነው።እኛም እርሱን የምናዳምጥበትና የምንሰማበት እርሱም እኛን የሚያደምጥበት መንገድ ነው።
ከእግዚአብሔር ጋር አብሮነትን፣ ወዳጅነትን፣ ቤተሰብነትን እና ህብረትን የምንፈጥርበት መሳሪያ ነው።
ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ፊት ለመድረስ የምንጓዝበት መሰላል ነው።
የምንማልደው፣ የምንናዘዘው፣ የምናመሰግነው እና የምናወድሰው በፀሎት ነው።
የጠላትን ሰራዊት የምናስረው፣ ሀይሉን የምንመታውና ምሽጉን የምናፈርሰው በፀሎት ነው።
የታመሙት የሚፈወሱት፣ እንቆቅልሽ የሚፈታው፣ ተአምራትና ድንቅ የሚገለጠው በፀሎት ነው።

ስለዚህ አማኞች በዚህ አለም ላይ በሚኖሩባቸው ዘመናት ሁሉ ተግተው መፀለይ አለባቸው።
ምክኒያቱም ፀሎት ለሁሉም ነገር መሰረት ስለሆነ።

https://t.me/KibreSolEmu
https://t.me/KibreSolEmu
https://t.me/KibreSolEmu