Get Mystery Box with random crypto!

በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰው ተከሳሽ ላይ በፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነ | 🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰው ተከሳሽ ላይ በፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነ ተከሳሽ ሞገስ ሙላት ለራሱ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ በቁጥር የሰ/ሃ/459/09 በቀን 15/02/2009 ለትክል ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሲቪል መኃንዲስ ባወጣው ማስታወቂያ ተወዳዳሪዎች ለትምህርት ደረጃው መነሻ የብቃት ማረጋገጫ COC ማቅረብ እንዳለባቸው ማስታወቂያው ስለሚገልፅ ተከሳሽም በዚህ ማስታወቂያ ከሳንጃ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ደረጃ lV በኢንሳይት ቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለዚህም የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ እንዳለፈ በማስመሰል በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ምዘናና ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመለያ ቁጥር CONBBC 2014 _ 2017 _03_ 154548 በሐሰት በማዘጋጀት በወጣው ማስታወቂያ ተመዝግቦ በማለፍ እና ስራ ላይ ሆኖ እየተገለገለ ብር 59,930.00 የማይገባውን ክፍያ /ጥቅም በማግኘቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፓሊስ መምርያ የሙስና ወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል በተከሳሹ ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምርያ የሙስና ጉዳይ ወንጀል የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን ምርምሮ በሰውና እና በሰነድ ማስረጃ ወንጀሉ ሰለመፈፀሙ አረጋግጦ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ በማቅረብ ጉዳዮ በክርክር ቆይቶ በ28.8.2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 አመት ፅኑ እስራት እና በብር 60,000 እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት መረጃውን ያደረሰን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ነው።