Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ 'ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ? ከሆነ በውሃው | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

"ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ? ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖቹ ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ፤ ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።" ዴርቶጋዳ

ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡

"ጦርነት በሕይወትና በቁስ ላይ ከሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ የሚያስጠላ ነገር በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ በመካከሉ የሚፈጠሩትን ልዩነቶች በውይይትና በሠላም የሚፈታበት ቀን መች ይመጣ ይሆን? ያ ቀን ናፈቀኝ።" በዓሉ ግርማ

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@Kezimkezia