ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ ሰውን ከክፋት ፣ ከስስት ፣ ከዕብሪት ፣ ከትዕቢት ጋር የሚያፋቅረው የመጀመሪያው ምክንያት "ዝንጋዔ ሞት" ነው። ሞትን ያህል ዕዳ መቃብርን ያህል እንግዳ መዘንጋት ሰው በሀብቱ ና በጉልበቱ እንዲመካ ይገፋፋዋል፤ ማን አህሎኝነት ይወርሰዋል። ይህንን ከመሰረቱ የተረዱ ጥንታዊ ሮማውያን ለገዥዎቻቸው አንድ አዛውንት ይመድቡ ነበር። ገዥው ማለዳ ተነስቶ ቁርስ ሲጎርስ ያ አዛውንት ድንገት ዘው ብሎ በመግባት አንዲት ቃል ተናግሮ ይወጣል:- "ትሞታለህ!" ሮማዊ ጀኔራል ከድል መልስ በሰረገላ ሆኖ ወደ ከተማው ሲመለስ ህዝቡ ዘንባባ ይዞ በክብር ይቀበለዋል። ምርኮውንም እያግተለተለ ሲያልፍ በዚህ ደስታ መካከል ያ አዛውንት ከጄኔራሉ ጀርባ መጥቶ:- " ትሞታለህ!" ብሎት ያልፋል። ሞትን ማሰብ የመታበይ መድኅን ነው የመታበይ ብቻ ሳይሆን የማግበስበስ ፍቱን መድሃኒት ነውና። ዓለማየሁ ገላጋይ መለያየት ሞት ነው መልካም አዳር የነገ ሰው ይበለን @kezimkezia 2.7K viewsedited 15:39