Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ በቀናችን ውስጥ የሚገጥሙንን ማናቸውም የሕይወት ሁ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

በቀናችን ውስጥ የሚገጥሙንን ማናቸውም የሕይወት ሁኔታዎች ወደድንም ጠላንም ማስቀረት አንችልም፡፡ አንዳንድ ቀኖች በጣም ደስተኛ ያረጉናል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ይበልጥ ፈታኝ ይሆኑብናል።

የተፈጠረውን ማንኛውንም ነገር መቀበል እና ከሁኔታው ጋር እርቅ መፈጠር ግን ብልሀት ነው፡፡ በዚህ ታላቅ የሕይወት ሚስጥር ለመቆየት ከትላንት ጭንቀቶች መላቀቅ አለብን፤ ትኩረታችንን ወደ አሁን መልሰን ማደረግ ምንችለውን ማስተዋል ይገባናል፤ በነበር እና በይሆናል መጨነቅ ችግራችንን አንድ እርምጃ አይፈታልንም፡።

እራስህን ለሚመጣው አዲስ እድል ክፈት፤ በዚህ ውድ ጊዜ እራስህን ሁን፤ ትናንት ቀድሞውኑ አልፏልና ያለፈውን ተወው። በእያንዳንዱ አዲስ ቀን ድንቅ ነገር እንደሚፈጠር አስተውል። በቀንህ የሚገጥምህን ምንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ሁን።

ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይቻላል። ግን የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፤ የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር፤ ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ትናንትህን መልቀቅ ይኖርብሀል።

ቀንህን የደስታህ ምንጭ አድርጋት።
አንተ አሁን ላይ ሙሉ ሰው ነህ፤ አንቺም ነሽ፤ ዘና በል፤ ዘና በይ።

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@kezimkezia