Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፴፫~ ( 233) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 'እንደዛ ማድረግ አል | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፫~ ( 233)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እንደዛ ማድረግ አልነበረብሽም።ይሄ ትልቅ ነውር ነው። በዛ ሁሉ ሰው ፊት የማይሆን ነገር ነው ያደረግሺው።በዛ ላይ የእናንተንና የእናታችሁን ስራ ሁላቸውም ያውቃሉ።ይበልጥ ነውራችሁን ነው በአደባባይ የገለጣችሁት "አለ የማለፊያ ባል። "ውይ አንተ ደግሞ ተወኝ በሀዘኔ ላይ ሌላ ነገር አትጨምርብኝ"አለችውና ገላመጠችው። ባለቤቷም ትኩር ብሎ ከተመለከታት በኋላ "እኔማ እተውሻለሁ ስራሽ እንዲተውሽ ነው እንጅ ራስሽን መለመን"ብሏት ትቷት ወጣ
***
ቀዳማዊ ያለው ሁኔታ ምቾት ባይሰማውም በዚህ ጊዜ መሄዱን አልፈለገውም። ነገር ግን ሐምራዊ የሰሞኑ ሁኔታዋ ልክ ስላልሆነ። ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ተነሳ። "ትንሽ ብትቆዩ ደስ ይለን ነበር"አሉ ዳሳሽና ሙሉቀን እንደተለመደው ቅር ተሰኝተው። "እኛም ደስ ይለን ነበር። ግን ደግሞ"አለና ቀዳማዊ ወደ ሐምራዊ በመዞር የሚሄዱበትን ምክንያት ለማስረዳት ሞከረ። ሙሉቀን የቀዳማዊ የአይንን ጥቅሻ በሚገባ ስለተረዳ "እሺ ዛዲያ ምን እናደርጋለን እንኸዳለን ካላችሁማ"በማለት ተረታ። ዳሳሽም የሙሉቀንን ሀሳብ ከደቂቃዎች በፊት ተከትላ እንዳይሄዱ ስትለምን እንዳልቆየች አሁን ደግሞ የሙሉቀንን ሀሳብ እየደገፈች። "እሺ እንግዲህ መልካም መንገድ ይሁንላችሁ። በሰላም ያስገባችሁ"አለችና ተገናኝታቸው ተለያዩ። መልካሙ (አቤል) መኪናውን አስነስቶ ወደ ሐመረ ኖኅ ጉዞ ጀመሩ።
ሁላቸውም ለየብቻቸው የራሳቸውን ወሬ እያወሩ። ቀዳማዊና ሐምራዊም አፍ ለአፍ ገጥመው እየተጫወቱ ሀመረኖኅ ደረሱ። "እንግዲህ ወንድሜ አቤል ላደረከው ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ። በደንብ እንጫወታለን። ያው እንግዳ ስለያዝኩ ነው እንጅ በሰፊው ብንጫወት ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን እንደምታየው ነው"አለ ቀዳማዊ በትሕትና። "ኧረ ወንድሜ በሚገባ እረዳለሁ። በስልክም በምንም እንጫወታለን። እናንተ በሰላም ግቡ። ሙሽሪትም በሰላም ተገላገይ ማርያም በሽልም ታውጣሽ። ወንድሜ እንዳትረሳ ስትወልድ ወዲያው ንገረን"አለ መልካሙ (አቤል)። ቀዳማዊ አቀፈው። መልካሙም መልሶ አቅፎ ጀርባውን መታ መታ አደረገውና "እንኳንም አገኘንህ። አሁን በጣም ደስተኞች ነን።"ብሎት ሁላቸውንም በየተራ እጂ ነስቶ ተሰናበታቸው።
***
"በጣም ይቅርታ ጋሼ! ከባለቤቴ ጋር ሆነን ልንመጣ ነበር ያሰብነው። በመሀል ያው እሷ ትንሽ አመም ሲያደርጋት ቀጥታ ወደዚህ መጣን። ያው ነፍሰጡር ስለነበረች"አለ ቀዳማዊ "አውቃለሁ የኔ ልጅ የሆነ እክል ኤንደገጠመህ ገብቶናል። ትሕትናም ስትነግረኝ ነበር። ግዴለም ልጄ መገናኛ ዘዴ አናጣም። እኔ እንደውም አደዋወሌ እንኳን ደስ አለህ። ባባትህ ስም ትምህርት ቤት መክፈትህ ትልቅ ነገር ነው። አሁን ከመቼውም በላይ አስተዋይና ብልህ ልጅ መሆንህን ተረድቻለሁ"አለ ደረጄ ኩራት እየተሰማው። "አመሰግናለሁ ጋሼ ያው መሠረታችንን ካላጠበቅነው መቆም አንችልም። ምንም ያህል በደል የደረሰብኝ ቀዬ ቢሆንም ነገር ግን መሠረቴም መነሻዬ ነው። አባቴ ደግሞ የኔነት ሰሪ ነው። ስለዚህ ያን ውሳኔ ወሰንኩ"አለና ቀዳማዊ ሀሳቡን በትንሹም ቢሆን ጠቅለል አደረገ። "በጣም ጥሩ ነው ያደረከው"አለና ደረጄ አበረታታው።
ሐምራዊ ብዙም ሳትጨነቅ በሰላም ተገላገለች። ተስረቅራቂ የህፃን ልጅ ድምፅ ተሰማ። ሁሉም በእፎይታ ተነፈሱ። ቀዳማዊ የሆስፒታሉን ኮሪደር ወዲያና ወዲህ እያካለለ ሳለ የሐምራዊን የመውለድ ዜና ሰማ። "እንኳን ደስ አላችሁ ሐምራዊ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች።"አለ አዋላጁ። ቀዳማዊ ልቡ በሀሴት ተሞላ። ጭንቀቱ ከመቅፀበት ሄዶ በደስታ ተተካለት። "ተመስገን አምላኬ!"አለ ጮክ ብሎ።
***
ከወራቶች በኋላ የሆኑ የፊልም ኢንዱስትሪዎች በቀዳማዊ የመስሪያ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ጠቋሚነት ስለ ቀዳማዊ የሚያትተውን ዶክመንተሪ ፊልም በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለምርቃት ቀረበ። በዚህ የሕይወት ዘጋቢ ፊልም ላይ ቀዳማዊ የነካቸውና ከቀዳማዊ ጋር ተያያዥነች ያላቸው ቦታዎች ተዳሰዋል። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ምርቃት በርካታ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ተገኝተዋል። እንዲሁም በቀዳማዊ ተጋባዥነት የመጡ መሀንዲሶች ዶክተሮችና ሌሎችም ተገኝተዋል። የዘጋቢው ፊልም ዋና ዳይሬክተር ንግግር ካደረገ በኋላ ባለታሪኩን ለንግግር ቀዳማዊን ጋብዞ ወረደ። "ሕይወት መልከ ብዙ ቀለም አላት።በጣም ብዙ። ወድቀን ስንነሳ ይዘነው የምንነሳው ቀለም፣ እንዲሁም ከወደቅንበት ተነስተን አራግፍን የሚታየው የሕይወት ቀለም ሌላኛው ደግሞ ያንኑ ልብስ አቧራውን አራግፈን የነበረውን ልብስ አጥበን ስንለብስ የሚታየው የሕይወት ቀለም ነው። የመጨረሻው ያን ልብስ ቀይረን በሌላ ልብስ ራሳችንን የምናሳየው የሕይወት ቀለም ነው። በቅደም ተከተልና በሂደት የምንሰራው ራሳችንን መጨረሻችንን ይናገራል። ሰው ራሱን በሂደት እየሰራ የተሻለ ያደርጋል። እኔ በእኔ ፅናት ብቻ ነው እዚህ የደረስኩት ብዬ አላምንም። እግዚአብሔር ነው ለዚህ ሁሉ ያደረሰኝ። ያለ ፈጣሪ እርዳታ ምንም አልሆንም የትም አልደርስም ነበር። ምክንያቶችን እየፈጠረልኝ ሕይዎቴን የተሻለ እንድናደርግ ረድቶኛል።ለዚህም ክብርና ምስጋና ይግባው።ፈጣሪ ማስተማሪያ እንድሆን ከእኔ ሕይወት በርካቶች እንዲማሩ ለማስቻል ደግሞ እነዚህን ወንዶሞቼን በማነሳሳት ይሄን ዶክመንተሪ እንዲያዘጋጁ አድርጓቸዋል። እኔም ለእሱ ክብር ይግባውና ይሄው ስላለፈው ሕይወቴ የተደረሰን ፊልም አስመርቄ እየተናገርኩ ነው። በጣም እድለኝነት ይሰማኛል"ብሎ በርካታ የሕይወት ምሳሌዎችንና እውነታዎች አንስቶ ለታዳሚዎች አቅርቦ አመስግኖ ወረደ።
"የኔ ፍቅር እንኳን ደስ አለህ።በጊዜ አለቀ እንዴት ነበር"አለችና ሐምራዊ ሳመችው። "አመሰግናለሁ የኔ ፍቅር ጥሩ ነበር። እስኪ "ኤሴቅን ስጪኝ ልቀፋት"አላትና ሕፃኗን ተቀበላት። "ምንድን እሱ የኔ አበባ አባትሽን ታውቂዋለሽ?"እያለ ከኤሴቅ ጋር ይጫዎት ጀመር። "እንዴት ነው አባቷን የማታቀው በዚህ እድሜዋ አባቷን ካላወቀችማ ምኑን ልጅ ሆነችው"አለችና ሐምራዊ ሳቀች። "የአባቷን ጠረን የምታውቀው አሁን ነው"ብሎ ኮስተር አለ። "እሺ ይሁንልህ ተጃጃል!"አለችና እየሳቀች ወደ ኪችን ሄደች።
@amba88
@ken_leboch