Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፳፪~ ( 222) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 **** አይኖቿ ለመሟ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፪~ ( 222)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
****
አይኖቿ ለመሟሸት የተጣደ የሸክላ ድስት ቂጥ መስሏል። ከደምነት ቀለም ወደ ጥቁርነት ቀለም የተለወጠና ሁለቱንም ቀለማት የቀላቀለ ውህድ። በዘመናት ለቅሶ የማይመለስ በይቅርታም ሆነ በሌላ ግብረ መልስ የማይሽር በስህተት የታተመ የፍቅር ማህተብ። ከልቧ የማትፍቀው በእልህና በአልሸነፍ ባይነት የእድሜ ዘመኗ የሰነቀችው የፍቅር ስንቅ፤ ማዕበሉ በሚያናውጣት የተስፋ ወጀብ ውስጥም ሆና የምትናፍቀው ካፒቴኗ። ጀልባው መልህቋን ስትጠል በከዋክብት ታጅቦ በልቧ ሰማይ ላይ የሚሳል ውብ ድንቅና ማራኪ ቀለም። በልቧ ሸራ ላይ እያንዳንዱ ድርጊቱና ስኬቱ የተሳለ ብቸኛ የሕይወቷ ገጠመኝ ቀዳማዊ። አሁን የማይታመነውን አምናለች። እውነት በገሀድ ወጥታ መርዶዋን ነግራታለች። ቀዳማዊ በበረሃ ጋመን እንደሚሸሽ የዝናብ ጉም በደቂቃዎች ተኗል። የሕልሟ ካብ ተንዷል። ደሐብ ከዚህ በኋላ የምትኖረውን የገሀነም አለም አሰበችው። ጣዕሙ አልጣጣማት አለ። ውበቱ አልታያት አለ። ቀዳማዊ እስከወዲያኛው በሐምራዊ ልብ የሚዋኝ ዓሳ መሆኑን ለማመን ተገደደች። እስከመጨረሻው የሰርግ ስነስርአት ድረስ ተስፋ አልቆረጠችም ነበር። ምንም እንኳ ተስፋ የጣለችበት ነገር ተስፋ ባይኖረውም ግን እውነቱን ሳይሆን የልቧን እምነት ብቻ በተስፋ ትጠብቅ ነበር። ብቻ የማታውቀው ነገር ግን ሰርጉን የሚያስቀር ሐምራዊን የሚያስተው ታዕምር እንዲኖር ታስብ ነበር። በሞት ውስጥ ተስፋ የሚደረግ እምነትም ነበራት። ነገር ግን ሁሉም ነገር ከቅዥት ያለፈ አልነበረምና አንዱም ከእሱ ጋር ልትሆንበት የምትችልበት መንገድ አልተፈጠረም። አንዳንድ ጊዜ ከሚታየን እውነት ለመራቅ በሸሽን ቁጥርና ባለማመን መንፈስ ከተገትርን ሕይወት በሌላ የሕይወት አዙሪት ውስጥ አስገብታ ታጥረናለች።
በእንባ የራሰ አንሶላዋን ቀስ አድርጋ አጠፈችና ከአልጋዋ ተነሳች። ስልኳን ስትመለከት በርካታ ሚስኮሎችን አየች። ደዋዮቹ ቤርሳቤህ ኪሩቤልና ታሮስ ናቸው።ነገር ግን ታሮስ በርካታ ጥሪዎችን አድርጎ ነበር። የማናቸውንም ጥሪ አልሰማችውም።ሕይወት ለካ እንዲህ ጣዕሟ ይጎመዝዛል። መኖርም ጣዕም የሚኖረው ለካ በራሳችን ሕይወት የሚኖረን ተስፋና ሰው ሲኖር ነው። ለካ ሰው ራሱን የሚያጠፋው ሌላ የተሻለ አለም ፍለጋ ኖሯል። ለካ ዘመንም የምሽቱን አድማስ በጨለማ የሚተካው ከፅሐይ አንዳች መፍትሔ ሲያጣ ነው። ለካ ጭንቅላት ማረፊያ ዋርካ ሲያጣ ነው ያገኘው ሀሩር ላይ ተሰጥቶ እንደ ቅቤ የሚቀልጠው። ለካ የሚወዱትን የሚናፍቁትን ገላ እንደ ነፋስ ሽው ብሎ ሲያልፍ ልብም እንደ ቃየል መሄጃ እስክታጣ ትቅበዘበዛለች።
*
"እኔ ሁኔታዋ አላማረኝም። ብቻ ፈጣሪ ይርዳኝ እኔ እሷን አጥቼ መኖር አልችልም"አለ ታሮስ ሆድ ቁርጠት እንደ ተያዘ ሰው ሆዱን በእጁ ታቅፎ እየተቁነጠነጠ። "ታሮ ተረጋጋ ምንም አትሆንም ይሄን ያህል ጅል አይደለችም። በደንብ የምታስብና የምታሰላስል ብልህ ሴት እኮ ነች። ለማይረባ ስሜት ብላ ነገዋን የምታበላሽ ሴት አይደለችም" "የማይረባ ስሜት አትበል ኪሩቤል!!!!"ታሮስ በድንገት ጮኾ ኪሩቤል ላይ አንባረቀበት። "ፍቅር ነው የያዛት ገባህ ፍቅር ነው። ይሄ ደግሞ የማይረባ ስሜት አይደለም። ፍቅርን ማጣት ስሜቱን አታውቀውም። በርግጥ እንደዛ የምትሆንለት ሰው እኔ ብሆን ደስ ይለኝ ነበር ግን አይደለሁም በቃ እኔ አይደለሁም። እሱ ብቻ ነው ለዚህ የታደለው "አለ ታሮስ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ። ኪሩቤል የታሮስ ሁኔታ አብሰከሰከው"ወንድሜ እመነኝ። እሱ የራሱን ሕይወት መርጦ ጀምሯል። ደግሞ እሱ ፈልጎ እኖዳላደረገው ታውቃለህ። በቃ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው። አውቆ ሁለቱም እንዲወዱት ቢያደርግ ኑሮ ያው የምናደርገውን እናደርግ ነበር። ግን እሱ የራሱን ኑሮ ሲኖር በተፈጠረ ነገር ተወቃሽ ልናደርገው አይገባም። በዛ ላይ አሁን እስከወዲያኛው ከሕይወታችሁ ይጠፋል። በምንም ታዕምር ልታገኙትም ሆነ ልትገጣጠሙ አትችሉም" በማለት ኪሩቤል ሊያባብለው ሞከረ። "አዎ አሁን ጠንክረህ እሷንም የምታጠነክርበት ጊዜ ነው። በጭራሽ እጅ አትስጥ እሱን እንድታስበው ለማድረግ ቦታ መስጠት የለብህም። ጊዜህን ስጣት። እኛ ሴቶች ከምንም በላይ የምንፈልገው ጊዜውን የሚሰጠንን ወንድ ነው። ገንዘብ ብትሰጣት ገንዘቡን መልሰህ ታገኘዋለህ። ሌላም ነገር ብትሰጣት መልሰህ የምታገኝበት እድል ሰፊ ነው። ጊዜ ግን አንዴ ከሄደ ሄደ ነው። የማይመለስ ጊዜውን የሰጠ ወንድ ደግሞ ፍቅሩን በቃላት ከሚገልፅላት በላይ ይገልፅላታል። ስለዚህ ጠንከር በልና አጠንክራት ጓደኛዬን በሚገባ አውቃታለሁ። ለጊዜው ነው እንጅ የምትጎዳው በደንብ ምቾት ከሰጠኻትና ከተንከባከብካት ትረሳዋለች......."ብላ ቤርሳቤህ ልትቀጥል ስትል "ቆይ አንድ ጊዜ እሷ ናት መሰል"ብሎ የሚጠራ ስልኩነሰ ከኪሱ አውጥቶ ተመለከተው እውነትም ደሐብ ነበረች። "አቤት የኔ ፍቅር አስጨነቅሽኝ እኮ የት ነሽ የት ልምጣ?"አለ ታሮስ። "የትም አትምጣ እኔ እዛው ያለኽበት እመጣለሁ "አለችና ያለበትን ጠይቃው ስልኩን ዘጋች። "አላልኩህም! እሷ ምንም አትሆንም ደሐብ ነገዋን የምታበላሽ ሴት ሳትሆን በፈራረሰው የትላንት ትዝታዋ ዛሬዋን የምታሰማምር ነገዋን ደግሞ የምታስውብ ሴት እንጅ ተሸንፋ ከሜዳ የምትወጣ ሴት አይደለችም። እና ወዳጄ ደስ ልትሰኝ ይገባል የእሷ ባል በመሆንህ አሁን ደስታችሁን የምታከብሩበት ቀን ሩቅ አይደለም"አለና ኪሩቤል በፈገግታ የታሮስን ትከሻ መታ መታ አደረገው።
**
"በሉ ሁሉንም እርሱት። የራሳችንን የወሬ ርዕስ ፈጥረን ነው እንጅ መጫወት ያለብን ሕመሟን የሚያስታውስ ወሬ ማንሳት የለብንም። ታሮስ በጣም ተጠንቀቅ ነግሬሀለሁ በምንም ታዕምር ስለ ቀዳማዊ ምንም ነገር እንዳታነሳ"ብሎ ኪሩቤል አስጠነቀቀው። "እሺ ምንም አታስብ ጓደኛዬ በጭራሽ አላነሳባትም"አለ ታሮስ። "እሺ ክቡራንና ክቡራት እዚህ ተሰብስባችሁ የየአዲስ አበባን ድንቅ ተፈጥሮ ትቋደሱልኛለችሁ አይደል?"አለችና ደሐብ የምፀት ፈገግታዋን ፈገግ ብላ ሁላቸውንም ስማ ታሮስ ቆሞ ያዘጋጀላት ወንበር ላይ ስባ ተቀመጠች። "እንዴት ነው እዚህ ሆናችሁ ስትመለከቱት የአዲስ አበባን ውብ ገፅታ?"አለች ደሐብ " እንግዲህ እንደ አስተያየታችን ነው። በመሀንዲስ አይን ካየናት ህንፃና መንገድ እንዲሁም በርካታ ፋብሪካዎችና የኤሌክትሪክ መብራቶች ይታያሉ። በዶክተሮች እይታ ደግሞ ታካሚዎችና በርካታ የታካሚዎች አስታማሚዎች ሲታዩ ሒሳብ ባለሞያዎች አይን ደግሞ። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እምብርት መሆኗንና በርካታ ገንዘቦቸሰ የሚንሸራሸርባት የንግድ ማዕከል ሆና ስትታየው። ሁሉም እንደየ ሰው አይንና እንደሚስማማው ወይም እንዲሚሰራው ስራ ቆጥሮ ያላትንና የሚጎላትን ይተነትናል"አለ ታሮስ ኪሩቤል እግሩን በእግሩ መታ አደረገው። ኪሩቤል የታሮስ ወሬ አጀማመር አላማረውም መዳረሻው ቀዳማዊን ማሳሰብ እንዳይሆን ሰግቷል። ታሮስ የኪሩቤል ጉሽምታ በሚገባ ተረድቶታል ወሬ ለመቀየር ብሎ "ፍቅሬ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ አይደል? ቅድም አሁን ስልክ ሳታነሺ ስትቀሪ በጣም ጨንቆኝ ነበር"አለ ታሮስ ደሐብ ለታሮስ ልትመልስለት ስትል ኪሩቤል ፊቱን አጨፈገገና በንዴት ታሮስን እየተመለከተ.........

@amba88
@ken_leboch