Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | ቅን ልቦች

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#የመጨረሻው_ክፍል

... እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን
ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ
ታጥበው ነበር.............
.........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል
እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው
አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ብሩክን
አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ
ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም
የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን
ለመዋጥ ስታስብ ብሩክ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ብሩኬ
ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ
ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ
ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት
እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ
ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ
ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች
ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም
አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ
እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ
ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም
ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ
በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ቅዱስ ነኝ በቤትስልክ
ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የቅዱስ ድምፅ
ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም
አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ
12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ
አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ
እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ብሩክ ተመልሶ
መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም
ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ..........
ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው
ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ
ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን
እያየች ቅዱስ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት
ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ
ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች......
......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም
ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር
ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ቅዱስ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን
ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮን ነበረ
ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም
ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ
የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ
በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ
ድኖ ጋቢ ለብሶ ከቅዱስ ቡሀላ እየተራመደ መጣ...........
............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ
በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው
መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ
ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮን
አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮ
እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ
መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ
ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ
እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮ
አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር
በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ
ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች
ጌዲዮ ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ
ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም
እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ
አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር
የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው
ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው
የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮም ቤተሰቦቿ
መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ
ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን
ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ
ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ
እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር
ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ በረከት ሲያይ ጠጋ ብሎ
እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው
ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ
ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ
አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም
አላቸው..............
.............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ
እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ
እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ
ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ
እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት
በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ
ስለሚውምመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ
ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ
አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች
አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር
እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮ የመቅደስ
ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት.......
........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም
በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ
አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ
ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር
አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ
ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........

ተፈፀመ

#ምስጋና
:-ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት በ @Tesfish2 ያድርሱን፡፡


ከወደዱት ሼር ያድርጉ


,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@ken_leboch // ,, @Tesfish2
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━