Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | ቅን ልቦች

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_27

... የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት
ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን
ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን
ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም
ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት.................
.........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት
ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ
ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር
ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት
ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት
እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ
ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች
ነው........
.....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን
መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች
ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ
በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ
እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን
ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች
ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ
ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት
ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ
ቢወድቁም አልማርም አለች ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና
በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው
ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል
አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር
ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም
ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት
አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ
ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ
ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ
መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ
ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ
መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት
እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ...
.....ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ
ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ
አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን
አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው
ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው
የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ
የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ
በፀሎት አልተለዩትም እንደምታስታውሱት በክፍል ሀያ አምስት
ላይ ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት
አንስቶ አስታማሚው ቅዱስ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ
ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን
ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ...


ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@ken_leboch // ,, @Tesfish2
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━