Get Mystery Box with random crypto!

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~ ክፍል 3 ....ነገር ግን እንባዋ ይበልጥ ይፈስ ጀመር... እንደ | ከመፃሕፍት ጥግ

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~

ክፍል 3

....ነገር ግን እንባዋ ይበልጥ ይፈስ ጀመር... እንደዚህ መሆኗ ይበልጥ እያስደነገጠኝ ይመጣ ጀመር። ከዚህ የተለየ የማላውቀው ነገር እንዳለ ጠየኳት ነገር ግን አሁንም ከዝምታ በስተቀር መልስ አልሰጠቺኝም ግራ መበጋባት ስሜት "ምን እዛው የመቅረት ሀሳብ አለሽ? ፣ በእኔ እርግጠኛ አይደለሽም? ፣ ወይንስ "ሌላ ሰው አግብተሽ ነው እንዴ የምትሄጅው" አልኳት ከረጅም ዝምታ በኃላ አንገቷን እያወዛወዘች "አዎ" አለቺኝ..... "አዎ" የሚለው ቃል ልቤን እንደሰማ እንደጦር የሚወጋ ስሜት ይሰማኝ ጀመር። በቤተሰቦቿ ጫና ምክንያት ወደ ውጪ አግብታ ልትሄድ መሆኑኑ ብቻ ነገራኝ ዝም አለች ። ያኔ ውስጤ በጣም ተረበሸ አይኔ ላይ ባንዴ እንባዬ በጉንጮቼ ይወርድ ጀመረ። እንባዬ እንዳታይ እና ይበልጥ እንዳይከፋት ብዬ ፊቴን አዞርኩት ነገር ግን መቆጣጠር አቃተኝ። ፍቅር በጣም እንደምታፈቅረኝ ስለማውቅ እንባዬን እንደምንም ተቆጣጥሬ የሚሰማኝን የልቤን መሰበር ሳላሳውቅ እሷን ማባበል እና ማረጋጋቱን አስቀደምኩት። በጣም እንደማፈቅራት እና ማድረግ የምችለውን ሁሉ እንደምናደርግ፣ የሄድኩበትም የደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደማያሳፍረኝ፣ እኔም አንቺም ጋር ንፁህ እውነተኛ ፍቅር ስላላ ምንም አይለየንም አልኳት። ከሷ ግን እንባ ያቀረሩ አይኖቿ ውጪ ዝምታን መርጣለች።
በዚህ ሀሳብ ውስጥ ብዙ ዝምታዎች፣ ብዙ የውስጥ ህመሞች ሁለታችንም ጋር ቃላት በሌለው የእንባ አይኖች ጋር በዝምታ ብዙ ደቂቃዎች አለፉ። ለዝምታዎቻችን ማቅለያ ይሆን ዘንድ በብዛት እርሷ የምታዳምጣቸው ዘፈኖች እና አብረን ሆነን የምናዳምጣቸው ሙዚቃዎች ስልኬን አውጥቼ ከዮቲዩብ ከፈትኩት። በዝምታዎቻችን ላይ ብዙ ትውስታዎችን የምናስብበት ሙዚቃ በስሱ ተከፍተዋል። ከቆይታ በኃላ እራሴን አረጋግቼ ይሄንን ዝምታውን መቀየር እንዳለብኝ ተሰምቶኝ ጥረት ማድረግ ጀመርኩ። እንደዛው እንዳለች ይሄም ፈተና እንደሚያልፍ በማሰብ በእርሷ ስልክ ሰልፊ ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ... ነይ ሳሚኝ ብያት ከተደገፈችበት የኃላ ወንበር የደኔ ጠጋ ብላ ጉንጬን ስትስመኝ እንባዋ ውስጥ ከታመቀው ትንፏሿ ጋር ሰውነቴን ሲነካኝ ይበልጥ ደረት ላይ የሚወጋ ስሜት ተሰማኝ። ጉንጬን እየሳመቺኝ ፎቶውን አንስቼው ይሄንን ፎቶ ቴሌግራም ላይ ላኪልኝ አልኳት። ቀን አልፎ ነገሮችን ካስተካከልነው በኋላ ይህንን ፎቶ ማስታወሻ ይሆነናል አልኩኝ ለራሴ። ዝምታችን እንዳይቀጥል ለነገ ጉዞ የግድ ሻንጣ ማዘጋጀት እንዳለባት ነግሬያት መኪናችንን አስነስቼ ወደ ሰፈሯ መንገድ ጀመርን ነገር ግን አሁንም አብራኝም ሆና የምር ትናፍቀኛች። ከፊት መታ እንድትቀመጥ አደረኩኝ እና በጎን አንገቷን ትከሻዬ ላይ ደገፍ ብላ ጉዞአችንን ወደ ሰፈሯ ማድረግ ጀመርን። ነገር ግን ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ስንደርስ እኔም እሷም ናፍቆታችን አሁንም ስላልወጣል ነው መሰለኝ እራት እንብላ በሚል ምክንያት ወደ አንድ ሬስቱራንት ሄድን። እዛም አስተናጋጁን ፒዛ እና ለሷ ከቀዝቃዛ ፋንታ አናናስ ለኔ እስኘራይት እንዲያመጣልን ነገርኩት። (ፍቅር ፒዛ በጣም ትወዳለች) ያዘዝነው ፒዛ መኪናችን ውስጥ ከመጣልን በኋላ አብረን እንዳሳለፍናቸው አመታት ሁሉ ቅድሚያ እሷን እያጎረስኩዋት በዛ የልብ መሰበር ስሜት ውስጥ ሆኜ የራሴን ሀዘን ዋጥ አድርጌ እሷን ለማስደሰት እና ከዛ ስሜት እንድትወጣ ጥረት ማድረጌን እሷ እያንዳንዱን ነገሮች ሁሉ በማስተዋል እያየች ነበር እና ከአይኗ እንባ እየፈሰሰ እንዲ አለቺን "በጣም አፈቅርሀለሁ! አንተን በጣም የተለየህ እና በጣም ጥሩ ሰው ነህ አንተን ማስቀየም እጅግ በጣም ከባድ ነው" አለቺኝ። እኔ እንባ እየተናነቀኝ አይን አይኗን እያየሁ "እኔም በጣም አፈቅርሻለሁ! ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባል ሰው አይደለሁም ግን አብረን ላሳለፍናቸው እናዛ ምርጥ የፍቅር አመታት እና ለወደፊት አብረን ስንኖር ምርጡ እና ጥሩ የሚባል ባልሽ ለመሆን ግን እየሞከርኩኝ ነው" ብዬ እንባ ባራሰው ፊቴ ደስተኛ ለመምሰል ፈገግ አልኩኝ።

#ይቀጥላል

ነቢያት ሙሉጌታ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....