2023-02-19 15:18:18
ዘወረደ
የአቢይ ጾም የመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል
ይህ ዕለት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ነው
አምላክ ከሰማይ ስለመውረዱ
ለሰው ልጆች በረከትን ስለማደሉ በስፋት ይነገራል
በዐቢይ ጾም ውስጥ ስምንት ሳምንታት ያሉ ሲሆን
ቅዱስ ያሬድ የየራሳቸው ስያሜ ሰይሟቸዋል
ዘወረደ
ቅድስት
ምኩራብ
መፃጉዕ
ደብረዘይት
ገብር ኄር
ኒቆዲሞስ
ሆሣዕና ናቸው
እነዚህ የየራሳቸው ምሥጢር እና ታሪክ ያላቸው ሲሆን
የመጀመሪያው ሣምንት ዘወረደ ይባላል
ከሰማየ ሰማያት የወረደው ከድንግል ማርያም የተወለደው
ለኩነተ ሥጋ የመጣው
ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም
ከድንግል ማርያም ያለ እናት የተወደውን ልዩ ልደት ይነገራል
ይህ ጾም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ካሉት ሰባቱ አጽዋማት ታላቁና
ራሱ ጌታችን የጾመው ጾም ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል።
ይህች የዘወረደ ሳምንት
ጾመ ሕርቃል በመባል ይታወቃል
ይህ ሳምንት በሕርቃል ስም የተሰየመው
የራሱ የሆነ ምሥጢር ያለው ሲሆን
በ714 ዓመተ ምህረት በቤዛንታይን ነግሦ የነበረ ንጉሥ ነው
በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወረው የጌታችንን መስቀል ማርከው ወደ ፋርስ ወስደውት ስለነበረ ምዕመናን እያዘኑ ይኖሩ ነበረ
እባክህን መስቀሉን ከፋርስ ባባቢሎን አምጣልን አሉት
ንጉሡ ሕርቃል አማኝ ንጉሥ ስለነበረ
ከፋርሳውያን ጋር ከመዋጋቱ በፊቱ ሐዋርያት በሲኖዶስ
ነፍስ የገደለ ሰው እስከ ዕድሜ ልኩ ይጹም ብለው ሥርዓት
ሠርተዋልና ጾሙን ፈርቶ ስለነበረ
በኢየሩሳሌም የነበሩ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባቸው ምዕመናን
በአንድነት ሆነው የአንድ ሰው ዕድሜ ሰባ ነው ቢበዛ ሰማንያ ነው
እኛ በኢየሩሳሌም የምንኖር ምዕመናን አንድ አንድ ሳምንት ስላንተ እንጾምልሃለን ብለውት ተስማምተው
ወደ ፋርስ ዘምቶ መስቀሉን ከፋርሳውያን እጅ ነጥቆ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል።
ይህንንም መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜው ጾመ ሕርቃል ብላ ትጾመዋለች
ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ ያሬድ ስለ ዘወረደ
በስፋት በጾመ ድጓው ያመሰጥረዋል
ዘወረደ እምላእሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእምሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሀዩ በቃሉ
ከሰማይ የወረደውን ከድንግል የተወለደውን አይሁድ ሰቀሉት
የዓለም ጌታ መሆኑን አላወቁም
አይሁድ ከሰማይ የወረደው ከድንግል የተወለደው ማን እንደ ሆነ አላወቁም
በዚህ ዓለም ከባዱ ነገር
የእግዚአብሔርን አባታዊ ፍቅር አለመረዳት
እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ምድር የተጓዘውን ጉዞ አለማስተዋል
የተከፈልልንን ዋጋአለማቅ
ከባዱ ኃጢአት ይህ ነው
እግዚአብሔር የከፈለለትን ዋጋ የሚያውቅ ሰው
ክብሩን ሁሉ ለአምላኩ ሲል ይተዋል
አምላክ ከሰማይ ወርዷል ከድንግል ተወልዷል
እኔም አለኝ ከሜለው ሁሉ ልውረድ
ከአልጋ ወርጄ ፈቃደ እግዚአብሔርን ልፈጽም
ይላል
ግን በዚህ ዘመን ማን ይሆን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን እየፈለገበረከትን የሚሻ
እባካችሁ
ማን እንደኛ የምትሉ
ጊዜው የኛ ነው የምትሉ
በዘር በፖለቲካ የምትወሸቁ
እባካችሁ ውረዱ
የቤተ ክርስቲያን አምላክ የወረደው እኛን ከፍ ሊያደርግ ነው
የተዋረደው እኛን ሊያከብረን ነው
የሞተው እኛን ሊያነሣን ነውና
እባካችሁ ወደ ልባችን እንመለስ
መዝሙሩም ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ነው
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ ይላል
መዝሙሩና የዕለቱ ስብከት እንመለስበታለን
የቅዱሳን አምላክ ማስተዋሉን ያድለን ጾሙን የበረከት ያድርግልን
ጸልዩ በእንተሰ ሰላም ስለ
ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራስላሉት እንጸልይ
በልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራ ስላሉት እንጸልይ
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሰላሙን ያጽናልን
አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
አዲስ አበባ 11/06/2015
ሼር ማድረግዎን እንዳይረሱ
49 views12:18