Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ክብሮም

የቴሌግራም ቻናል አርማ kebrom01 — ዘማሪ ክብሮም
የቴሌግራም ቻናል አርማ kebrom01 — ዘማሪ ክብሮም
የሰርጥ አድራሻ: @kebrom01
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 224

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-05 13:43:19
36 views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 10:38:05 #መርቋቸው ፃድቃኔ ማርያምን ሕንፃ ቤተክርስቲያኗን አስዉባችሁ ሰርታቹሃል ኢንጂነር ብስሬ ክብር ይገባቹሃል አሁንም በእጃችሁ ላይ ያሉትንም የሕንፃ ቤተክርስቲያን ያስፈፅማችሁ። ወንድሞቼ እግዚአብሔር አምላክ በብዙ ይባርካችሁ
81 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 10:38:01
75 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 13:19:26
79 views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 14:38:31
96 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 14:26:13 በወቅታዊ ጉዳዮች ከማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት የተላለፈ መልእክት

ማኅበረ ቅዱሳን በኢ/አ/ተ/ቤ/ን ቅዱስ ሲኖዶሶ በ1984 ዓ.ም እውቅና አግኝቶ በ1994 ዓ.ም በጸደቀለት ሕገ ደንብ መሠረት አገልግሎቱን ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም የቅድስት ቤተክርስቲያን ዐቢይ ተልዕኮ የሆነውን የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግሥት በስፋት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ እንዲዳረስ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል። በየጊዜው ያጋጠሙትን ፈተናዎችን እግዚአብሔር ቸርነት በከፍተኛ ትጋትና ጽናት ያለፈ መሆኑን ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ማኅበሩ ካሉት የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አንዱ የብሮድካስት አገልግሎቱ ሲሆን፤ በ2012 ዓ/ም የተጀመረው ይህ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጨው የወንጌል አገልግሎት በመላው ምእመን ዘንድ አማራጭ ሚዲያ ከመሆን አልፎ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው የየዕለት ስንቅ በመሆን በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ እንደ ዐይን ብሌን የሚጠብቁት ሚዲያ ለመሆን በቅቷል።

የብሮድካስት አገልግሎት ልዩ ጥንቃቄ የሚሻ ሥራ ከመሆኑም በተጨማሪ ማኅበራችን አገልግሎቱን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና መንፈሳዊ ቅኝት የሚያከናውን በመሆኑ ሁሌም ምስጉንና የተከበረ ጣቢያ መሆኑን ምእመናን ሁሉ የሚመሰክሩት እውነታ ነው።

በዚህ መነሻነት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሜቴ ያዘጋጀውን መግለጫ በማስተላለፋችን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ "ጊዜያዊ እገዳ" ማድረጉን ገልጾልናል፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለጊዜያዊ እገዳ የሰጠው ምክንያት ማኅበሩ ከተቋቋመለት ዓለማ ውጭ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ እንኳን ሊያሳግድ ይቅርና ጥያቄ ሊነሳበት የማይገባ ጉዳይ መሆኑን ማኅበሩ ይረዳል። የእግዱ ሂደትም የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን ያልተከተለና የሚዲያውን አገልግሎት በጸሎት፣ በገንዘብና በእውቀታችሁ በመደገፍ ሊዚህ ያበቃችሁትን ካህናት፣ ምእመናንና አባላትን ያሳዘነ መሆኑን ተረድተናል፡፡

በመሆኑም እግዱ የምእመናን ድምጽ የሚያፍን ብሎም ትምህርተ ወንጌልን የመማር መብታቸውን የሚገድብ መሆኑን በማሳወቅ ለሚመለከተው አካል አቤቱታውን በደብዳቤ አቅርቧል። አቤቱታውም በአግባቡና በሕጉ መሠረት ታይቶ በጎ ምላሽ እንደሚሰጠው ተስፋ እናደርጋለን። እንዲሁም ማኅበራችን ጉዳዩ የሕግ አግባብን ተከትሎ ውሳኔ እስከሚያገኝ አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲገነዘብልንና ይህንኑ በየጊዜው በይፋ የምናሳውቅ ስለሆነ በታላቅ ትዕግሥት አንዲጠብቅ እንጠይቃለን።

በዚህ አጋጣሚ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ስለ ጉዳዩ በተፈጠረባችሁ ቁጭትና ከፍተኛ የቁጣ ስሜት የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር ለምታደርጉት ተነሳሽነት ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ከፍተኛ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።

በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦቱ ርክበ ካህናት ስብሰባ ግንቦት 14/2015 ዓ.ም ባደረገው ምልአተ ጉባኤ ችግር ባለባቸውና አስፈላጊ በሆኑ አኅጉረ ስብከቶች ፱ አዳዲስ ኤጴስ ቆጶሳትን በጥናት ለመሾም አስመራጭ ኮሜቴ መሰየሙ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የምርጫ ሄደቱም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የተከተለ፣ ግልጽነት ያለው፣ ካህናትና ምእመናንን ያሳተፈ እንደሚሆን እንጠብቃለን፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡
78 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 09:25:02
41 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 09:24:50 የልደትሽ ቀን
ልደታችን ነው

ኢያቄም ወ ሀና ወለዱ ሰማዬ
ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐዬ

እያቄም እና ሀና ሰማይን ወለዱ
ሰማዩ ደሞ ፀሐይን አስገኘች
እንኳን አደረሳቹ።

የዩቲዩብ ቻናሌን በዚህ ሊንክ #Subscribe በማድረግ ይጎብኙ ይከታተሉ
https://youtube.com/channel/UCheSkImxBegvVbRUxEmxqCQ

ቴሌግራም ቻናሉንም ይቀላቀሉ አዳዲስ መረጃዎችንም ያግኙ
https://t.me/kebrom01

ለፌስቡክ
https://www.facebook.com/zema

ለዩቲዩብ
https://youtube.com/@zemarikebromtube1302
41 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 09:14:15
35 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 09:13:50 እንኳን አደረሳቸሁ አደረሰን
“መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤”
* መዝ 86፥1*
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ"

➠የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም
የሁላችንም እናት ልደቷን ስናከብር ቅር ሚላቸው ሰዎች ካሉ ይህን ቃል ያስተውሉ
“ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”
ሉቃስ 1፥14 ልደት ማለት መወለድ ማለት ነው። በመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ሚደሰቱ ከሆነ ታዲያ እውነተኛው ዳኛ፣አማናዊውን ፀሐይ፣እውነተኛውን መብልና መጠጥ፣ቅን ፈራጁን ኢየሱስ ክርስቶስ የወለደች የእናቱን(የእናታችን) የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደትማ እንዴት አናክብር ያው በልዩ ሁኔታ ልደትሽ ልደታችን ነው ብለን እናከብረዋለን።
ዘማሪ ክብሮም ገብረኪዳን
ግንቦት 01/09/2015 ዓ.
38 views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ