Get Mystery Box with random crypto!

'ከወቀሳ በፊት ምክር ይቅደም፦' 'ለክርስትና መቆርቆርና በክርስትና ስም መነቆር ይለያያል። የተሳ | ከ

'ከወቀሳ በፊት ምክር ይቅደም፦'

"ለክርስትና መቆርቆርና በክርስትና ስም መነቆር ይለያያል። የተሳሳተን መመለስ የተጣመመን ማቅናት የወንድምን ድካም መሸፈን የክርስቲያኖች ባህሪ ነው ፤ መጀመሪያ ምክር ነው የሚቀድመው ከወቀሳው ።

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ፤የቤተክርስቲያን ለዛ ያሬዳዊው ውበት ጠፍቷል ፤ አዳራሽ እንድንለማመድ ከዓውደ ምሕረት እንድንርቅ መሳለም መስገድ መዳበስ እንድንተው አደጋ አለው ብሎ አሳብ ማቅረብ ይቻላል።

አሳብ ሰጥቶ አስተያየት አቅርቦ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ እርምት እንዲደረግባቸው አካሄዱን በመለየት በጥበብ ሴራም ካለው አክሽፎ ተንኮል ካለው በቅንነት አሸንፎ እሺ ካለ በፈሊጥ እንቢ ካለ በፍልጥ ልኩን ማሲያዝ ይቻላል።

አዋቂ መሳይ የእምነት ተቆርቋሪ፣ ሆኖ ከአዋቂዎች በላይ ተሟጋች ሆኖ መቅረብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው ፤ በስሜት ሳይሆን በስሌት መሄዱ የተሻለም ነው ባይ ነኝ።..."
-